BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Sunday, 27 July 2014

ሰማያዊ ፓርቲ ምሁራን ተሳትፈውበታል ያለውን የቃል ኪዳን ሰነድ ይፋ አደረገ

ሰማያዊ ፓርቲ ምሁራን ተሳትፈውበታል ያለውን የቃል ኪዳን ሰነድ ይፋ አደረገ-ፓርቲዎች በድርጅታዊ ፕሮግራሞቻቸው ውስጥ እንዲያካትቱት ጠይቋል ሰማያዊ ፓርቲ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ በርካታ ምሁራን ተወያይተውበት ብዙ ጥናትና ምርምር አድርገውበታል ያለውንና ‹‹የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ›› በሚል መጠሪያ ያዘጋጀውን ሐምሌ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ይፋ አደረገ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ይፋ ያደረገው የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ዜጎች በጋራ አንድ ሆነው ሊስማሙባቸው የሚችሉ፣ አጠቃላይ በአገራቸው ሁኔታ ላይ የሚግባቡባቸው ጉዳዮችን የያዘ የጋራ ሰነድ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ከፕሮግራም፣ ከፖለቲካ ሐሳብ፣ ከአስተሳሰብና ለወቅታዊ ችግሮች መፍትሔ ከመስጠት ልዩነት ባሻገር፣ ኢትዮጵያዊያን እንደ አገር የሚግባቡበት አንድ የጋራ ሰነድ አስፈላጊ መሆኑን ፓርቲው ገልጿል፡፡ ይህም ሰነድ ፓርቲው ብቃት ባላቸው ምሁራን ተጠንቶና ውይይት ተደርጎበት፣ ሕዝብ ውይይት አድርጎበት አንድ የሚሆንበትና ‹ሕገ መሠረት› (የሕገ መንግሥት ማርቀቂያ መነሻ መሠረት) ሲል የጠራው ሰነድ መሆኑን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) ገልጸዋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደብረዘይት አየር ሃይል ግቢ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

ሐምሌ ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሰኔ 18 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ ደብረዘይት በሚገኘው የአየር ሃይል ግቢ ውስጥ በአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
ኢሳት የተለያዩ ምንጮችን አነጋግሮ ባሰባሰበው መረጃ አቶ አንዳርጋቸው በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ድበደባው ቆሞ፣ የማሰቃያ መርፌዎችን እየተወጉና በኤልክትሪክ ሾክ እየተሰቃዩ መረጃ እንዲያወጡ እየተገደዱ ነው።
መርማሪዎች ከአቶ አንዳርጋቸው የሚፈልጉት መረጃ ከግንቦት7 ጋር በጋራ የሚሰሩ  አሁን በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግን አመራሮችን እንዲሁም በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያሉ አዛዦችን ስሞች ሲሆን፣ አቶ አንዳርጋቸው ግን እስካሁን ምንም አይነት መረጃ ባለመስጠታቸው ፣ መርማሪዎች ሲበሳጩ መታየታቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ለወትሮው አንድ መረጃ ሲያገኙ በታላቅ ደስታ የሚፈነጩት መርማሪዎች፣ ምርመራቸውን ጨርሰው ሲወጡ የሚያሳዩት ብስጭት፣ እስካሁን ድረስ የሚፈልጉትን እንዳላገኙ የሚያሳይ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል።

Saturday, 19 July 2014

ጨቋኙ እና አምባገነኑ የወያኔ ቡድን በሴቶች እህቶቻችን ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ (የአብስራ ዳኛቸው)

ወያኔ በ97ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ አይን ባወጣ ድርቅና ምርጫውን በማጭበርበር በአሸናፊነት ተወጥቻለሁ ብሎ የንፁሁን ህዝብ ድምፅ በመንጠቅ እና ድምፁ የነጠቀውን ህዝብ ያደረገውን ተቋውሞ በመሳርያ ሀይል በመጠቀም የንፁሁን ህዝብ ደም በማፍሰስ እና አካል በማጉደል በማን አለብኝነት ፖርላማውን ለብቻው በመቆጣጠር ህዝቡን ያለ ፍላጎት በግድ ሲገዛ የማህበረሰቡ አንድ አካል የሆኑ ሴቶች እህቶቻችን በወያኔ የደረሰውን እልቂት በመመልከት ከፖለቲካ ትግላቸው የሚሸሹና የሚያቆሙ መስሎ ተሰምቶት ነበር በአንፃሩ ግን ቡዙ ለአላማቸው ፅኑ የሆኑ ሴት ታጋዮች እንዲፈጠሩ መንገድ ከፍቷል።
        ሴቶች እህቶቻችን ተቋውሞአቸዉን ለመግለፅ እና በአለም ማህረሰብ ላይ ስለ ሀገራቸው ተጨባጭ ሁኔታ ለማሳወቅ ያስገደዳቸው ነገር ጨቋኙ የወያኔ ቡድን የሴቶችን መብት በሀገሪቷ ላይ ተንሰራፍቶ ባለው ስርአት እና በስርአቱ አንቀሳቃሾች እየደረሰባቸው ያለውን ግፍ አይምሮዋቸው ተቀብሎት አምኖ መቀበል ስላቃተው ነው።
        አምባገነኑ የወያኔ ስርአት በሀገሪቱ ላይ ዲሞክራሲን ያለገደብ አስፍኛለው በማለት ሴቶች እህቶቻችን በነፃነት የመናገር ሀሳባቸውን የመግለፅ መብት አላቸው በማለት ሲነገር ይደመጣል ነገር ግን እየተገበረ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው ለዚህም ምስክር የሚሆኑት በአሁኑ ሰአት በወያኔ እስር ቤት ተጥለው ከሚገኙት እንኳን ወጣቷ ጋዜጠኛ እና መምህርት ርዮት ተጠቃሽ ናት።

ለዴሞክራሲ ነፃነት በሚደረግ ትግል የሚሸበረው ማን ነው?!

ጌታቸው ፏፏቴ
መግቢያ፦ በሜዳ የሚደረገው ትግል እየጠነከረ ሲሄድና ዳሩ መሃል እየሆነ ሲመጣ ነገሮች ሁሉ አዳጋች ሲሆኑ ገዥዎች በሥልጣን ለመሰንበት የሚወስዷቸውን እርምጃዎች ከዚህ ቀደም ደርግ ይወስድ ከነበረው ርምጃ በቂ ትምህርት አግኝተናል። በጭፍን አስተሳሰብ ዐይኑ ያልወደደውን ሁሉ ወደ እስር ማጋዝና ነጻ ርምጃ በሚል ፈሊጥ በጅምላ ሕዝብ ጨፍጭፏል። «የፍየል ወጠጤ ልቡ ያበጠበት»ሳይባል የተገደሉትን ብርቅየ የኢትዮጵያ ልጆችማ ቤት ይቁጠራቸው።

ህወሃት አሁን የሚገኘበት ደረጃ የሚያሳየውም ያነውኑ ነው። በሰላማዊ መንገድ መታገል በራሱ በህወሃት ሕግ የተፈቀደ ነበር። ነገር ግን አንዲት ጠጠር ሳይወረውሩና ቅጠል ሳይበጥሱ ሕጉ በሚፈቅድላቸው መንገድ በመሄድ እየታገሉ ባሉ የተቃዋሚ ኃይሎች ላይ ህወሃት ያደረሰባቸውን እንግልት እስራትና ንብረት ዘረፋ ተመልክተናል። በአብዛኛው እኔ በመጣሁበት መንገድ ካልመጣችሁ በማለት ገፊ ሁኔታዎችን እየተነኮሰም ነው። የሰላማዊ ትግሉን እንዳይቻል አድርጐታል እንጅ ቢቻል በሰላማዊ መንገድ ታግሎ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሥልጣን መረከብ ወይም ማስረከብ የ21ኛው መቶ ዓመት ሥልጡን ህዝብ ጨዋ ሥነ-ምግባር ነበር። እነዚህ የኛ ድናቁርቶች ግን በሕገ-አራዊት እየተመሩ ነገር የሚገባቸው ሆነው አልተገኙም።

Friday, 18 July 2014

በለንደን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አድረጉ

ሐምሌ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በመገኘት ፣ የኢህአዴግ መንግስት በግንቦት7 ዋና ጸሃፊ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ
በወሰደው ህገወጥ እርምጃ የእንግሊዝ መንግስት ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። በስፍራው የነበረውን ዘጋቢያችን ወንድማገኝ ጋሹን አነጋግረነዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ አሸባሪዎችን እንዲዋጋላቸው በሚል ኢህአዴግን የሚደግፉት አሜሪካና እንግሊዝ፣ አገዛዙ በዜጎቹ ላይ በሚፈጽመው ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ገልጿል።

ሰበር ዜና:- ጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ ላይ ሽብርተኛ ተብለው ክስ ተመሠረተባቸው

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ጦማሪያን፣ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ፣ እንዲሁም ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ላይ ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡ተጠርጣሪዎቹ የሽብርተኝነት ወንጀል በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተሳታፊ በመሆን ለአመፅ ተግባር በህቡዕ መደራጀታቸውን፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው የክስ ቻርጅ ይገልጻል፡፡

Ethiopia charges journalists with 'terrorism'

Three journalists and seven bloggers, in prison since April, accused of plotting "to destablise the nation".
A group of Ethiopian bloggers and journalists held in jail for nearly three months have been charged with terrorism for having links to an outlawed group and for planning attacks, a judge said.
The seven members of the blogging collective Zone Nine and three journalists were arrested in April, prompting an outcry from rights groups who said the case was an assault on press freedom.
"They took training in how to make explosives and planned to train others," Judge Tareke Alemayehu told the court on Friday.