.png)
በፌደራል ፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉን አደራጅታችኋል የተባሉ በርከት ያሉ ተማሪዎች መታሰራቸውንም ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ስልጠናው አርብ መስከረም 30/2007 ዓ.ም የጨረሱት ተማሪዎች መጀመሪያ ላይ እንደሚከፈላቸው ቃል ተገብቶላቸው የነበረው የውሎ አበል አይከፈላችሁም በመባላቸው በትናንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ተማሪዎቹ አበሉ አይከፈላችሁም ቢባሉም አሰልጣኞቻቸው
‹‹ገንዘቡ መጥቷል፡፡ አንከፍልም የሚሉት ዝም ብለው ነው›› ማለታቸው ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ገፋፍቷቸዋል ተብሏል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ሴት ተማሪዎች ከግቢው እንዳይወጡ የከለከለ ሲሆን ወንድ ተማሪዎች ከግቢው እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ መደብደባቸውንና
መታሰራቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የአዋሳ ፖሊስ አዛዦችን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
No comments:
Post a Comment