BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 1 April 2014

ውሃ ፣መብራት፣ቴሌ አሁንም ሕዝቡን እያስመረሩት ነው



መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ የመጠጥ ውሃ እና የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሁም የሞባይልና የኢንተርኔት አገልግሎቶች መቆራረጥ በያዝነው መጋቢት ወር ተባብሶ በመቀጠሉ ነዋሪዎች ለአላስፈላጊ ኪሳራ ከመዳረጋቸው ጋር ተያይዞ በነዋሪው ዘንድከፍተኛ ምሬት መፍጠሩን ዘጋቢያችን ገልጿል።
በያዝነው  ወር የኤሌክትሪክ ኃይል ቢያንስ በሁለት ቀን አንድ ጊዜ ለሰዓታት የሚጠፋበት ሁኔታ በተደጋጋሚ መስተዋሉን ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን በዚህም ምክንያት ለአንድ ፍሬ ሻማ ወጪ ከአራት አስከ አምስት ብር ለማውጣት ተገደዋል፡፡
በተጨማሪም አንድ ጄሪካን የመጠጥ ውሃ በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ10 ብር እየተጠየ መሆኑን የጠቀሱት ነዋሪዎች መንግስት በቴሌቪዥን የሚናገረውና በተግባር የሚታየው ሊጣጣም አልቻለም ይላሉ።

የኤርትራ መንግስት ከእኛ ጋር ለመታረቅ ከፈለገ ከጉያችን ያሉ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ምን ይሆናሉ ብለን አንሰጋም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ



መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ጌታቸው አረዳ እንደተናገሩት ” የኤርትራ መንግስት ሃሳቡን ቀይሮ ወደ ሰላም ቢመጣ የኢትዮጵያ መንግስት ችግር የለበትም። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ከጉያችን ስላሉ ምን እንሆናለን የሚል ስጋት የለብንም” በማለት ተናግረዋል።
የታጠቁ የኤርትራ ሃይሎች እርምጃ የማይወስዱት በድንበር አካባቢ የኤርትራ ሰራዊት በብዛት ስላለ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል ዳይሬክተሩ፣ የኤርትራ መንግስት ከእኛ ጋር ለመስማማት ከፈለገ ምንም ቂምና ቁርሾ የምንይዝበት ነገር አይኖርም ሲሉ አክለዋል።

በሀረር የታሰሩ ሰዎች በዋስ እንዲለቀቁ ቢወሰንም ፖሊስ እንደማይለቅ አስታወቀ

መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በከተማዋ ከተነሳው ቃጠሎ ጋር በተያያዘ የታሰሩ 7 ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ እንዲለቀቁ ዳኛ የሱፍ ውሳኔ ያስተላለፉ ቢሆንም፣ እስረኞቹ አስፈላጊውን ክፍያ ከፈጸሙ በሁዋላ ከእስር ለመውጣት ሲዘጋጁ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ክንፈ አብዱል ፈታ ” ፍርድ ቤት አቃቢህግና መርማሪ ፖሊስ ባልተገኘበት ሁኔታ ስለሆነ ውሳኔ ያስተላለፈው አትፈቱም” በማለቱ ዛሬ መለቀቅ የነበራቸው እስረኞች ሳይለቀቁ ቀርተዋል።

ከምዕራብ ሸዋ ዞን መሬት ተቀማን ያሉ የአማራ ተወላጆች ሰሚ አጣን አሉ


1510357_10201735795417514_1563874087_n
“ወደ አንድነት ፓርቲ የመጣነው መሬት ያስመልስልናል ብለን አይደለም” 
 ስምንቱ በአዲስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው አድረዋል  
“ያለ አግባብ የተያዘ መሬት ላይ ሁሌም እግድ ይጣላል” - የዞኑ አስተዳደር 
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ አዋዲ ጉልፋ ቀበሌ፤ የመጡ 29 የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች “መሬት እንዳናርስ ተከለከልን፤ ቅሬታችንን የሚሰማን አጣን” ሲሉ አማረሩ፡፡ ከ29ኙ ስምንቱ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ ወረዳ ሰባት ፖሊስ ጣቢያ፣ ረቡዕ ማታ ታስረው ማደራቸውንና ሀሙስ ረፋድ ላይ መለቀቃቸውን አርሶ አደሮቹ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ አብዛኞቹ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደርና ከሌሎች የአማራ አካባቢዎች መሸኛ በማምጣት መሬት እንደተሰጣቸው፣ በአዋዲ ጉልፋ፣ በአጂላ ዳሌና በዙሪያው መሬት በማልማት፣ ቤተእምነት በመገንባትና ሌሎት መሰረተ ልማቶችን በመስራት ከ20 ዓመታት በላይ በሰላም እንደኖሩ ገልፀው፣ ከ2004 ዓ.ም ወዲህ ግን በአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች ላይ የመሬት እቀባ እንደተጣለ ተናግረዋል፡፡ 

የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ከሥልጣናቸው ተነሡ




የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ የነበሩት ወ/ሮ አማረች በቃሉ፤ከቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቤት ኪራይ ውል አፈፃፀም ጋር በተገናኘ በተፈጠረ የሥራ ዝርክርክነት  ከሃላፊነታቸው እንደተነሱ ምንጮች ጠቆሙ፡፡

መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተፃፈ ደብዳቤ ሃላፊዋ፣ በአሰራር ዝርክርክነት ከሃላፊነታቸው እንደተነሱ የጠቆሙት ምንጮች፤በዝርክርክነት ተብሎ የተጠቀሰውም የቀድሞ ፕሬዚዳንት የቤት ኪራይ ውል አፈፃፀም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በስድስት ወር ውስጥ 41 ሰዎች በመንገድ ጉድጓዶችና ኩሬዎች ውስጥ ገብተው ሞተዋል




  • “በመንገድ ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ተጠያቂ ነው”
  • “መንግሥትን በሰራው ጥፋት መክሰስ ህገ-መንግስታዊ መብት ነው” - የህግ ባለሙያ

ለአዛውንቱ አቶ ተስፋዬ ኪዳኔ መስከረም 10 ቀን 2006 ዓ.ም መልካም ቀን አልነበረም፡፡ ከመ/ቤታቸው ወጥተው ወደ ቤታቸው እያመሩ ነበር፡፡ ከ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ጌጃ ሰፈር በሚወስደው መንገድ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ ሲደርሱ በፍፁም ያልጠበቁት አስደንጋጭ አደጋ አጋጠማቸው፡፡ መንገድ ዳር ከሚገኝ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው እግራቸው ተሰበረ፡፡

“የአገር ፍቅር ከየትኛውም ሽልማትና ሞገስ በላይ ነው”


የአሜሪካ መንግሥት “የአፍሪካ ስኬታማ ወጣት መሪ” በሚል የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት መርጦ ለመሸለም ጥሪ ማድረጉየፓርቲው ልሳን ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ዘግቧል፡፡ በሌላ በኩል ከአሜሪካ ኤምባሲ በኩል የተገኙ መረጃዎች የሰማያዊ ፓርቲ መሪ የተመረጡት የአሜሪካ  ስቴት ዲፓርትመንት  በየዓመቱ ለሚያዘጋጀው የሊደርሺፕ ፕሮግራም እንጂ ለሽልማት አይደለም ይላሉ፡፡  የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው የፓርቲውን ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃልን በጉዳዩና ኤርፖርት ላይ በገጠማቸው ችግር ዙርያ አነጋግራቸዋለች፡፡

ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ኤርፖርት ከገቡ በኋላ ችግር እንደገጠመዎት ሰምቻለሁ፡፡ ችግሩ ምን ነበር?