BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Thursday, 3 July 2014

የአቶ አንዳርጋቸው እገታ ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ከየአቅጣጫው ቁጣቸውን እየገለጹ ነው



ሰኔ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን መንግስት የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን  ማገቱን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች ቁጣቸውን እየገለጹ ነው።
አላማጣ አካባቢ የሚኖሩ አንድ አስተያየት ሰጪ  ” የየመን መንግስት ያገተው አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። በዚህ የቁርጥ ቀን ልጅ ላይ አንድ ነገር ቢደረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆ ብሎ ይነሳል። የመን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አብራ ለመኖር ካሰበች አንዳርጋቸውን በአሽኳይ ትልቀ ” ብለዋል።
ሌላ ወጣት ደግሞ ” አቶ አንዳርጋቸው የታሰሩት ለኢትዮጵያ ህዝብ እስከሆነ ድረስ ፣ ማንኛውንም መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን” ስሜቱን ገልጿል።

Wednesday, 2 July 2014

ግንቦት7 አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማስፈታት ጥረቱን መቀጠሉን አስታወቀ

ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው የስራ አስፈጻሚ አባልና የህዝባዊ እምቢተኝነት ዘርፍ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የየመን የጸጥታ ሃይሎች አቶ አንዳርጋቸውን በአስቸኳይ ይለቁት ዘንድ ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት ደብዳቤ ከመጻፍ ጀምሮ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፎችን እና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉበትን መንገድ እያመቻቹ ነው።
ግንቦት7 ለየመን ፕሬዚዳንት ፊልድ ማርሻል አብዱ ራቡ ማንሱር ሃዲ እኤአ ሰኔ 30፣ 20014 በጻፈው ደብዳቤ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን ህገወጥ በመሆኑ የየመን መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈታው ጠይቋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎቹን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፣ ጋዜጠኞችንና መንግስትን የሚተቹትን ሁሉ አስሮ የሚያሰቃይ መሆኑ በአለማቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ የተረጋገጠ መሆኑን በመጥቀስ፣ የየመን መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ተላልፎ ያለመሰጠት መብቱን እንዲያከብር ጠይቋል።

አቶ አንዳርጋቸው በየመን መንግስት ከታገቱ በሁዋላ የኢትዮጵያ ትምባሆ ድርጅት ለየመን ኩባንያ ተሰጠ

የግንቦት 7 አመራር አባል በየመን መንግስት ታግተው ከተያዙ ከአንድ ሳምንት ወዲህ የፕራይቬታይዜይሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ውሳኔ መስጠት በተቸገረበት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ሽያጭ ጉዳይ ላይ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሳኔ በመስጠት ለየመን ኩባንያዎች ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ እንዲወስዱ ተደረገ::

andargachew
በአሁኑ ወቅት የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግታ ባለችበት ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የየመኑ ኩባንያ ሼባ ኢንቨስትመንት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 60 በመቶ ባለቤት እንዲሆን መወሰኑ በርካታ ፖለቲከኞችን እያነጋገረ ይገኛል;:
ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው የ70 ዓመት ዕድሜ ባለቤት የሆነው ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 22 በመቶ የሚሆነው አክሲዮን ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ በየመኑ ሼባ ኢንቨስትመንት ሲያዝ፣ ቀሪው 78 በመቶ አክሲዮን ደግሞ በመንግሥት የተያዘ ነበር፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወሰነው አዲስ ውሳኔ ሼባ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 38 በመቶ አክሲዮን ከመንግሥት ላይ እንዲገዛ የሚፈቅድ በመሆኑ፣ ሼባ ኢንቨስትመንት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ላይ አንበሳውን ድርሻ 60 በመቶ ሲይዝ፣ መንግሥት ደግሞ 40 በመቶ ድርሻ ይዞ ይቀጥላል፡፡

Tuesday, 1 July 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ
ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም
የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቷል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን የጉዞው መዳረሻ አልነበረም፤ ከየመን ጋርም የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ አልነበረውም። የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግቶ ለአንድ ሰዓት እንኳን ለማቆየት ምንም ምክንያት የለውም። በዚህም ምክንያት ያለአግባብ የታገተብን የንቅናቄያችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። እንዲያውም የየመን ባለስልጣናት አምባገኑን ወያኔ ለመርዳት ባለው ፍላጎት ሳቢያ መሪያችንን አሳልፎ ሊሰጠው ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮብናል።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ጊዜውን፣ እውቀቱንና ጉልበቱን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ፤ ዝግጁነቱንም በተግባር ያሳየ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። የየመን መንግሥት ከዘረኛውና ፋሽስታዊው ወያኔ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ታጋይ መሪያችን ላይ እየፀመ ያለውን ደባ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅ የንቅናቄዓችን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስኗል።

ምርጫ ይራዘምን ምን አመጣው? ማንን ይጠቅማል? በግርማ ሰይፉ ማሩ (የፓርላማ አባል)

የሰላማዊ ትግል አማራጮች ብዙ እንደሆኑ የሰላማዊ ትግል መስመር የመረጡ ዜጎች እንደሚረዱት እሙን ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ፅሁፍ ያቀረበው ጄን ሻርፕ ከአንሰታይን ኢንስቲትዩት አንዱ ሲሆን ይህም በህዳር 1998 ወደ አማርኛ ተመልሶዋል፤ እርገጠኛ ነኝ ይህ ፅሁፍ እንዲተረጎም ያደረጉት ሰዎች ድህረ ምረጫ 97 የገጠመንን የሰላማዊ ትግል ክፍተት የተረዱ ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ  “የሰላማዊ ትግል 101” በሚል አንድ መፅኃፍ በሰላማዊ ትግል አቀንቃኙ ግርማ ሞገስ ለገበያ ቀርቦዋል፡፡ ይህ መፅሃፍ የቀረበበት ጊዜም ከምርጫ 2007 መቃረብ ጋር ሰናያይዘው ብዙ እንደምንማርበትና ስላማዊ ትግል ፈታኝ መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡

የሽብር - ዘፍጥረት (ተመስገን ደሳለኝ)


በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ፣ በመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ንቅናቄ መፈጠሩን ያስተዋለ  አልነበረም፤ …ከሺህ ዓመታት በፊት በአገር አልባነት፣ በተለያዩ የዓለም አህጉራት የተበታተኑት አይሁዳውያን ይደርስባቸው ከነበረው መገለልና ጭቆና (ፀረ-ጽዮናዊነት) ነፃ ለመውጣት በፈረንጆች አቆጣጠር በ1896 ዓ.ም. ቴዎድሮ ሄርዘል በተባለ ሰው መሪነት የጽዮናዊ ንቅናቄን መሰረቱ፤ ዋነኛ ዓላማውም ለዘመናት ሲናፍቋት ወደቆየችው ‹‹ተስፋይቱ ምድር›› መመለስን እውን ማድረግ ሲሆን፤ ይች ዕለት ትቀርብ ዘንዳም ገና ከልጅነት ዕድሜው ጀምሮ ‹‹ሃ-ቲካያ›› (ተስፋችን) የተሰኘውን ዝነኛ መዝሙር ሲዘምር የኖረው እያንዳንዱ አይሁዳዊ፣ ተደራጅቶ ለመታገል መወሰኑ ደስታውን ሰማይ ጥግ አደረሰው፤ ንቅናቄው ከተመሰረተ ከሁለት አስርታት በኋላም ባካሄደው የመጀመሪያው ኮንግረስ ታሪካዊ ሊባል የሚችል ውሳኔ ላይ ደረሰ፤ በአውሮፓ አገራት ተበታትነው ይኖሩ ከነበሩ ጽዮናውያን መካከል የተወሰኑት በግል ገንዘባቸውም ሆነ ቡድናቸው በሚያደርግላቸው ድጎማ ወደ ፍልስጤም በተናጠል ሄደው መሬት እየገዙ እንዲሰፍሩ የሚል ነበር፤

የኢትዮጵያ ህዝብ በዝምታ እየተቀበላቸው የሚገኙት በደሎች


የኢትዮጵያ ህዝብ በዝምታ እየተቀበላቸው የሚገኙት በደሎችከአንድነት ሃይሌ
በየመን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መታገትን በመስማቴ አዘንኩ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በዝምታ እየተቀበላቸው የሚገኙትን በደሎችም መለስ አድርጌ ባጭሩ እንድቃኝ አስገደደኝ።
ያሳዝናል! በአመት ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ህፃናት በማደጎነት ሲሸጡ እያየን፣ እየሰማን፤ ከ45 ሺህ በላይ ሴቶቻችን ለሳውዲ አረቢያ በቤት ሰራተኝነት ሲቸረቸሩና፤ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዜጎቻችን በተመሳሳይ መልኩ ለሌሎች አረብ ሃገራት በሃራጭ ሲሸጡ እያየን፣ እየሰማን፤ ሴቶቻችን በየ አረብ ሃገሩ ለመስማት እጅግ በሚያዳግት ሁኔታ አሰቃቂ በደሎች ባደባባይ ሲፈፀምባቸው እያየን፣ እየሰማን፤ አያሌ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ህይወታቸውን ለማትረፍና ለማሻሻል ወደተለያዩ ሃገራት ተሰደው ስቃይ ውስጥ እንደሚገኙ እያየን፣ እየሰማን፤ ከዚህም በላይ ደግሞ ይህ ሁሉ በደል በዜጎች ላይ ሲፈፀም ቢያንስ ተቃውሞውን ሊያሰማ ፈፅሞ ፍላጎት የሌለው፤ ይባስ ብሎ በደሉን በተቃወሙ ዜጎች ላይ ከበዳዮቹ ሃገራት ጋር በማበር ንፁሃን ዜጎችን የሚደበድብ፣ የሚያስር ጭካኝ ስርዓት በጫንቃችን ተሸክመን፤ አንጀታችን እያረረ፣ ልባችን በሃዘን እየተጎዳ፣ ሞራላችን በውድቀት እየተሰበረ፣ አንገታችንን ደፍተን በዝምታ እየኖርን እንገኛለን።