ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የመንግስታቸውን የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ለፓርቲያቸው የፓርላማ አባላት ባቀረቡበት ወቅት(ሁለት ወንበር ከማጣታቸው ውጪ) ‹‹ዴሞክራሲያዊነት ለመንግስታቸው የህልውና ጉዳይ ››እንደሆነ አውስተው ነበር፡፡ልማታዊ በመሆናችን ዴሞክራሲን እንደ ትርፍ ነገር የምንቆጥር የሚመስላቸው ተሳስተዋል ለማለት አስረግጠው ሲናገሩ አድምጬ ነበር፡፡
ኢህአዴግ በየጊዜው የፖለቲካ አክሮባት እየሰራ ንፋሱ እንደወሰደው ከአንዱ ርዕዩተ ዓለም ወደ አንዱ እንደፌንጣ እየዘለለ ‹ልማታዊ ወ ዴሞክራሲያዊ ነኝ› እያለን ነው፡፡ድርጅቱ ወይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት መንግስት አንዱን መሆን ሳይችል በእመስላለሁ የፖለቲካ ድርቅና ልማቱም ዴሞክራሲውም አይቅርብኝ እያለ ነው፡፡
ኢህአዴግ በየጊዜው የፖለቲካ አክሮባት እየሰራ ንፋሱ እንደወሰደው ከአንዱ ርዕዩተ ዓለም ወደ አንዱ እንደፌንጣ እየዘለለ ‹ልማታዊ ወ ዴሞክራሲያዊ ነኝ› እያለን ነው፡፡ድርጅቱ ወይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት መንግስት አንዱን መሆን ሳይችል በእመስላለሁ የፖለቲካ ድርቅና ልማቱም ዴሞክራሲውም አይቅርብኝ እያለ ነው፡፡
ልማትን እንደ ኢህአዴግ ችሮታ ከሚቆጥሩ ሰዎች ጋር መከራከር ትርፉ ልፋት ብቻ ቢሆንም አንድ መንግስት መንገድ፣መኖሪያ ቤት፣ግድብ ሆስፒታል ወይም የትምህርት ተቋማትን ካልሰራ ምኑን መንግስት ተሰኘ?እነዚህን ነገሮች ስለሰራም ሊኮፈስ አይችልም፡፡ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች የሚሰሩት ከህዝብ በሚሰበሰብ ግብር አገሪቱ ከድርጅቱ በኋላም ቢሆን በምትከፍለው ዕዳ ነው፡፡ኢህአዴግ እነዚህን ነገሮች ለመስራት ከራሱ የሚያወጣው ሰባራ ሳንቲም የለም፡፡
እነዚህ ነገሮች በሙሉ ራሳቸውን ‹ልማታዊ መንግስት› በማለት በማይጠሩ ገዢ ፓርቲዎች የሚከወኑ መሆናቸውንም መዘንጋት የለብንም፡፡ከልማታዊነት ጎን ለጎን ኢህአዴግ ራሱን የሚመለከተው ‹ዴሞክራሲያዊ› በማድረግ ነው፡፡የተከበሩ አቶ ኃይለማርያም ለድርጅታቸው ዴሞክራሲያዊነት የህልውና ጉዳይ መሆኑን አስረግጠው ነግረውናል፡፡አቶ ኃይለማርያም ይህንን ንግግር ካደሩ በኋላ ባሉት ጥቂት ቀናቶች የተፈጸሙ የኢ-ዲሞክራሲያዊነት መገለጫዎችን እንመልከት፡፡
በወለጋ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላነሱት ጥያቄ የተሰጣቸው ምላሽ ከጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የተገኘ አልነበረም፡፡ፖሊሶችና ፌደራሎች በተለመደው መንገድ ተማሪዎቹን ቀጠቀጧቸው፣የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይፋ ባልሆነ መንገድ ተለቃቅመው እስር ቤት ተወረወሩ፣ታሳሪዎቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ የተደረጉ ጥረቶች በሙሉ የተሳኩ አልነበሩም፡፡ህገ መንግስቱ የህጎች ሁሉ የበላይ መሆኑ ቢነገርለትም በተዋረድ በወጣ አዋጅ ተሸሮ ተጠርጣሪዎቹ በዘመዶቻቸው፣በጓደኞቻቸው እንዳይጠየቁ ተደርገዋል፡፡እነዚህ ለመጥቀስ የሞከርኳቸው የጥቂት ቀናት ጥቂት ድርጊቶች ገዢው ፓርቲ ዴሞክራሲያዊነትን የህልውናው ማስጠበቂያ በማድረግ እንደማይወስደው ‹‹ዴሞክራሲያዊነትን››ለምዕራባዊያን ማታለያነት ሊጠቀምበት እንደፈለገ ማሳያ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment