BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 29 October 2013

ድንግል ማርያም-የማራኪ ክርስቲያናዊ ሕይወት ምሳሌ


ድንግል ማርያም-የማራኪ ክርስቲያናዊ ሕይወት ምሳሌ
መጽሐፍ ቅዱስ ድንግል ማርያም ከዳዊት ዘር መወለዷን ይመሰክራል፡፡ (ማቴ. 11-18)፡፡ የቤተክርስቲያን የትውፊት ትምህርት ደግሞ ከኢያቄምና ከሐና በሕግ በሆነ ሩካቤ እንደተወለደች፤ በንፅህናና በቅድስና በመቅደስ እንዳደገች ያስተምራል፡፡ (ቅዳሴ ማርያም . 38 ገጽ 169)፡፡ ድንግል ማርያም መድኃኒት ወደ ዓለም የገባባት በር ናት፡፡ እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን የቀጠረው ቀን ሲደርስ የአንድያ ልጁ ዙፋን አደረጋት፡፡ ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እርሷ ተልኮ መጣ፡፡ ከእግዚአብሔር የሠማውን የምስራች ሰበከላት፤ የሰውን ልጅ የመዳን ዜና አበሰራት፡፡ (ሉቃ. 126-36፡፡ ቅዳሴ ማርያም . 45 ገፅ 170)

በራማው መልአክ የሰላምታ ቃል ውስጥ የድንግል ማርያም ውበት ተብራርቷል፡፡ ከተለዩ የተለየች፤ ከከበሩት የከበረች፤ ከተመረጡት የተመረጠች እንደሆነች ተገልጧል፡፡ መልአኩአባቶችሽ ሱባኤ የቆጠሩለት፣ ትንቢት የተናገሩለት መሲህ ካንቺ ይወለዳልና ደስ ይበልሽ፡፡ ሕይወትን የሚደግፋት፤ ሁሉን የሚያድን፤ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ አባቶችሽ በጽድቅ ያመለኩት እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና፡፡ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ (ለክብሩ ዙፋን የተለየሽ) ነሽአላት፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአካላዊ ቃል (የመለኮት) ማደሪያ ሆናለች፡፡ አባቱ በዙፋኑ ሆኖ ሲያይ በትሕትናዋ ልቡ አረፈ፤ በትህትና ለሚገለጠው ልጁ እናት አደረጋት፡፡ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ናት፡፡ 431 . በጉባኤ ኤፌሶን ንስጥሮስ ከተወገዘባቸው ሃይማኖታዊ ጉዳዮች አንዱ ክርስቶስ አምላክ መሆኑን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ መሆኗን ስለካደ ነው፡፡ በጊዜው የነበሩት የክርስትናው ዓለም ሊቃውንት ንስጥሮስን አውግዘውክርስቶስ የዘላለም አምላክ መሆኑን፤ እናቱ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ (Theotokos) መሆኗን መስክረዋል፡፡ የእመቤታችን ትልቅ ክብር አምላክን ለመውለድ መመረጧ ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ እሳት የነካው ትውልድ የጌታዬ እናት ብሎ ይጠራታል፡፡ ሉቃ. 143፡፡ የወለደችው ልጇም ክብሯ፣ ጌታዋ፣ አምላኳና መድኃኒቷ ነው፡፡ በልጇ ቀልድ አታውቅም፡፡ (ሉቃ. 147)፡፡
ድንግል ማርያም የደስታ መፍሰሻ ናት፡፡ የመላእክትን ተድላ ደስታ የምእመናንን ፋሲካ ኢየሱስ ክርስቶስን ወልዳለችና፡፡ ሀዘን የወጋውን ልብ በደስታ የሚያፈካው፣ አልቃሻውን ዓለም የደስታ ዘይት ያፈሰሰበት፤ የናዝሬቱ ኢየሱስ የማይወሰድ ደስታ፤ የማይነጠቅ በጎ እድል ነው፡፡ ዳዊት በአባቱ ቀኝ ያለ ፍሰሀ ብሎ ተመክቶበታል፡፡ (መዝ. 1511)፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የክርስትና ትልቅ ፊደል ናት፡፡ድንግል ማርያም የማራኪ ክርስቲያናዊ ሕይወት ምሳሌ ናት፡፡አምብሮስ (Ibid 2:2:6, p116:208) እግዚአብሔር በድንግል ማርያም ሕይወት ውስጥ የልጁን መልክ ስሏል፡፡ ከሕይወቷ ገጽ የምናነበው አርአያነት አላት፡፡ እስኪ እናንብባት፡-
1. የእምነት ሕይወት፡- ከመልአኩ በድንግልና የመውለድን ዜና ስትሰማእንዴት ይሆናል?” የሚል ጥያቄ አነሳች፡፡ መልአኩምለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም፡፡በማለት የእምነትን መሰረት ሰበከላት፡፡ እርስዋም በእምነትየጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝብላ መለሰች፡፡ በእግዚአብሔር መቻል ተደገፈች፡፡ ፀሐፊው ሉቃስምያመነች ብፅዕት ናትብሎ መሠከረላት፡፡ (ሉቃ. 136-46)፡፡ ሴት ያለወንድ ዘር ወለደች የሚል የዓለም ዜና የለም፡፡ የዓለም ሥርዓት በተፈጥሮ ሥርዓት ግዛት ሥር ነው፡፡ ድንግልን መልአኩ ያለ ወንድ ዘር በድንግልና ትወልጃለሽ፤ ይህም በእግዚአብሔር መቻልና ማስቻል ይከናወናል፤ ሲላት በእምነት ተቀበለች፡፡ በቃና ገሊላ ሠርግም ሁሉን እንደሚችል አምና ጠየቀችው ሁሉን ቻይነቱንም ሰበከች፡፡የሚላችሁን አድርጉብላ አዘዘች (ዮሐ. 21-11)፡፡ የማይሆን ያልነው በእግዚአብሔር መቻል እንደሚሆን ካመንን ድንግልን በእምነት መስለናታል፡፡ ዛሬ በእምነት ሳይሆን በማየት የሚመላለሱ፤ በራሳቸው ማስተዋል የተደገፉ፣ በእግዚአብሔር መቻል የማይተማመኑ ሰዎች እየበዙ ነው፡፡ ከድንግል ማርያም ሕይወት እምነትን እንዲማሩ እንጋብዛለን፡፡

2. የድንግልና ሕይወት፡- ድንግል ማርያም ኢሳይያስ ቀድሞ የተናገረላት ድንግል ናት፡፡ ኢሳ. 714፡፡ ሕዝቅኤልም በምስራቅ ያያት የተዘጋች ደጅ፤ የታጠረች ተክል ናት፡፡ ድንግል በድንግልና ወለደች፡፡ የወለደችው ከእርሷ በፊት የነበረውን ፈጣሪዋን ነው፡፡ ቅዱስ ቄርሎስድንግል ፈጣሪዋን ወለደችእንዳለ፡፡ ስለዚህ የድንግልና ሕይወት አርአያ ናት፡፡

ሴት ከሁለቱ ምርጫዎች አንዱን ብቻ ትጠቀማለች፡፡ ወይ ወልዶ መሳምን ወይ በድንግልና መኖን፡፡ በድንግልና መኖር ምርጫዋ ከሆነ የእናትነት ፀጋን ታጣለች፡፡ እናት መሆን ካማራት ድንግልናዋን ታጣለች፡፡ ድንግል ማርያም ግን ሁለቱንም ዕድሎች እግዚአብሔር አሟልቶ ሰጥቷታል፡፡ እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ ይዛለች፡፡ እናትም ድንግልም ናት፡፡ የወለደችውም በድንግልና ነውና፡፡ ከወለደችም በኋላ ድንግል ናት፡፡

ቅዱስ ጄሮም ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 44 ሲተረጉምቅድስት ማርያም ሕዝቅኤል ያያት የምስራቅ ደጅ ናት፡፡ የአብ አንድያ ልጅ ሳይከፈት ወደ እርሷ ገባ፡፡ ሳይከፍትም ወጣ፡፡ እናትም ድንግልም ናት፡፡ “St. Mary could be a mother and a virigin at the same time” ብሏል፡፡ (Epist. 48:21) አባ ሕርያቆስም አባ ኤፍሬምም ተባብረውየተዘጋች የሕዝቅኤል ምስራቅ፤ የምስራቅ ደጅብለው አመሰግነዋታል፡፡ (ቅዳሴ ማርያም . 36 ገፅ 169) (ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ)፡፡

3. የትሕትና ሕይወት፡- ድንግል ማርያም ከልዕልናው አገዛዝ ሥራ በትህትና የታዘዘች እመቤት ናት፡፡ ራሷየባሪያውን ትህትና ተመልክቶአልናበማለት መስክራለች፡፡ በሰው ፊት ትሁታን የሚመስሉ ልብን በሚያየው አምላክ ፊት ደግሞ ኩራተኛ ልብ ያላቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ድንግል የነበራት የእግዚአብሔርን ዓይን የሳበ የልብ ትህትና ነው፡፡ የመልአኩ የሚያስደንቅ ሰላምታ አስገረማት እንጂ አላስታበያትም፡፡ እመቤታችን ማርያም ሁሉን ሰጥቷት ሳለ ትሁት ልጇ ጌታ ኢየሱስ ሁሉ እያለው ትሁት እኛ ባለን ጥቂት ነገር የምንታበይ ከየት በቅለን ነው?
4. የምስጋና ሕይወት፡- ድንግል ማርያም ልጇንጌታዬ የነፍሴ መድኃኒትብላ አመስግነዋለች፡፡ ሉቃ. 147-55፡፡ ይህ ምስጋናዋ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ክንዱን ያሳየባቸውን ታላላቅ ተአምራት የዳሰሰ ነው፡፡ በዘመናችንም እግዚአብሔር የብዙዎቻችንን ታሪክ ውብ አድርጎ ሠርቷል፡፡ ነገር ግን እንደ ጆተኒ ውጠን ዝም ብለናል፡፡ ከድንግል ማርያም የምንማረው ተቀብሎ ዝም አለማለትን፤ ማመስገንን ነው፡፡ ዋስ ሆኖ ተይዞልን ቤዛ ሆኖ አድኖን ሞቶ ሕይወት ሰጥቶን እንኳ ገና የምስጋና እዳችንን አልከፈልንም፡፡ የድንግል ማርያም የከንፈሯ ዝማሬ፤ የነፍሷ ከፍታ፤ የመንፈሷ እረፍት ልጇ ኢየሱስ ነበረ፡፡ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፡፡ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሀሴት ታደርጋለች” (ሉቃ. 147)፡፡
5. የቅድስና ሕይወት፡- ድንግል ማርያም ክብርት፤ ልዕልት፣ ውድስት፣ ንጽሕት፣ ብፅዕት፣ ቅድስት ናት፡፡ ክብሯንና መባረኳን ቀድሞ የሰበከው ሰማያዊ መልአክ ነው፡፡ ምድራውያንን ወክላ በመንፈስ ቅዱስም ተሞልታ ቅዱስ ኤልሳቤጥ መስክራለች፡፡ ብፅዕናዋን የዳነው ትውልድ እንደሚመሰክር የተነበየችው ድንግል ራሷ ናት፡፡ (ሉቃ. 128-49)፡፡

ድንግል ማርያም ከዓለማውያን ማታለልና ከሥጋ መሻት ርቃ በመቅደስ ያደገች እናት ናት፡፡ ብሉያቱ ሲተረጎሙ ለእግዚአብሔር የታመኑ ታላላቅ ሰዎችን ታሪክ ሰምታለች፡፡ ለታላቁ ለእግዚአብሔርም በመታመን ኖራለች፡፡

እመቤታችን ማርያም አዲሲቱ (ዳግሚት) ሔዋን ናት፡፡ የመጀመሪያዋ ሄዋን ውዳሴ ከንቱ ሰምታ ስትሳሳት ዳግማዊት ሔዋን ድንግል ግን እውነተኛውን ውዳሴ ከእውነተኛው መልአክ ሰምታ አልተንበረከከችም፤ የተሸነፈችው በእምነት ነውና፡፡ የመልአኩን ቃል አሜን ብላ የተቀበለችው የእግዚአብሔርን መቻልና ማስቻል ሲሰብክላት ነው፡፡የመጀመሪያዋ ሄዋን የሞት ዜና ሰማች፤ ዳግማዊት ሄዋን የመዳናችንን ዜና ሰማች፡፡ የመጀመሪያዋ ሄዋን ልጅ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ የዳግማዊት ሄዋን ልጅ አዳኝ ነው፡፡ የመጀመሪያዋ ሄዋን ልጅ ወንድሙን ገደለ፡፡ የአዲሲቱ ሔዋን ልጅ ስለወንድሞቹ በሥጋ ሞተ፡፡ቅዱስ ኤፍሬም፡፡

ድንግል ማርያም የአዲሱ ትውልድ እናት ናት፡፡ ሄዋን የፍጥረታዊው ሰው እናት ናት፡፡ ድንግል ማርያም በልጇ የዳነው ትውልድ እናት ናት፡፡ድንግል ማርያም የማራኪ ክርስቲያናዊ ሕይወት ምሳሌ ናት፡፡ በእምነትዋ፣ በትህትናዋ፣ በቅድስናዋና በምስጋናዋ እንምሰላት፡፡ ስሟን በምስጋና ማንሣት ብቻ ሳይሆን ሕይወቷንም ለአርአያነት ማየት ይጠበቅብናል፡፡ ሕይወቷ ይኑረን፣ ፍቅሯ ይብዛልን፡፡
የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡


No comments:

Post a Comment