ክስ ሳይመሰረትበት ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ግፍ እየተፈጸመበት እንደሆነ ታወቀ። ሃብታሙ አያሌው ለአንድ ሳምንት ወደ መጸዳጃ ቤት እንድዳይሄድ በመከልከሉ በፌስትታል ይጠቀም እንደነበረ፣ ለሶስት ሳምንታትም ቁጥር ስምንት በምትባል የጨለማ ቤት ዉስጥ ለብቻው እንዲቀመጥ መደረጉንም አረጋግጠናል።
ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ዋና ኦዲተር፣ አባካኝ የመንግስት ተቋማት በሚል ለጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት እና ለተወካዮች ም/ክር ቤት አፈ ጉባኤ ያቀረበው ሪፖርት ለህዝብ ይፋ ይሁን አይሁን የሚለው ጉዳይ ሚኒስትሮችን አወዛግቧል።
ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለቤታቸውን በድንገተኛ ሞት ከማጣታቸው በፊት የፓርላማ አባል የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በራሳቸው ፍቃድ ፓርላማውን ከመልቀቃቸውም በተጨማሪ በድርጅታዊ ስራዎች ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እየተዳከመ መምጣቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የፖለቲካ ስልጠና መድረክ ከወረዳ ጽ/ቤት እስከ ማዕከል ቢሮዎች የሚገኙ ሰራተኞች እና የፌደራል መ/ቤት ሰራተኞች ከማክሰኞ ጥቅምት 3 ቀን እስከ ቅዳሜ ጥቅምት 14/2007 ዓ.ም ለተከታታይ 11 ቀን የፖለቲካ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፣ በዚህ መድረክ እስካሁን ከታዩት በላይ በሰልጣኖችና በኢህአዴግ አመራሮች መካከል ፍጥጫ ታይቷል። ጠንካራ ጥያቄ በማቅረብ ሰልጣኙን አነሳስቷል የተባለ አንድ ሰልጣኝ ከስራው እንዲባረር መደረጉን ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የፌደራል ፖሊሶችን ልዩ ሃይልንና መከላከያን ባቀፈው የመንግስት ጦርና፣ መሳሪያ በታጠቁ የብሄረሰቡ ተወላጆች መካከል በተደረገው ውጊያ ከ40 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላትና