BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!
Tuesday, 29 April 2014
ያ ትውልድ
የ«ያ ትውልድ ተቋም»ን ድረ ገጽ ይፋ መደረግ 2ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ
የሜይ ዳይ እንቅስቃሴ ቅኝቱን የጀመረው በ18ኛው ምዕተ ዓመት ገደማ የሽካጎ ሄይ ገበያ ግርግር
(Chicago Haymarket Incident) እየተባለ በሚታወቀው የሽካጎ ሄይ ገበያ ሠራተኞች (Chicago
haymarket employee) ባደረጉት በቀን የ8፡00 ሰዓት የሥራ ሰዓት ሕግ ጥያቄ ነው። በዚህም
ሰሌፍ ሊይ ከፖሉስ ጋር በተደረገው ግጭት ሳቢያ በፖሉስ ተኩስ ቁጥሩ ያሌታወቀ ስራተኛ
ሕይወቱን አጥቶአል።
በ1889 እ.ኤ.አ. ገደማ የፓሪሱን አብዮት የመቶ ዓመት መታሰብያ በማድረግ ፓሪስ ላይ
የተሰየመው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ጉባዔ ይህንን ቀን ሚያዝያ 23 (May 1st)ን የሽካጎን
ሠራተኞች ትግል በማስታወስ፤ ይህ ቀን እንደ መታሰቢያነቱ የዓለም ሠራተኞች ትግል መታሰቢያ
ቀን እንዱሆን አሳስቦ ሀሳቡ በዚህ ጉባዔ የደመቀ አድማጭ ሳያገኝ ቀረ።
ከዚህ ስብሰባ በኋላ በ1891 ጄኔቭ ሊይ የተሰየመው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ ጉባዔ ሜይ ዳይን
(May Day) የዓለም ሠራተኞች የትግል መታሰቢያ ቀን እንዱሆን እውቅና ሰጠው። ከዚህ እውቅና
በኋሊ የዓለም ሠራተኞች በቀን የ8፡00 ሰዓት የሥራ ሰዓት ሕግን፣ የሠራተኛ ማሕበር የማቋቋም
መብትን፣ እንዱሁም ላልች የሠራተኛ መብት የታገለበትን ቀን የሚያከብሩበት፡ ለዓለም
ሠራተኞች አጋርነቱን የሚገልጥበት ቀን በመሆኑ በሠራተኛው ሕዝብ ሰልፍ እና በትርዒቱ
የሚያከብረው የሠራተኞች ቀን መሆኑን አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ቀስ በቀስ እያወቀው መጣ ።
ይህ ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ በየካቲቱ 1966 አብዮት ምክንያት የመጣው የሜይ ዴይ አውደ
በዓል በተከበረበት እና በኖረበት የክብረት ሕይወቱ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሊይ የጭንቀት ደወሌል
መታሰቢያ እያደረገ አልፎአል። በመሆኑም ይህ የኢትዮጵያው የሜይ ዳይ (May Day) የጭንቀት
ደወል በተለይ የሚያዝያው 21 ቀን 1969 ዓ.ም. በጨካኝነቱ ተወዲዲሪ የማይገኝለት፤ በመሌኩም
ፍፁም አስቀያሚ ጭፍጨፋ የተካሄደበት ዕለት ነበር። በመሆኑም ድርጊቱ በኢትዮጵያ ሕዝብ የስነ-
ልቡናዊ ዘይቤ ላይ የጣለው ጥቁር መንፈስ፡ በማንኛውም ዘዳ የማይገፈፍ የክፉዎች ሁለ ቀን
የበላይ ነበር።
የሚያዚያ 21 ቀን 1969 ዓ.ም. በተለይ በአዱስ አበባና በተመሳሳይ መልኩ በላልች ክፍለ ሀገር
ከተሞች በዓለን በሰላማዊ ሰልፍ ለማክበር በወጡ ወጣቶች ላይ ደርግ የጥይት ሩምታ በመልቀቅ
በርካታ ሕፃናትና ወጣቶች ደም እንደጎርፍ የፈሰሰበት ዕለት ነው።
«ያ ትውልድ ተቋም» በዚህ ቀን በመላ ሀገራችን ለዳሞክራሲ መብትና ለሕዝብ መንግሥት
ምሥረታ፤ የሊብ አደሩና አርሶ አደሩ ቀዲሚ ፋና ወጊ በመሆን የተጨፈጨፉ ወንድምና
እህቶቻችንን እየዘከርን በጊዜው ከነበረው የሰልፉ ሂደት የአንድን አካባቢ እውነተኛ ታሪክ ትረካ
እናቀርብላችኋለን።
ያ ቀን ከጠዋቱ ጀምሮ ያ ያደኩበት የአዱስ አበባ ጀምበር፡ አዱስ አበባን ሳይመስለኝ እንደቀፈፈኝ
ረፈደ፡፡ (ጢሞ)
ያን ለት ከፓርቲው (ኢሕአፓ) የሚመጣው መረጃ ሠልፉ ይደረጋሌ፡ አይደረግም እየተባለ
ቢለዋወጥም የማታ ማታ ሠሌፉ እንደሚደረግ ታወቀ። (ሳሙኤል)
ከቀኑ 9፡00 ሰዓት መምሕር ቤት፡ የሠሌፍ ዝግጅት ተጀመረ።
1ኛ. ሠሌፉ የሚሆነው ማታ ሆኖ የሚጀመርበት ሠዓት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ሆነ።
2ኛ. ሠሌፉ የሚነሳው ከአቡዋሬ ከ2ኛው እንሳሮ ሆቴሌ ፊት ለፊት ይጀምርና ውስጥ ውስጡን
ተጉዞ፡ በሌዕሌት ዘነበወርቅ ትምህርት ቤት (የአሁኑ የካቲት 66) ጀርባ አዴርጎ፡ በብሊታ ትርፌ
ሹምዬ ቤት በኩሌ፡ የግንፍላን ወንዝ ተሻግሮ፡ ካዛንቺስ ቶታሌ ሊይ ሠሊማዊ ሠሌፉ እንደሚያበቃ
ተወሰነ።
ይህንን ዴርጅታዊ መረጃ ይዘን ከሠሌፉ መሄጃ መስመር በቀር የሠሌፉን ሰዓት እና ቦታ ወደ ታች
ለአባላት ለማስተላለፍ ተስማምተን ተለያየን።
ከቀኑ11፡00 ሰዓት
እንደ ገና ወደ መምሕር ቤት ተመልሰን ለሰልፉ የሚያስፈሌግ ዝግጅት ማድረግ ጀመርን።
ዝግጅት ፦ ወቅታዊ መፈክር፣ መዝሙር፣ የዴምፅ ማጉያ (ሜጋፎን) እና ባትሪ ማዘጋጀት።
ፕሮግራም ፦ ሠልፉን የምንመራው እኛ በመሆናችን፤ የሠሌፉን ሥነ ሥርዓት እና የየራሳችን
የስራ ዴርሻ ምን እንደሚሆን ተነጋገርን። ከመሀሌ ሆኖ መፈክር እያሰማ ሠሌፉን እንዱመራ
(ሳሙኤሌ) ተመደበ። (ጢሞ) ከሠሌፉ ፊት እንዱሆን እና የሠሌፉን መሄጃ አቅጥጫ መስመር
እንዱመራ፤ መምሕርና ቄሱ ከሠሌፉ ኋሊ በመሆን ሠሌፉ እንዲይበተን መስመሩን እንዲይስት እና
በላሊ ሜጋፎን ሠሌፉን ማድመቅ ሀሊፊነት ተደለደልን።
ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት
እንደ ተባባልነው ሠልፉ በሳሙኤሌ መሪነት ሜዲው መሀል ሊይ ሆኖ ”ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግስት
በአስቸኳይ ይቋቋም !” ብል በድምፅ ማጉያው ሲጮህ ወጣቱ ከየጥሻው እየወጣ ከእንሳሮ ሆቴል
ፊትለፊት ያለውን ክፍት ቦታ አጥለቀለቀው። «ለዘመናት» መዝሙር ያስተጋባ ጀመር።
“. . . ቢወቀጥ አጥንቴ
ቢንቆረቆር ደሜ
ላዲስ ሥርዓት ልምላሜ።
ፍጹም ነው ዕምነቴ
የትግለ ነው ሕይወቴ . . .” ያት ቅጽ 1 ቁጥር
ጢሞ ፡ ከሠልፉ ፊት በላሊ ዴምፅ ማጉያ ሳሙኤሌ የሚለውን እየደገመ ለሠልፉ በእጁ ምሌክት
እየሰጠ አቅጣጫውን አስያዘው። ሠሌፉም ተከተለው። መምሕርና ቄሱም በበኩሊቸው በላሊ ዴምፅ
ማጉያ የሳሙኤሌን የጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግስትን ጥያቄ መፈክር እያሰሙ በሠሌፉ ዙሪያ እንደ
እረኛ ይራወጣለ፡፡ ሠልፉ አቅጣጫውን እንዲይለቅ፡ እንዲይቆረስ፡ እየተከተለ ወደ ፊት ይገፋለ።
ሠልፉም በደመቀና በተዋጣ ሁኔታ ወደ ፊት ተጓዘ። ወዱያውም የሠሌፉ ዴምቀትና ጩኽት፡
የሚዘመረው መዝሙር፡ የሚፈከረው መፈክር፡ የዴምፅ ማጉያውን ዴምጽ ዋጠው። እንደ ሰደድ
እሳት አካባቢውን የዋጠው ሰሌፈኛ የጋለ ስሜቱና የወኔው ጉብዝና ትንፋሽ ያካባቢውን አየር
የአጋደው መሰለ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ውስጡን ተጉዘን፡ ሌዕሌት ዘነበወርቅ ትምህርት ቤት
መዳረሻው ሊይ ያለው መስቀለኛ መንገድ ላይ ስንደርስ ሠሌፉ በትሌቅነቱ፡ በግዝፈቱ፡ እንደ ደራሽ
ውሃ ያገኘውን ሁለ ጠራርጎ ይዞ የሚሄዴ ትሌቅ የሰው ሀይሌ ሆነ። የሠሌፉ ጩኸት እያስተጋባ፡
አካሄደ እንደ ጎርፍ ውኃ በጉልበት የሚተራመሰው ሠሌፈኛ በዘነበወርቅ ት/ቤት ጀርባ፡ በ7ኛው ቀን
አዴቬንቲስት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት፡ አዴርጎ በብሊታ ትርፌ ሹምዬ ቤት ጀርባ አሌፎ በግንፍላ
ወንዝ ሊይ፡ በአስፋ ወሰን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት (የአሁኑ ምሥራቅ ጎህ) ደን ደኑን፡ ካዛንችስ ቶታሌ
ሲደረስ የሠሌፈኛው መዝሙርና መፈክር እያስተጋባ ካዛንቺስን አጥለቀለቀው። ይህ ሰልፍ
በደረሰበት ሁለ እንደ ደራሽ ጎርፍ ያገኘውን ሁለ እየዋጠ ገዝፎ እዚህ የደረሰው ትዕይንተ ህዝብ
ሲታይ፡ ቤቱ የቀረ ወጣት ያለ አይመስልም ነበር። ይህ የሰው ጎርፍ፡ ካዛንቺስን ያጥለቀለቀው ለ15
ደቂቃ ያህሌ መፈክር ሲያሰማ ቆይቶ ለዘመናትን ዘምሮ ሲያበቃ፡ ሠልፉ በዚሁ እንዲበቃ ተነግሮ፡
ላለ ሠልፍ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ ማሳሰቢያ ተሰጥቶ ሠልፉ ተበተነ።
ሰልፉ ካበቃ በኋላ ሁለም ወደየቤቱ ተመለሰ፡፡ ሠልፉ እስቲበተን እዛው የቆዩትም ጢሞ፣ ቄሱ፣
ሳሙኤል እና መምሕር፡ መምህርን ቤቱ ድረስ በመሸኘት እና ድምፅ ማጉያዎቹን በመደበቅ በታላቅ
ደስታ፡ በታላቅ ድል ወደ የቤታቸው ገቡ።
ሚያዚያ 22 ቀን 1969 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት
ዑራኤሌ ቤተ ክርስቲያን እንዴንገኛኝ ቀጠሮ ስለነበረን፡ ቤተ ክርስቲያን ተሳሊሚ መስዬ ወደዚያው
እሄዳለሁ። ጠዋትነቱን በሰውነቴ ሰማሁት፡ በሳምባዬም ያንን የአዱስ አበባ ቀዝቃዛ አየር ማግ ማግ
አደረኩት። ግን የትናንትናው ሙሉ ዕለት ተኩስ እና የውሻው ጩኸት ሲረብሸኝ ስለ አደረ
ቅ..ፍ..ፍ.. ቅ..ፍ..ፍ.. እያለኝ ዑራኤሌ ደረስኩ። (ጢሞ) አንዲህ አንዲህ እያልንም ተገናኘን።
ሰልፉ እኛጋ እንደተሳካው በላልች ቀበላዎች አለመሳካቱን መረጃ ደረሰን፡፡ በአንዲንዴ አካባቢዎች
ደርግ በደረሰው መረጃ መሠረት ገዲይ ኃይልቹን አሰማርቶ ሰልፉ ሲጀመርና የጥይት ሩምታ
ሲለቀቅ እኩል ሆነ። በርካታ ሕፃናትና ወጣቶች "ፍጹም ነው እምነቴ" እንዳለ ሕይወታቸውን
ለትግል ሰጡ። አዲስ አበባ የደም ጎርፍ አጥለቀለቃት። አስፏልቶች በወጣቶች ደም ታጠቡ።
በየአካባቢው ምሽቱ ደም በጠማቸው የደርግ ገዲዮች ሽብር ሆነ። ማን ይሙት ማን ይትረፍ
መለየት እስኪያቅት ተኩስና ለቅሶ ዕለቱን አድረውበት፡ ለተረኛው ንጋት ለቀቁ።
ወደ ቤቴ ስመለስ፡ በማልፍበት አቅጣጫ ሁለ የየቀበላው ነዋሪ ለሴቶቹ ነጠላ እንኳ ሳይደርቡ
በሌሊት ልብሳቸው ጸጉራቸው እንደቆመ ደረታቸውን እየመቱ፡ ወደ ሰማይ እጆቻቸውን እያወራጩ
በመረበሽ ይሯሯጣለ። ወንድቹ በየበራፉቸው ሊይ በዝምታ ቆመው እንደ ጸሎተኛ አንዳ ወደ
ሰማይ፡ አንዴ ወደ መሬት አንገታቸውን እያደረጉ፡ የልጆቻቸውን ሞት ይዞ የሚነፍሰውን ትኩስ
ወሬ በፍርሀት ይጠብቃለ። አንደን ቀበላ አቋርጬ ወደ ሌላው እያልኩ ሠፈሬ መዳረሻ ላይ ቀስ
እያለ የስዉ ሩጫ፡ ወደ ግርግር፡ ጩኸቱ ወደ ለቅሶ እያተለወጠ መጣ። ንጋቱም ወደ ረፋድ፡ ያት ቅጽ 1 ቁጥር
ረፋድ ወደ እኩለ ቀን ሲደርስ፡ ድፍን የአዱስ አበባ ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ባገሩ፡ በሰፈሩ፡ በቤቱ ሙሾ ሊያወርድ ሀዘን ተቀመጠ። ነጠላዎች ተዘቀዘቁ፡ ቀሚሶች ጥቁር ሆኑ፡ እናቶች አባቶች ሀዘን፡
ቁጭትና እየዬ ዋጣቸው።
ከቀኑ 9፡30
መምህር ቤት፡ የደርግ መንግስት ትናንት ላሉቱን “የጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግስት ይቋቋም !” ብል
ሰልፍ የወጣውን ወጣት ገደል የገደለበትን የጥይት ዋጋ 250 ብር ማስከፈለን ሰማን፡ ቤተሰቦች
የሌጆቻቸውን ለቅሶ መከሌከሊቸውን አየን። በዚያ ምሽት የከፍተኛ 15ቱ ቀበላ 23 አብዮት ጠባቂ
ሉቀ መንበር ፲/አ ሰልሞን ከአንዴ ቤት አራት ወንዴማማቾችና (ሐምሴ ብርሃኑ፣ ግርማ ብርሃኑ፣
ሞገስ ብርሃኑና ተፈራ ብርሃኑ) አንዴ ያክስታቸውን ሌጅ ከተኙበት አውጥቶ በመግደል ወላጅ
እናትና አባት ያሎቸውን ብርቅዬ ሌጆች በአንዴ ምሽት ጭጭ አደረጋቸው። ግራዚያኒስ ከዚህ
በሊይ ምን አደረገ? የ1969 ዓ.ም. ሚያዚያ 21 ቀን ሠሌፍ በአዱስ አበባ ብቻ እስከ 2000 ወጣቶች
የተሰውበት ፡ ከግራዚያኒ ጭፍጨፋ ቀጥል አዱሱ የኢትዮጵያ ልጆች የእልቂት ምዕራፍ ሆነ።
ደርግ አንደ ብርቅዬ ትውልድ ጨረሰ። ሀገሪቷ በዴህነት አቅሟ ለልማትና ለዕድገት
የኮተኮተቻቸውን ልጆቿን ደርግ በሊ። በሕዝብ መብትና ነፃነት በግምባር ቀደምትነት የተሰለፉ
ጀግኖች ሌጆቿን፤ እምቡጥ አበባዎቿን ኢትዮጵያ ተነጠቀች። ክንዳ ልጇን አጣች።
ኢትዮጵያዊነት ኩራቷን መለያ ክብሯን ጥቁር ድባብ አጠላባት። እምቢኝ ለመብቴ፣ እምቢኝ
ለሀገሬ፣ እምቢኝ ለሕዝብ ያለ ትውልድ በጥይት ተለቀመ። እየታነቁ ተገደሉ። በቁማቸው ከገደል
አፋፍ ተወረወሩ። ወደ ባህር ተጣለ። ሕጻናት ይህን አረመኔያዊ ድርጊት እያዩ እንዲያደርጉ
ተገደዱ። የዚህ አረመኔ አገዛዝ ጦስ ለዛሬም ተርፎ ብሔራዊ ስሜት እተሸረሸረበት፤ ያባት
የእናቶቻችን ጀግንነት ተረት እሆነበት ዘመን ላይ አድርሶናል።
«ያ ትውሌዴ ተቋም» ልክ የዛሬ ሁለት ዓመት ለሀገራቸው ክብርና ለሕዝባቸው መብት ሲፋለሙ
ክቡር ሕይወታቸውን ለሰዉት የኢትዮጵያ ጀግኖችና የያ ትውሌዴ ሰማዕታት መታሰቢያነት በ«ያ
ትውሌዴ» ስም ያ ትውሌዴ ዴረ ገጽን (www.yatewlid.com ወይም www.yatewlid.org)
ለሕዝብ ይፋ ያደረግንበትን ሚያዝያ 23 ቀን 2004 ዓ.ም. ሁለተኛ ዓመት ስናከብር ታሪካችን
ከትውሌዴ ትውሌዴ ይተላለፍ ዘንድ በሩን በመክፈታችን ታላቅ ደስታ እየተሰማን ነው። ዛሬ
አጠገባችን የሌሉትን ወንድምና እህቶቻችንን ቢያንስ ስማቸውንና ምስላቸውን እንደያዘ ለትውልድ
የሚተላለፍ በየትም ሀገርና ቦታ ሆነው የሚያዩት ሀውልት አቁመንላቸዋልና ከተቀበልነው ቃል
ኪዲን ጠብታዋን በማድረጋችን እየተደሰትን ከፊታችን የተደቀነውን ከባድ ኃሊፊነት በትጋትና
በሙለ ስሜት ለመወጣት ቃል በመግባት ነው። አብረን ተሰልፈን፡ አብረን ጮኸን፡ አብረን
ታግለን፡ አብረን ተሰቃይተን በተለያየ አጋጣሚ ዛሬ በሕይወት ያለን የዚያ ትውልድ አባላት
ቢያንስ ልንዘክራቸው፡ ልናስባቸው ይገባል። እኛ ልንኖር እነሱ ሞተዋል። ደማቸውን ያፈሰሱ
አጥንታቸውን የከሰከሱት "ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ይቋቋም !" "የዳሞክራሲ መብት ያለገደብ
ለሁለም !" እየፈከሩ፡ "ደሀ ደሀ ምን ታየበት፤ እንዳይማር የሆነበት" እየዘመሩ፡ ለሕዝብና ለሀገር
እንደጮሁ፡ መሆኑን በመመስከር ታሪካቸው ታሪካችን፡ ደማቸው ደማችን ነውና፡ እነሱን
እያስታወስን አኩሪ ተጋድሎችንን ከታሪክ በራዦችና ጥላሸት ቀቢዎች በመጠበቅና በመከልከል
ቀጣዩ አዱስ ትውልድ እነማን እንደነበርንና ምን ሠርተን እንዳለፍን ግንዛቤ በማስጨበጥ ከእኛ
ሊቀስም ከሚችለው ትምህርት በመውሰድ ሀገሩንና ሕዝቡን አፍቃሪ ብቁ ዜጋ ይሆን ዘንድ
ማዘጋጀት ይጠበቅብናል።
ውድ የኢትዮጵያ ልጆችና ሕዝባችን ! በአፋኝ አገዛዞች በተለይም በፋሽስቱ ደርግ ኢሠፓ አገዛዝ
ለዳሞክራሲያ መብትና ለሕዝብ መንግስት ምሥረታ የላብ አደሩ፣ የአርሶ አደሩ በጥቅለ የመላው
ኢትዮጵያ ሕዝብ ግምባር ቀደም አለኝታ በመሆን አምባገነኑን ፋሽስታዊ አገዛዝ ሲፋለሙ
እስከወዲያኛው ያሸለቡ የኢትዮጵያ ልጆች በያ ትውልድ ተቋም ጥረት ገደሏቸውና ታሪካቸው ከፍ
ከፍ እያለ ነው። የ«ያ ትውልድ ተቋም» የኢትዮጵያ የትድል ታሪክ መረጃ ማሰባሰቢያ በሆነው ድረ
ገጽ www.yatewlid.org ወይም www.yatewlid.com በየቦታው ወዴቀው የቀሩ ወንዴሞቻችንና
እህቶቻችን ታሪክ እንዲይታወስ፣ እንዲይነሳ፣ እንደተዳፈነ ይቀር ዘንድ ምኞታቸውና ፍላጎታቸው
የሆኑትን ዛሬ አሳፍሯል። በዚህ የሁለት ዓመት ጉዟችን ከጎናችን ሳትለዩ ላበረታታችሁን በሀገር
ቤትም በውጪው ዓለም ላላችሁ የዚያ ትውልድ ወገኖችና አካላት፤ በተለያየ ወቅት ትብብር
ላደረጋችሁልን የሚዱያ፤ የድረ ገጽ ወገኖችና በጠንካራ መሰረት በመሰባሰብ «ያ ትውልድ
ተቋም»ን እዚህ ላደረሳችሁት የ«ያ ትውልድ ተቋም» አባላት በሙሉ የዓለም ሠራተኞችን ቀን ሜይ
ዴይ 2004 ዓ.ም.ን ምክንያት በማድረግ ለመሊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ ላደረግነው ያ ትውልድ
ዴረ ገጽ ሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓልና ዝክረ ሰማዕታት ቀናችን እንኳን በደህና አደረሳችሁ እያልን
ቅን ትብብራችሁና ድጋፋችሁ አሁንም ከሰማዕታቱ ጋር ይሁን እንላለን።
«ያ ትውሌዴ ተቋም» በዚህ የሁለት ዓመት ጉዟችን ምን አቅደን ስንቱ ተግባራዊ ሆነ? «ያ
ትውልድ ተቋም» ይዞት በተነሳው ተልዕኮ ተግባራዊነት ሊይ ያጋጠሙን አዎንታዊና አለታዊ
ጉዲዮች ምንዴናቸው? የመሳሰለትን ጥያቄዎች በመቃኘት ቀጣይ የአጭርና የረዥም ጊዜ ዕቅድ
በማውጣት በተጨማሪ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍልችና ቡዴኖች የሚደርሱንን አስተያየቶችና
ምክሮች ግንዛቤ በመስጠት ለቀጣይ ጉዟችን በጠንካራ ስሜት በመዘጋጀት ቀኑን እንዘክረዋለን።
የ«ያ ትውልድተቋም» ራዕይና ተልዕኮ ስኬታማነት ያሳለፍናቸው የሁለት ዓመት የሥራ
ክንውናችን ምሥክር ነውና “ሜይ ዳይና ዝክረ ሰማዕታት” ስንል ጊዜያችን፣ ዕውቀታችን፣
ገንዘባችንና ኃይላችን የታሪካችን ምሰሶ የሆኑት ሰማዕታት ወገኖቻችን ናቸውና የ«ያ ትውልድን»
ታሪክ ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር የምናደርገው ጥረት ቀጣይነቱን በማስመር ነው።
<<ያ ትውልድ ተቋም>>
ሚያዝያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም. (May Day 2014)
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment