BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Saturday, 5 April 2014

ኢትዮጵያዊው ኖርዌጃዊ ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ካለፈቃዱ ተወሰደ”

ኢህአዲግ/ወያኔ የኖርዌይ ዜግነት ያለውን ትውልደ ኢትዮጵያዊ የቀድሞ የጋምቤላ ክልል አስተዳዳሪ ኦኬሎ ኦቻላን ከደቡብ ሱዳን ጋር በመተባበር ጠልፎ ወደ ኢትዮጵያ በመውሰዱ ከኖርዌይ መንግስት ጋር ዲፕሎማሳዊ ፍጥጫ ውስጥ ገብቷል።ኢህአዲግ/ወያኔን ”ድንበር ተሻጋሪ አሸባሪ” ለመሆኑ ይህ በቂ ማስረጃ ነው የሚሉ አሉ።

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ኦኬሎ ኦቻላን በታህሳስ/1996 ዓም (ዲሴምበር 13/2003 እ አ አቆጣጠር) በጋምቤላ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ወቅት ከሀገር መውጣታቸው እና በተለያዩ ሃገራት ከኖሩ በኃላ ወደ ኖርዌይ በመምጣት ዜግነት ማግኘታቸው ይታወቃል።
ሐሙስ መጋቢት 25/2006 ዓም ከ 150 ዓመት በላይ በሕትመቱ ዓለም መቆየቱ የሚነገርለት የኖርዌይ ቁጥር አንድ ተነባቢ ጋዜጣ
አፍተን ፖስተን” ”ትውልደ ኢትዮጵያዊው ኖርዌጃዊ ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ካለፈቃዱ ተወሰደ” በሚል አርዕስት ስር ባስነበበው ዘገባ ስር ጋዜጣው ዜናውን ሲቀጥል ” የሰብአዊ መብት አክቲቪስት” በማለት የጠራቸውን አቶ ኦከሎ ኦቻላ በደቡብ ሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች አጋዥነት ወደ ኢትዮጵያ ተወስደው እንዲታሰሩ መደረጋቸውን እና ኖርዌይ ጉዳዩን አዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲዋ እየተከታተለች መሆኗን ጋዜጣው ያብራራል።
ሚስተር ስቫየን ሚቸልሰን የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኮምንኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ስለ ጉዳዩ የሚከተለውን ብለዋል ”He confirmed that Aquai (ኦኬሎ) is a Norwegian citizen and that UD is familiar with the matter . The Norwegian Embassy in Addis Ababa now assisting Aquai”

No comments:

Post a Comment