BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 23 December 2014

"ትንሽ እርሾ ብዙውን ሊጥ ታቦካለች "

ለአገር ትንሣኤ እርሾ ለመሆን የተደረገውን ሙከራ በአሞተቢስ አፈግፋጊዎች ፍራትና ሽሽት አፈር ለበሰ የሚል ትዝብት አስነስቷል።
ለአገር ተቆርቋሪ ፣ አሳቢና ሰላማዊ በመምስል ወደ ትግሉ ጎራ በመቅረብ ትግልን ለማክሸፍ ሽፍጥና ሽሽት ማካሄድ፣ በአገርና በሕዝብ ሕልውና ላይ መነሳሳት፣ ትልቅ ክህደት ከመሆን ጋር የአገር ነፃነት ትግልን ለራስ ጥቅም ማስቀደም ከጠላት ያላነሰ አገር የማጥፋትና የመሸጥ ወንጀል የባንዳዎች ሴራ ሽረባ ነው።

ኢትዮጵያና ሕዝቧን መድፈር፣ ታሪክና ትውልድን መናቅና መፈታተን ነው። ይህ ይቅር የማይባል ሽፍጥና ተንኮ፣ ታሪክና ትውልድ አክባሪውን ሁሉ በእጅጉ አስቆጥቷል። ሰለሆነም ለኢትዮጵያና ለሕዝብ ነፃነት የቆሙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ሁሉ ይህን በአንክሮ ተመልክቶት እንደ ቀደምት ትውልዶቻችን ታሪካዊ ጀብዱን በቁርጠኝነትና በፅናት በብሔራዊ ቃል ኪዳን መታገልና ሁሉንም ጠላት በየአቅጣጫውና በየፈርጁ በማንበርከክ ደምሰሶ የኢትዮጵያን ትንሳኤ የሚያበስርበት የድል ቀን ቅርብ ይሆናል።
ልብ ያለው ልብ ያድርገው
ትውልድ አክባሪ ለድል ተቃርቧል! !
በጀግና ልጆችዋ ኢትዮጵያ ምንጊዜም ትኖራለች ! !
ታህሳስ 2/2007 ከበላይ መታፈሪያ ዶ/ር

No comments:

Post a Comment