.png)
እንደምንጮች ገለጻ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉት ድርጅቶች ውስጥ አንዳንዶችን በማካተት፣ በውጭ ከሚገኙ ገዢውን መንግስት በሃይል እናንበረክካለን ከሚሉ ወገኖች ጋር ለማቀራረብ አሜሪካውያን የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን እያነጋገሩ ሲሆን፣ ኖርዌይ ውይይቱን ለማዘጋጀት እየተንቀሳቀሰች ነው።
ኢህአዴግ በድርድሩ ላይ ለመገኘት ፈቃደኝነቱን መግለጹ የተነገረ ሲሆን፣ በተቃዋሚዎች በኩል ግን አንዳንዶች ለውይይት ለመቀመጥ ፈቃደኝነታቸውን ሲገለጹ ሌሎች ግን እያንገራገሩ ነው።
ምርጫውን ተከትሎ ህዝባዊ አመጽ ቢነሳ ኢህአዴግ ሊወድቅ ይቻላል የሚል ስጋት የገባቸው ምእራባውያን፣ ምናልባትም ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎች የተወሰኑ መቀመጫዎችን በመልቀቅ ውጥረቱ እንዲበርድ ሊያደርግ ይችላል የሚል እምነት ይዘዋል።
የአውሮፓ ህብረት ከሁለት ምርጫዎች በሁዋላ የኢትዮጵያን ምርጫ እንደማይታዘብ ባስታወቀ ማግስት የተጀመረው የአሜሪካ እና የኖርዌይ ጥረት ይሳካ አይሳካ ለወደፊቱ የሚታይ ነው። በጉዳዩ ዙሪያ የኖረዌይና የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቶችን ለማናገር የተደረገው ጥረት አልተሳካም።
No comments:
Post a Comment