BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!
Friday, 6 February 2015
Thursday, 5 February 2015
በአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ መከረ
ጥር ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህብረቱ ጥር 27፣2007 ዓም በብራሰልስ ቤልጂየም የአውሮፓ ህብረት ጽ/ቤት ውስጥ ለ3 ሰአታት ባደረገው የኢትዮጵያ የሰአብአዊ መብት ግምገማ በኦጋዴን ክልል እና በተቀሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ሰቆቃ የአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታት በዝምታ መመልከታቸውን ማብቃት አለበት የሚል ውሳኔ አስተላልፈዋል።
ስብሰባውን ያዘጋጁት የህብረቱ የሶሻሊስትና የዲሞክራቲክ ፓርቲዎች ጥምር ህብረት ፣ ውክልና አልባ ህዝቦች ተቆርቋሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው።
በአማራና ትግራይ ድንበር የተነሳውን ውዝግብ ለመፍታት የተጠራው ስብሰባ ተበተነ፧፧
ጥር ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራና በትግራይ ክልል ድንበሮች አካባቢ የተነሳውን ችግር ለመፍታት ከፌደራል መንግስት ፣ ከትግራይና ከአማራ ክልል የተውጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጥር 26 ቀን 2007 ዓም ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጡ 300 ነዋሪዎችን ሰብስበው ያነጋገሩ ቢሆንም፣ መግባባት ሳይቻል በመቅረቱ ለየካቲት 4 በድጋሜ መቀጠሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ሽፈራው ተክለማርያም፣ የአማራ ክልል ፕ/ት ገዱ አንዳርጋቸው፣ የትግራይ ክልል ፕ/ት አባይ ወልዱ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ የሰሜን ምእራብ እዝ አዛዥ ሌ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ዘመቻ ሃላፊ ሜ/ጄኔራል ገብረእግዚአብሄር መብራቱ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣኖች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል።
Wednesday, 4 February 2015
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሩ በደረሰባቸው ድብደባና መድኃኒት ክልከላ ሕይወታቸው አለፈ።
Andenet members join Semayawi Party
WASHINGTON, DC - A week or so ago, the opposition party Unity for Justice and Democracy (UDJ)- widely known by its Ethiopian name Andenet - was brimming with confidence that it will contend for power in the national elections in May 2015. Of course, there was an uphill battle, and that was to make sure the elections would be free and fair.የዞን 9 ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ሰብሳቢ ዳኛው ከችሎቱ እንዲነሱላቸው ጠየቁ
ጥር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ላለፉት 9 ወራት በ እስር ላይ ይሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ሰብሳቢ ዳኛው ከችሎት እንዲነሱ ጠየቁ፡፡
ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ለ17ኛ ጊዜ ጥር 26/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ ቸሎት ሲቀርቡ በጽሁፍ ባቀረቡት አቤቱታ፦ የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ የሆኑት አቶ ሸለመ በቀለ ፦‹‹የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታችንን አላስከበሩልንም›› በማለት ከችሎት እንዲነሱ ጠይቀዋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)
.png)
