መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በከተማዋ ከተነሳው ቃጠሎ ጋር በተያያዘ የታሰሩ 7 ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ እንዲለቀቁ ዳኛ የሱፍ ውሳኔ ያስተላለፉ ቢሆንም፣ እስረኞቹ አስፈላጊውን ክፍያ ከፈጸሙ በሁዋላ ከእስር ለመውጣት ሲዘጋጁ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ክንፈ አብዱል ፈታ ” ፍርድ ቤት አቃቢህግና መርማሪ ፖሊስ ባልተገኘበት ሁኔታ ስለሆነ ውሳኔ ያስተላለፈው አትፈቱም” በማለቱ ዛሬ መለቀቅ የነበራቸው እስረኞች ሳይለቀቁ ቀርተዋል።
ችሎቱን የተከታተሉ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት አቃቢ ህጉ በችሎቱ ላይ ተገኝቶ ውሳኔውን ሰምቷል። ዳኛ የሱፍ አቃቢ ህግ ዘግኢቶ በመምጣቱና እስረኞችን በማጉላለቱ እንዲታሰር ወስነው የነበረ ሲሆን፣ ውሳኔው ተግባራዊ አለመሆኑም ታዛቢዎች ገልጸዋል።
ፖሊስ ጋራጅ እየተበላ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ታስረው የሚገኙ እስረኞች ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በጉዳዩ ዙሪያ የፖሊስ ኮሚሽነሩን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሰካላንም።
No comments:
Post a Comment