BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Wednesday, 29 October 2014

ሃብታሙ አያሌው ቶርቸር እየተደረገ ነው !

ክስ ሳይመሰረትበት ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ግፍ እየተፈጸመበት እንደሆነ ታወቀ። 

ሃብታሙ አያሌው ለአንድ ሳምንት ወደ መጸዳጃ ቤት እንድዳይሄድ በመከልከሉ በፌስትታል ይጠቀም እንደነበረ፣ ለሶስት ሳምንታትም ቁጥር ስምንት በምትባል የጨለማ ቤት ዉስጥ ለብቻው እንዲቀመጥ መደረጉንም አረጋግጠናል።

ባለፉት 23 ዓመታት ውስጥ በልጆቻቸው መታሰር በፅኑ ሃዘን የተወጉትን እናቶች ማሳያ የሆኑት 70 ዓመታት ያለፋቸው. . . . .

 የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ተመስገን በተፈረደበት ዕለት የነበሩበትን ሁኔታ የተመስገን ወንድም እንደፃፈው (ኦድዮ) ያድምጡት



http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35800

ሚኒስትሮች ባልተወራረደ የመንግስት ገንዘብ ጉዳይ ላይ ጎራ ለይተው ተከራከሩ

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ዋና ኦዲተር፣ አባካኝ የመንግስት ተቋማት በሚል ለጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት እና ለተወካዮች ም/ክር ቤት አፈ ጉባኤ ያቀረበው ሪፖርት ለህዝብ ይፋ ይሁን አይሁን የሚለው ጉዳይ  ሚኒስትሮችን አወዛግቧል።
አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አቶ ደመቀ መኮንን፣ አቶ አዲሱ ለገሰና አቶ ጸጋየ በርሄ፣ የፌደራል ኦዲተሩ ሪፖርት ለህዝብ በፍጹም ሪፖርት መደረግ የለበትም ብለው ሲከራከሩ፣ የመንግስት ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ከማል፡ ለህዝቡ ይፋ በሆነ  መልኩ የማሳወቅ እርምጃ መውሰድ ይገባል የሚል አቋም አንጸባርቀዋል። አቶ በረከት ስምኦንና ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለዘብተኛ የሆነ አስተያየት በመስጠት አቃም ለመያዝ በመቸገራቸው ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም።

አዲስ አበባ ውስጥ ሌሊት የሚለጠፉ ወረቀቶችን ተከትሎ ውጥረት መንገሱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ፖሉ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን ነገረ ኢትዮጵያ በዘገባው አመልክቷል።

የወ/ሮ አዜብ መስፍን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መዳከሙ ተሰማ

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለቤታቸውን በድንገተኛ ሞት ከማጣታቸው በፊት የፓርላማ አባል የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በራሳቸው ፍቃድ ፓርላማውን ከመልቀቃቸውም በተጨማሪ በድርጅታዊ ስራዎች ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እየተዳከመ መምጣቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ አዜብ ባለፈው አንድ ዓመት በፓርላማው መቀመጫቸው ላይ ታይተው የማያውቁ ሲሆን ለፓርላማው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ወይዘሮዋ  በራሳቸው ፈቃድ ከፓርላማ አባልነታቸው መሰናበታቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ወቅት  የትግራይ ክልል ካለው 38 የፓርላማ መቀመጫ ሁለቱ በእርሳቸውና ባለቤታቸው መያዙ ይታወቃል:: እንዲሁም በ2003 ዓ.ም በስምንተኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ወቅት መለስከህወሃት 9 የሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል ወ/ሮ አዜብን በማስመረጥ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ እንዲቀላቀሉ አድርገዋል፡፡

Saturday, 25 October 2014