BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Monday, 4 August 2014

አንድ መቶ ሰባ አምስት ኪሎ ወርቅ ከሃገር ሊወጣ ሲል ቢያዝም በሳሞራ የኑስ ትእዛዝ እንዲያልፍ ተደርጓል።

ምንሊክ ሳልሳዊ

  • 661
    Share
የጄኔራል ሳሞራ የኑስ እንደሆነ የሚጠረጠረው አንድ መቶ ሰባ አምስት ኪሎ ወርቅ ከአገር ሊወጣ ሲል ተይዞ የነበረ ቢሆንም በጄኔራሉ ትእዛዝ ከአገር እንዲወጣ መደረጉን የአየር መንገዱ የደህንነት ምንጮች ጠቁመዋል። ይህ በሁለት ካርቶን ታሽጎ በበረራ ቁጥር 600 እና 612 ወደ ዱባይ ሊሻገር ሲል በቁጥጥር ስር የዋለው ወርቅ በጊዜው ባለንብረቱ ተፈልገው ባለመገኘታቸው እንዲቆይ ቢደረግም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ቦታው ድረስ አሽከሮቹን በመላክ እንዲለቀቅ እና እንዲያልፍ/እንዲጫን የተደረገ መሆኑ ታውቋል።

የጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ የክስ መቃወሚያ ቀጠሮ ተላለፈ

10516863_863085593719102_3664242472454329896_n

የዞን ዘጠኝ ስድስት ጦማርያንና ሶሰት ጋዜጠኞች በወንጀለኛ መቅጫ ህግና በፀረ ሽብር አዋጁ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የሽብር ወንጀል ለመፈፀም አቅደዋል፣ ተዘጋጅተዋል፣ አሲረዋል፣ አነሳስተዋል እንዲሁም ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሁከትና በአመፅ ለመለወጥ አስበዋል ተብለው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት በህገ መንግሥትና በህገ መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ በሚደረግ የሙከራ ወንጀል ተከሰው ባለፈው ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል፡፡ከሦስት ወራት የምርመራ ጊዜ በኃላ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡት ተከሳሾች በፅሑፍ የቀረበላቸውን ክስ ካደመጡ በኃላ በአቃቢ ህግና በጠበቆቻቸው መካከል በተደረገ የዋስትና ጥያቄ ክርክር ብይን ለመስጠትና የክስ መቃወሚያ ለማዳመጥ ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
በዛሬው ቀጠሮ ዘጠኙም ተከሳሾች ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም በዋስትና መብት ጉዳይ በጠበቃና በአቃቢ ሕግ መካከል የተደረገው ክርክር የህግ ትርጓሜ እንደሚያስፈልገው ጠበቃዎች በጠየቁት መሰረት ከመቅረጸ ድምጹ ላይ ተገልብጦ ለህግ አስተርጓሚ እንዲላክ እንዲሁም በሌለችበት ክስ የተመሰረተባት 1ኛ ተከሳሽ ሶሊያና ሽመልስ በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላት የተሰጠው ትዕዛዝ ባለመፈፀሙ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።