BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Thursday, 26 December 2013


በቦሌ ቡልቡላ፣ በለሚና እና በአቃቂ ክፍለ ከተማ በርካታ ህዝብ ሜዳ ላይ መውደቁ ተገለጸ

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደገለጹት ላለፉት 25 አመታት ከኖሩበት ቤት በጉልበት ተነሱ በመባላቸው ሜዳ ላይ ለመውደቅ ተገደዋል።
ነዋሪዎቹ ስሜታቸውን በከፍተኛ ሀዘን እየገለጹ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል። የመንግስትን እርምጃ በመቃወማቸው የተወሰኑ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁንም ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በአዳማም በተመሳሳይ መንገድ  ከ25 ሺ በላይ ህዝብ ቤት አልባ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።


በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በነጭ ሳር ግቢ የሚማሩ ከ25 ያላነሱ ተማሪዎች መታሰራቸው ታወቀ

Wednesday, 25 December 2013


  በደቡብ ሱዳን ተገደው የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን                         ሴቶች ጁባ ገቡ::

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ የተደፈሩ 4 ሴቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል በሚገኝበት ጁባ ደርሰው ምርመራ እየተደረገላቸው ነው። ሴቶቹ መደፈራቸውንና ሆስፒታል መግባታቸውን ለማረጋገጥ የtቻለ ሲሆን፣ ሴቶቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ አልtቻለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ታውቋል። አምባሳደሩ በዚህ አስቸጋሪ ሰአት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በአገሪቱ ያሉ ኢትዮጵያውያን ተችተዋል።

Thursday, 5 December 2013


በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ገበታው ላይ እያለ በወያኔ ታጣቂዎች በግፍ የተገደለው ወንድማችን ግድያ አጥብቀን እናወግዛለን! የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ወጣቶች ላይ በተደጋጋሚ እየፈፀመ ያለው የግፍ ግድያ, በኦሮሞ ህዝብ ላይ የከፈተው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካል ነው!


ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ በ1983 ዓ.ም በዲላ ዞን፣ ፍሰሀ ገነት ወረዳ፣ ቀበሌ 02 ተወለደ፡፡ ይህ ወጣት ተማሪ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የማርኬቲንግ ክፍል /department/ ተማሪ ሲሆን ወደ ዩኒቨርሲቲ በ2004 ዓ.ም የገባና በ2006 ዓ.ም ይመረቅ የነበረ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ህዳረ 24/2006 ዓ.ም ቁጥራቸው ከ60 በላይ ከሚሆኑ ከክፍሉ ተማሪዎች ጋር በመሆን ዳሽን ቢራ በተባለ ቦታ የግብዣ ፕሮግራም አድርገው ነበር፡፡ ከግብዣው ፕሮግራም በኋላ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ወደ ዩንቨርሲቲው ቅጥር ግቢ እየተመለሰ ሳለ የኦሮሞ ተማሪዎች ለብቻቸው ተነጥለው የትግል ዘፈኖችን እየዘፈኑ ይሄዱ ነበር፡፡ የሀበሻ ልጆችም አካባቢውን በጩኸት በመበጥበጥ በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ሰው ሁሉ ሲደበድቡ ነበር፡፡ የኦሮ ልጆች በወቅቱ የትግል ዘፈኖችን ከመዝፈን ውጪ ያነሱት ሁከት አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን ከዳሽን አለፍ ብለው “ቀሀ” የተባለውን ወንዝ ተሻግረው 18 ቀበሌ ሲደርሱ የሀበሻ ልጆች መንገዱ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የወያኔ ታጣቂዎች ላይ ድንጋይ መወርወር ጀመሩ፡፡