BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Thursday, 15 September 2016

ግፍ አመጽን ይወልዳል፤ የጸናም ጎሕን ያያል!!!

 ቅጽ 42 ቁጥር 9                                                                                         ሐምሌ/ነሐሴ 2008 ዓ.ም
                                                                                                        
ነሐሴ 26/ 1967 ዓ.ም የሀገራችን የመጀመሪያው ዘመናዊ ፓርቲ/ድርጅት የሆነው ኢሕአፓ፤ ለሦስት ዓመት በህቡዕ ድርጅታዊ ሥራ ሲሠራ ቆይቶ ራሱን በሚያስደንቅ ሁኔታ ይፋ አደረገ። መርሃ ግብሩን/ፕሮግራሙን በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች (በእንግሊዝኛ ጭምር) በአንድ ቀን በመላ ሀገሪቷ ሲያሰራጭ አንድም አባል አልተያዘም ነበር። ያ ቀን የጭቁኖች ፈንጠዝያ ቀን ተብሎ ቢወራ ኋላ እንዳየነው ማጋነን አልነበረም። ኢሕአፓ ዛሬም በትግል ላይ ነው። ነሐሴ 2008 ደግሞ ጭቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በስፋትና በጥልቀት በወያኔ ላይ አምጾ ተነስቶ ወሳኝ ፍልሚያ እያካሄደ የወያኔን የቀብር ደወል በማጮህ ላይ ይገኛል። በአካባቢ የተወሰኑና መለስተኛ ጥያቄዎች እየተካሄደ ላለው ሕዝብ አመጽ አቀጣጣይ ክብሪት የነበሩ ቢሆንም ዋናው መሰረታዊ ምክንያት ግን ኢሕአፓ ለትግል ሲነሳ አንግቦ የታገለላቸው ቋሚ የሆኑት የሕዝብ መብትና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸው ነው።
መብታችን ይከበር፤ ዘረኝነት ይወገድ፤ መሬት ለአራሹ፤ ፍትሃዊ አስተዳደር ይምጣ፤ እኩልነት ይስፈን፤ የንጹሃንን ደም ማፍሰስ ይቁም፤ የሀገር ሉዓላዊነት ይረጋገጥ፤ . . .ወዘተ የሚሉት የዛሬ መሠረታዊና አታጋይ መፈክሮች፤ በዛም አነሰም በ1966 በኢሕአፓ ታጅበው የቀረቡ ናቸው። በጊዜ ሂደት የተጨባጩ ሁኔታ መልክ ቀየር ማለቱ የሚጠበቅ ቢሆንም፤ አንዱ ጨቋኝ ከሌላው ለወጥ ሊል ቢችልም፤ የኅብረተሰቡ ዋና ችግሮችና ጥያቄዎች ምላሽ እስካላገኙ ድረስ ዳግምና በቀጣይ ደረጃ የሚቀርቡ ይሆናሉ። የሀገራችን ችግሮች፤ ትውልድና ዘመን ተሻጋሪዎች ቢሆኑም በሕዝባዊ አመጽ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት እየተደረገ ነው። የየካቲቱ ትውልድ ከአርበኞች ማኅደር ብዙ ትምህርት ቀስሟል። ከዚያ ቆራጥ ትውልድ ጸረ-ፋሺስት ትግልም የአሁኑ ትውልድ ብዙ የሚማር ሊሆን ይችላል። የሰማዕታትን ታሪክ ለማርከስ ብዙ የደከሙ ቢኖሩም ዛሬ የኢትዮጵያ ወጣቶች በእነዚያ ሰማዕታት ፈለግ ወያኔን ለማስጨነቅ መቻላቸው የተባለውን እርኩስ ጥረት ውድቅ አድርጓል። በየካቲት 66ም ቢሆን፤ ወጣቱ ወዲያውኑ ወደ ድርጅታዊ ትግል አልመጣም ነበር። ተሳትፎው እየጨመረ የመጣው በትግሉ ውስጥ እና ከዘመቻው ጋር መሆኑ ይታወሳል። ላባዳሮች እና ሌሎች ጭቁን ዜጎችም እንዲሁ። ጸንቶ የሚታገልና የሚያታግል፤ ተስፋ የማይቆርጥ ድርጅት በመኖሩ ግን ሰፊው ሕዝብ ወደ ተደራጀ ትግል ሊሳብ ችሏል። 25 ዓመት ረጅም ጊዜ ነው። "ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል" ቢባልም፤ መሸፈቱ፤ በወተት ፍላት ፍጥነት የሚሆን አይደለም። በተለይም የሕዝብ ድርጅቶች ተጠቅተው ሚናችውን ሊወጡ ከማይችሉበት ደረጃ ላይ ከሆኑ! በየካቲቱ 66 ትግል፤ ከተሞች በተለይም አዲስ አበባ ደምቆና ግንባር ቀደም ሆኖ ሲገኝ፤ በፀረ ወያኔው ዙር፤ ከመሃል ካለው ይልቅ፤ አመጹ የተቀጣጠለው በሌሎች ከተሞች ሆኗል። አምቦ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ደብረ ታቦር፣ ማጀቴ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ዴሞ ቅጽ 42 ቁ 9 ሐምሌ/ ነሐሴ 2008 ዓ.ም 2 ቡሬ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔና ሌሎችም ከተሞች የአመጽና የአድማ ማዕከሎች ሆነው ቆይተዋል። አመጹና አድማው እየተስፋፋ ነውና ደምዳሚ ግምገማ ወይም ሙሉ ዘገባ የማድረጊያው ጊዜ ገና ነው። ዛሬም እየታየ እንዳለው ስር ነቀል ለውጥ የቶሎ ቶሎ ጉዳይ አይደለምና (ለምሳሌ የካቲት 66 ወራትን ወስዷል ) ይህ ከባድ ተልዕኮ ትዕግስትንና ጽናትን ይጠይቃል። ወያኔ 25 ዓመት በሥልጣን ሊቆይ የቻለባቸውን ተጨባጭ ሁኔታዎች በተገቢው ጥልቀት መመርመርም ግድ ይላል። ወያኔ ሥልጣን ላይ ሊቆይ የቻለው ጭካኔ የተሞላበት ተግባር በመፈጸምና ሕዝብን ከፋፍሎ ለማዳካም በመቻሉ መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው። ወደ ሥልጣን የተጓዘው ጥላቻን መሠረት አድርጎ መሆኑ የታወቀ ሲሆን በባዕዳን እርዳታና ትብብር ሥልጣን በያዘበት ወቅት ሰፊና ሀብታም ሀገር የሆነችውን ኢትዮጵያን መጋጥና መበዝበዝ የተሻለ መሆኑ ሊገነዝብ ቢችልም የተመሠረተበት የጠባብነት ዓላማና ግብ ተዋህዶት ስለነበር ትግራይን ለብቻ አሊያም ትግራይ ትግሪኚ በሚል ከሻዕቢያ ጋር ሊያቆራኝ ወስኖ የጎንደር፣ የወሎና የአፋርን ለም መሬቶችን በመዝረፍ በትግራይ ክልል ውስጥ የማጠቃለል እርምጃ ወሰደ። ይህ ዓይን ያወጣ የሕዝብን መብትና ጥቅም የተጻረረ ወንጀል ምን ጊዜም ከማይወጣበት ቀውስ ዳርጎት ይገኛል። ወያኔ ኃይሉን በመጠቀም የሕዝብን ትግል ለማፈን የቻለው የፋሺስቱ ደርግ--ኢሠፓ ሥርዓት ጥቃት ስላዳከመው መሆኑ ግልጽ ነው። ሰው በላው አገዛዝ ታጋይ ሀገር ወዳዶችን በሽብር ጨፍጭፎ፤ ተመክሮ ያላቸውን የሀገሪቱን መኮንኖችና ጀኔራሎች ገድሎ፤ የአገሪቱንም ሉዓላዊነት ለሚክደው የባዕድ ኃይል አስረክቦ፤ ብዙ ግፍ ፈጽሞ ሕዝብን በድሎና አሰቃይቶ ጥሎ ፈርጥጧል። በርካታ የዚህ ሥርዓት ኮለኔሎችና ባለሥስልጣናት ዛሬ ከወያኔ ጋር አብረው መቆማቸው የሚያስገርምም አይደለም። በየወሳኝ ወቅቱ የት ደርሰናል ? ብለን ስንጠይቅ፤ ያለፈውን ገምግመን፤ የዛሬውን አጢነን፤ ለነገው እንድንዘጋጅ ነው - "ታሪኩን የረሳ ስህተቱን ይደግማል" ተብሎ የለ ! 25 ዓመታት የሰፈረብን ድባብ፤ የቀቢጸ ተስፋ ጭጋግና ዘረኛ የክፍፍል መቅሰፍት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ (እየተቀፈፈና) እየተቀረፈ መውደቅ ጀምሯል። ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ወጣት ኦሮሞዎችና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ፍርሃትን አፈር አብልተው በመነሳት፤ ወያኔን ፤ በጎንደርና ጎጃም ገጥመው እያርበደበዱ ያሉት አኩሪ ዜጎች የወያኔን አሰቃቂ አገዛዝ የመጨረሻ ምዕራፍ በደማቸው እየጻፉ ነው። እንደ እርካሽ ዕቃ ተክቸልችላና ተጥላ የነበረችው ኢትዮጵያዊነት በሀቀኛ ሰንደቋ ታጅባና አሸብርቃ ወያኔን ስትጋፈጠው አዲስ ታሪክ መጻፏን ጀመረች። የወያኔ በሥልጣን መቆናጠጥ--በባዕዳን ተደግፎ ማለቱን ሳንዘነጋ--በኢትዮጵያ ላይ ያመጣው የውድቀት አደጋ ፤ ሕዝብን በመከፋፈል ላይ ተመስርቶ ያቆመው ዘረኛ ሥስርዓት የትግራይን ሕዝብ ከሌላው ለዘላቂው ሊያጋጭ አልሞ እንደነበር የሚታወቅም ነው። ሕዝብን አዳክሞ ያስረከበው ደርግ-ኢሠፓ ቢሆንም፤ ለወያኔ የባዕዳን ድጋፍ--በተለይ የሱዳን፣ የሊቢያ፣ የአሜሪካ አለሁ ባይነት ጠቅሞታል። ሀገር ወዳድ ዜጎች ደካማ ስለነበሩና፤ የቀሩት ደግሞ ለባለነፍጡ ለወያኔ መስገዱን ስለመረጡ ፤ ያን ጊዜ የተቃወሙት ተማሪዎችም ሆኑ ለዓመታት የታግለው ኢሕአፓ አጋር አጥተው የህይወት ዋጋ በአያሌው ከፈሉ። ሰሚ ጠፍቶ እንጂ ወያኔ ፀረ ኢትዮጵያ መሆኑ ሲነገር የቆየ ነው። ወያኔ በ1967 መርሃ ግብሩ (ማኒፌስቶው) መገንጠልን እንደ ዋና አማራጭ ከማቅረቡ ባሻገር፤ በዚያው ቀጥሎ ታላቋ ትግራይ በሚል የጎንደርን የወሎንና የአፋርን መሬቶች፤ ትግራይ ብሎ አጠቃሎ ካርታ ስሎ አቅርቦም እንደነበር የማይካድ ሐቅ ሲሆን ይህንን በቅድሚያ የተቃወመው ግን ኢሕአፓ እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል። የየካቲት 66 ታሪካዊ አንደምታ፤ በርካታ የሕብረተሰቡ ክፍሎች በጋራ ተነስተው መታገላቸው ሲሆን ፤ ዛሬም ወያኔ ቀውስ ውስጥ የገባው በተመሳሳይ መንገድ፤ በከፍተኛ ደረጃ፤ የገጠር ከተሞችን ማዕከል አድርጎ ሕዝብ በቃኝ አሻፈረኝ፤ ወያኔ ይወገድ ብሎ ደሙን ሊያፈስ ቆርጦ በመነሳቱ ነው። ፍርሃትና ግለኝነት ከሞላ ጎደል ተወግደው፤ ለሀገር ደም ማፍሰስ ዴሞ ቅጽ 42 ቁ 9 ሐምሌ/ ነሐሴ 2008 ዓ.ም 3 አኩሪ ሆኖ ሲታይ፤ የወያኔ የውድቀት ደወል ተደወለ ማለት ይቻላል። ባሁኑ ወቅት ደግሞ ፍርሃት ተወግዶ፤ ኢትዮጵያዊነትና አንድነት የበላይነትን ይዞ፤ ወያኔ ሲሽመደመድ በተጨባጭ እየታየም ነው። ቅራኔውና መሠረታዊ ትግሉ፣ በወያኔነትና በኢትዮጵያዊነት መካከል መሆኑን ከምንጊዜውም በላይ በግልፅ እያሳየ የመጣበት ሁናቴ መሆኑን እያንፀባረቀ ነው። ጎጃም ጎንደር ስንል ይህንኑ መሠረት በማድረግ መሆኑ ግልጽ ነው። አረመኔውን የታጠቀን ዘረኛ ቡድን እየተፋለመ ያለው ሕዝብ የወያኔ ቀፎነትን አጋልጧል። የሚኩራራበት ኃይሉም የሽሮ ድንፋታ መሆኑን ተገንዝቧል። ኃይል የሕዝብ መሆኑም በማያወላውል መንገድ ተረጋግጦ ወያኔን ብርክ አስይዟል። የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘረኛ ቢላዋ ሲመትር የቆየው ወያኔ በተለይም ጠላቴ ነው ብሎ የፈረጀውን አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ያላደረገው የለም። ውሎ አድሮ ይህ መከራ በሊሎችም ላይ ተረጨና ብዙዎች ተጨፈጨፉ። አኝዋኩ፣ ኦሮሞው፣ ሶማሌው፣ የምሙ፣ ሱርማው፣ አፋሩ፣ ... ወዘተ በሞላ በወያኔ ግፍ ተፈጽሞበታል። ወያኔ በባዕዳን ድጋፍና በኃይሉ ቢመካም፤ እየዋለ እያደረ የራሱን የሥልጣን ዘመን፤ በሚያደርሰው ወንጀል ገዝግዞ ውድቀቱን አፋጥኖታል። በሕዝብ ላይ ያለው ንቀትና ወጥሮ የያዘው ዕብሪትም ወደ ማይቀርለት የመቃብር ጉድጓዱ እያመሩት ናቸው ። ተባባሪዎቹም አደጋ ተደቅኖባቸዋል። በውድቀቱ ሂደት ግን የጨዋውን የትግራይ ሕዝብ የነገ ዕጣ ሊያበላሽና ታሪኩንም ሊያቆሽሽ ይችላል የሚል ስጋት አለ። ወያኔ ወደ ውድቀቱ እያመራ ቢሆንም የኢትዮጵያን ሕዝብ ድል በመንገዱ ላይ የሚያደናቅፈው አይኖርም ብሎ መደምደም ስህተት ይሆናል። ታሪክ ያሳወቀን ሐቅ ቢኖር ሕዝብ ወደ ድል ሲገሰግስ ጠላቶቹ በጋራም በተናጠልም ጋሬጣ ጥለው ወደ ግቡ እንዳይደርስ ለማገድ ሲጥሩ ነው። አሁንም ተነስተዋል። በቅድሚያ መገንዘብና ማተኮር ያለብን ግን ጠላቶቻችን ሊያደርሱብን የሚፈልጉትን ጉዳት ሳይሆን፤ራሳችንን እንደ ሕዝብ፤ እንደ ኢትዮጵያዊነት፤ እንዴት ጸረ ወያኔ ትግሉን እናጠናክራለን የሚለው ነው። ራሱንም ያወቀ ፤ ጠላቱንም ያወቀ፤ አንድ ሺ ጦርነት ቢገጥም ሁሉንም ያሽንፋል የተባለውን ያስታውሷል ነውና፤ ይህ የተጀመረው ታሪካዊ ተጋድሎ ወያኔን በማስወገድ እንዲደመደም ከተፈለገ መስፋትና መጠናከር አለበት። ከአዲስ አበባ እስከ ሞያሌ፣ ከጅማ እስከ ሐረር፣ ከአፋር ምድር እስከ ወለጋ ትግሉ መፋፋም አለበት። በጎንደርና በባህር ዳር፤ በአምቦና በለቀምት፣ በሻሸመኔ በሀረሚያ ...ወዘተ የሚኖረው ሕዝብ በተናጠል እንዳይጠቃ ማድረግ የሚቻለው ምልዓተ ሕዝቡ የሚያካሄደው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወያኔን ሊያሽመደምደው ሲችል ብቻ ነው። በጎጃምና በወለጋ፤ በሀረርና ...በተናጠል እንዳይጠቃ ከተደረገ፤ በዚህ ወያኔ እየደረሰበት ያለው ጉዳት የሚያሽመደምደው መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም። የትግሉን ቀጣይነት ማረጋገጥ የሚቻለውም በዚሁ ብቻ ነው። ይህን ስንልም አለምክንያት አይደለም። ሙስሊም ወገኖቻችንን በተገቢው መንገድ የደገፋቸው ባለመኖሩ በተናጠል መጠቃታቸውን ማስታወስ ይገባል። ቀጣይነት፤ ኅብረት መደጋገፍ፤ ለወያኔ ጥቃት አለመበገር ትግሉን በድል ለመደምደም ወሳኝነት ይኖረዋል። ጎንደር -ጎጃም የጸረ-ደርግ የትግል አውድማ ሆነው ይህ ነው የማይባል ድርጅታዊ ተመክሮን ያካበቱ አካባቢዎች ናቸው። አማራው፣ አገዉ-ሺናሻው፣ ጉምዙ በድርጅት ዙሪያ ተሰልፎ አረመኔውን ደርግ ያስጨነቀ ነው። አሁንም የተለየ አይሆንም ብንል ስህተት አይደለም። የየካቲቱ " የይቻላል መንፈስ" ፤ ደብዝዞ ቢቆይም ዛሬ ዳግም አለሁ ብሎ ታይቶ እንደነበረው ብቅ ብሏል። ሰልፍ፣ ሙት ከተማ፣ ተኩስ፣ አድማ የዚያ ትውልድ መንገዶችና ቅርሶች ናቸው። ሕዝብ፣ ባለ ድል ለመሆን፤ ትግሉን ማስቀማት ዴሞ ቅጽ 42 ቁ 9 ሐምሌ/ ነሐሴ 2008 ዓ.ም 4 የለበትም። ከሞኝ ደጃፍ የተባለው ሊደገምብን የሚችል 1997 መሆን የለበትም ። " የነብርን ጭራ ከያዙ አይለቁ " የተባለውንም ይትብሃል፤ የጎንደር ጎጃም ሕዝብ አውቆታል። ወያኔ እንኳን የሚመሳሰለው ከእርያ ጋር ቢሆንም ! ሕዝባችን በተግባርም፤ ወያኔን በትግል አልለቅ ብሎ እያራወጠው ይገኛል። በቅድሚያ ራስን ማወቅ በተባለው መሠረት ፤ ታጋዩ ሕዝብ ከጎራህ ነን እያሉ ትግሉን ሊያኮላሹ ከሚችሉ አፍራሽ ኃይሎች ራሱን መጠበቅ አለበት። እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ ትግል ልዩ የሚያደርገው፤ አንደምታው ጎጥን ሳይሆን፤ ሀገርን በማስቀደሙና ኢትዮጵያዊነትን በማንጸባረቁ ነው። በጎንደርና በጎጃም ተቃውሞ ያሰማው አማራ የኦሮሞው የሙስሊሙ እና የሌላው ደም የእኛው ነው ሲል ፤ በአዳማና በሌሎች ቦታዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ያደረጉት ኦሮሞዎች ደግሞ የጎጃምና የጎንደር ደም የኛም ደም ነው ብለው የወያኔንና የሌሎችን ጎጠኞች ግድግዳ አፍርሰውታል። የሕዝቡ መፈክር ኢትዮጵያዊነት ነውና ለመነሻ የአካባቢ በደሎችን መሠረት ቢያደርግም ፈንድቶ የወጣውና ይኸው መሥዋዕት እየከፈለ የቀጠለውም ኢትዮጵያዊና ሕዝባዊ የሆኑ ብሔራዊ ጥያቄዎችን እያስተጋባ ነው። ይህንን ቀልብሰውና ወያኔም በሚፈልገው መልክ ወደ ጎጥ ክልል ለማውረድ የተነሱ እንዳሉም ምስጢር አይደለም። የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እያስተላለፉ ያሉትን መልዕክት ማዳመጡ ብቻ በቂ ነው። በሕዝብ ትግል ለመነገድ የተነሱ የለመደባቸው ጭልፊቶችም ብቅ ብቅ ሲሉ ታይተዋል። ወያኔ በሥልጣን ሊቆይ የቻለው በባዕዳን ድጋፍ መሆኑም ይታወቃል። ባዕዳኑ፣ እየተቀጣጠለ በመሄድ ላይ ባለው ሕዝባዊ ትግል ብርክ ይዟቸዋል። እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ አመፅ የተከፋፈለ የጎጥ ትግል ሳይሆን፤ ኢትዮጵያዊ ፍንዳታ መሆኑን ቢረዱትም ወያኔ፤ ያዘዙትን ተቀባይ፤ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አሳልፎ ሰጪ፤ ጃስ ሲሉት የሚናከስላቸው ውሻ፤ የሀገርን ለም መሬት አሳልፎ የሰጣቸው ከሃዲ ቡድን በመሆኑ እንዲወገድ አይፈልጉም። ወያኔ ከወደቀ የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካችንና ጥቅማችን ሁሉ ይነካል በሚል ሰግተዋል። ስለዚህም ነፍስ አድን ዘመቻቸውን ጀምረው በመራወጥ ላይ ናቸው። ወያኔ እንዳበቃለትና ፍርክስክሱም እየወጣ እንደሆነ ተረድተዋል። ለውጥ የተደረገ በማስመሰል የበላይነታችንን ሊጠበቅ የሚችል ሂደት እንፍጠር በሚሉት ብልጣ ብልጥ ወያኔዎችና በነበረው ሊቀጥሉ በሚፈልጉ፤ የወልቃይት ጉዳይ በትግራይ ክልል ይወሰን ብለው በሚያላግጡት ዘረኞች መሃል ልዩነቱ ጦፏል። በዚህ በዚያም ግን ይህ የወያኔ አገዛዝ እንዲቆይ የሚፈልጉ ቡድኖች የትግሉ ወዳጅ መስለው መርዛቸውን ሊረጩና ትግሉን ለማዳከምና ለማስቆም እየጣሩ መሆናችው ይታያል። አሜሪካ ለዚሁ ስምሪት ብዙ ሚሊዮን ዶላር መድባ ቅጥረኞቿን በርቱ እያለች ነው። ሴራው ተጀምሯል። ቀድሞም ለጥፋት ያጋለጡን የውስጥም የውጭም ጸረ-ህዝቦችን መሰብሰብ ይዘዋል --ከእነ ሄርማን ኮኸን፤ ዴቪድ ሺን፤ የአሜሪካ የወታደርና የስለላ ተቋሞች ኃላፊዎች ጋር በስብሰባ ተቀምጠዋል - ሕዝባዊ ትግሉን ለማክሸፍ። ኦሮሞውን ከሌላው የሚነጥሉ ቅጥረኞች በርቱ ተብለዋል። ኢትዮጵያዊውን ትግል የሚሸረሽሩና የሚከፋፍሉትም ተሰማርተዋል። በ1983 ዓ.ም እንዳየነው ወያኔን በአስመሳይ አዲስ ሽግግር የሚያጅቡ ምልምሎች እየተዘጋጁ ነው። በዚህ ላይ ደግሞ የሻዕቢያም ሚና ሆነ በግልጽ የሚታየው መደናገጥ በግምት መግባት ያለበት ነው። ባዕድ የተባለ ሁሉ ማንም ሆነ ማን በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ከወያኔ ነጻ ሆና የሕዝብን መብት የሚጠብቅ የመንግሥት ሥርዓት እንዲኖራት አይፈልጉም ። ይህን በመገንዘብ የይስሙላ ለውጥ በሚል ማደናገሪያ ወያኔን ከውድቀት ለማዳን የሚጥሩትን ባዕዳን ሆኑ ከሀዲ ዜጎችን ጥግ ማስያዝ ተገቢ ነው። ለባዕድ አድረው ደርግ-ኢሠፓን ከጥቅም ውጭ ያደረጉ ኮለኔሎችና ሻለቆች ዛሬም የሕዝብን ትግል ለቀጣሪያቸው አሳልፈው ሰጥተው ትግሉን ሊያኮላሹ እየጣሩ መሆኑ መታወቅ አለበት። መታለል ከለመደውና ወያኔ ዴሞ ቅጽ 42 ቁ 9 ሐምሌ/ ነሐሴ 2008 ዓ.ም 5 ዲያስፖራ ከሚለው ውጭ ሀገር ነዋሪ ከሆነው ክፍል ኪስ አውላቂ ሆነው የሚዘርፉት ጠንከር ብለው መሰማራታቸውም እየታየ ነው። ይህንን ጥረት ማክሸፍ የሕዝብ ትግል አንዱ ግዳጅ ነው። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ውድ ህይወቱን ለአግዓዚ ደፍሮ የሚሰጠውና ዋጋ የሚከፍለው ወያኔን በወያኔ ለመተካት ወይም ወያኔን በሌላ የባዕዳን ተቀጣሪ ስብስብ ለመለወጥ አይደለም። የሕዝብ ፍላጎት ወያኔን ከነግሳንግሱ አስወግዶ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግና በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አንድነትንና ሉዓላዊነትን ለማረጋጋጥ ነው። ባዕዳን ደግሞ ወያኔን ለሥልጣን አብቅተው ሀገራችንን በአያሌው እንደጎዷት ሁሉ አሁንም ወያኔን ከሙሉ ጥፋት አድነው ለማስቀጠል አሊያም የእነሱ በሆኑ ታዛዦች ተክቶ የበላይነታቸውን አረጋግጠው ለማስኬድ ነው። ምዕራባውያን ሀገር ወዳድ መንግሥት አይወዱም--ታዛዣቸው የሚሆነውን እንጂ። ጥቅማቸውን የሚጠብቅ አገዛዝ ነፍሰ ገዳይ ቢሆንም ይደግፉታል - እነሱን እስከተከተለ ድረስ ማለት ነው። ይህ ፖለቲካቸውና ርኩስ አቋማቸው በአፍሪካ ፤ በተለይ ደግሞ፤ በኢትዮጵያም የታየ ነው። በአንድ ወቅት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ወያኔን በነጻ ምርጫ የተመረጠ ነው ብሎ ያወደሰው ሐቁን አጥቶት ሳይሆን ለእኛ ሎሌ እስከሆነ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቹን ቢገድል ግድ የለንም ከሚል ነው። ጥቅማቸውን ስለሚያስቀድሙ የኢትዮጵያን ጥቅም ክብር የሚሰጥ አገዛዝ አይፈልጉም። በመሆኑም ወያኔ ወድቆ በሀገር ወዳድ መንግሥት ወይም ሥርዓት እንዲተካ ከቶም ምኞታቸው አይደለም። የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁሉ ሀገራችን ደቃና ደክማ ከምትገኝበት አሳዛኝ ደረጃ ወጥታ እንድታንሰራራ አይመኙላትም። የሚበዘብዙን አረቦች፤ የሚዘርፉን ቻይናዎች፤ መሬታችንን የወሰዱት ሱዳኖች፤ የሚቀልዱብን ፈረንጆች ኢትዮጵያ የራሷ የምትኮራበትና የሚያኮራት መንግሥት እንዲኖራት ስለማይፈልጉና አልፎም የወያኔን ጸረ አማራነት የሚጋሩ በመሆናቸው የጎንደር ጎጃም ...ወዘተ የሕዝብ ትግል መርዶ ሆኖባቸዋል። ይኽም የሚጠበቅ ነው። በኦሮሞው አካባቢ የሚካሄደው ትግልም ራስ ምታት ሆኖባቸዋል። "ሽንኩርት የባሕሪውን ይሸታል " እንዲሉ ወያኔ ለይስሙላ ስብሰባ፣ ግምገማ ብሎ ምንም ላይፈይድ ገንዘብ አባክኖ የወልቃይትን ችግር የትግራይ ክልል ይፍታው ብሎ አላግጦ ተበትኗል። መጋዣውንም-ማለትም የአህያው ሞክሼ የሆነውን ወዲ ደሳለኝንም ተጠቅሞ በሕዝብ ላይ ሙሉ ጦርነትን አሳውጇል። በዚህም በዚያም ወያኔ ምንም ሊለወጥ የማይችል ቡድን መሆኑን እንደገና አረጋግጧል። ስብሓት ሄዶ ጻድቃን ቢመጣ፤ አባይ ተወግዶ በስዬ ቢተካ ወያኔ ያው የደደቢቱ ወያኔ ነው --ዘረኛ፤ ክሀዲ፤ ጸረ ሕዝብ ጸረ ኢትዮጵያ፤ የባዕዳን ባሪያ፤ የሙስና ፊታውራሪ፤ ሀገርን ሺያጭ። የሰማ ይስማ፤ ያልሰማ ይግማማ የሚሉት የጥንቶቹ በዚህ ሁኔታ ነው። ከአንዴም ሁለቴም ሦስቴም ህይወት ገብረን ድል ተነጥቀናልና ከእንግዲህስ በቃ ማለት የሚጠበቅብን ነው። የሕዝብ ትግል መሪና ተጠሪ ነን ብለው ትግሉን ለጠላት አሳልፈው የሰጡ ፤ የሕዝብን አድማ ያከሸፉ፤ የከዱ ተመልሰው የሕዝብ ትግል መሪና ተጠባባቂ ሊሆኑም መፈቀድ የለበትም። የጠላቶች እንዳለ ሆኖ፤ የውጮቹም ያው እንዳለ ሆኖ ደግመን ደጋግመን እያየን "የጎዳን የእኛው ጠማማ ነው " የሚለውን የዛፍ ቁጭት ማሰማትም የለብንም። ያረመኔ ልቡ ሁሌም ቀጋ ነውና ወያኔ ያልተፈጠረበትን ሰብዓዊነት ያሳያል ብሎ መጠበቅ ከንቱ ነው። ከራሳችንም ጠማሞች ቀና ነገር መመኘት እንዲሁ ፋይዳ ቢስ ነው። የጎጃም ጎንደርን፣... ወዘተ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ትግል ልዩና ተደናቂ ያደረጉት ሁኔታዎች ዳግም ላንደናገር፤ ዳግም ላንታለል፤ ዳግም ቡከኑን ከሀዲውን ጀግናና መሪ እንዳንል በተግባር አስጠንቅቆናል። ይህን ትግል ለምን ልዩና ታሪካዊ ቦታ ሰጠነው? ዴሞ ቅጽ 42 ቁ 9 ሐምሌ/ ነሐሴ 2008 ዓ.ም 6 ሀ/ በፊት ለታዩት ትግሎች ሁሉ ቀጣይ ሆኖ መገኘቱ--እስካሁንም አልቆመምና። ለ/ ወያኔ ገደልኩት ቀበርኩት ብሎ የነበረውን ኢትዮጵያዊነት አድሶና ታሪካዊውን ሠንደቅ ዓላማ በኢትዮጵያዊ መፈክሮች አጅቦ መነሳቱ፤ ሐ/ ወጣቱን ሽማግሌውን፣ ሴቱን ወንዱን አስተባብሮ መቀጠሉ፤ መ/ ሞት አይፈሬ ሆኖ የፍርሃትን መጋረጃ መጣሉ፤ ሰ/ ዘመናዊ የትግል ስልትን (ሰልፍ፣ ሙት ከተማ አድማ፣ ) ከብረት ትግል ጋር አያይዞ ሁለገብ ትግልና አመጽን ማስፈኑ፤ ረ/ ለወያኔ ግድያና ድንፋታ እጅ አለመስጠቱና የወያኔን መዋቅር ድክመት በማሳየቱና መለስተኛ ድሎችንም እየተቀዳጀ መምጣቱ ነው ማለት እንችላለን። ለሕዝብ ትግል ጆሮን መስጠት ማለት ሞቱን መቀበል ማለት መሆኑን ወያኔ ያውቀዋል። ትግራይን የመገንጠል ዕቅዱ አፈር እንደሚበላ ይረዳዋል። ስለዚህም ባለው አቅም ሁሉ ተሰማርቶ፤ ገንዘብ አፍሶና ቅጥረኞቹን አሰማርቶ ይህን ትግል ለማክሸፍ ጥረት ማድረጉ የሚጠበቅ ነው። ኃይል መጠቀም ገደብ አለውና ሁሌም በዚህ መንገድ ብቻ አሸንፋለሁ የሚል ቅዠት እንዳማይኖረው እናውቃለን። ስለሆነም በጣም የሚተማመንበት ዘዴ ሕዝብን መከፋፈል ነው። አማራውና ኦሮሞውን፤ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን እርስ በርሱ ማጋጨትና መከፋፈልን ዋና ስልት አድርጎ እየተጠቀመ ነው። ከሕዝብ ጎራ ነን እያሉ ግን በዚህ መስክ ተሰማርተው ሕዝብን የሚከፋፍሉትን ማበረታታቱን ቀጥሎበታል። ባዕዳን እንዲረዱት እየተማጸነ ነው። የሕዝብ ትግል ለድል እንዲበቃ አሁን እንደጀመረው መስፋት፤ መስፋፋት አለበት። ድል እስኪቀዳጅ ድረስ ቀጣይነት፤ ተከታታይነት ሊኖረው ይገባል። እስካሁን ከትግሉ አውድማ መገኘት ያልቻሉት የህብረተሰብ ክፍሎች አለን ማለት መቻል አለባቸው። ላባደሩ፣ ሰርቶ አደሩ፣ ... የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ወያኔን ማንገዳገድ ይጠበቅበታል። የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማክበር ያቃታቸው ባዕዳን የሕዝብን ቁጣ ልክ ሊገነዘቡ የሚችሉት ትግሉ ሲከርና ሲመር ነው። ኢትዮጵያዊነት፣ ትግል፣ ቀጣይነት፣ ለወያኔ አልበገር ባይነት ህያው ሆኖ መቀጠል መቻል አለበት። እውን እየሆነ የመጣው ትብብርና አንድነት ከተሸራረፈ ወያኔ ከውድቀት ሊያመልጥ እንደሚችል መገንዘብ አለብን ። የትግራይ ሕዝብ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር አብሮ ቆሞ ወያኔን መታገል ይጠበቅበታል። ይህ ካልሆነ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። የወያኔ ተቃዋሚ ኃይሎች ነን የሚሉት ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። የሀገር ወዳዱ ሕዝብ ደግሞ እየተሸረበ ያለውን ሴራ በግምት አስገብቶ የትግሉን ድል እንዳይነጠቅ መሟሟት አለበት - አምና ሞኝ ዘንድሮም ደገመኝ ይባል የለ ? ድል ቀርቧል። የወያኔ ውድቀት ደወል ተደውሏል። ሥርዓቱንም ለመቅበር ሕዝብ ቆርጦ ተነስቷል። ኢትዮጵያዊነትም ጠላቶቹን እያቸነፈ ነው። ጎሕ ሲቀድ ለማየት ያብቃን ! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !! የወያኔና የባዕድ ቅጥረኞች ሴራ ይከሽፋል !! በተባበረ ትግል ወያኔ ይወድቃል !!

No comments:

Post a Comment