BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!
Thursday, 14 July 2016
ባለፈው ታሪክ ብቻ የሚኖር ፤ በወደፊቱ ላይ ማተኮር ይሳነዋል !
በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ
ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. የተላለፈ ሐተታ
ኢትዮጵያ፤ እንደማነኛውም ሀገር፤ የራሷ መጥፎም ሆነ መልካም ታሪክ ነበራት/ አላት። የጥቃትና የድል፤ የጥጋብና ረሀብ፤ የስፋትና የመጨራመት፤ የመከራና ሀሴት ዘመናት ሁሉ ተፈራርቀውባታል ። የተለያዩ ሥርዓተ- ማኅበራትንና ገዥዎችን ሁሉ አሳልፋለች። ድንበሯ ያልተደፈረ ፤ ታሪኳ የተከበረ ፤ ሉዓላዊነቷ ያልተገሰሰ ፤ የንግድ መናሃርያዋ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ የተዘረጋ፤ ኃያል ሀገር ነበረች ። የጦርና የንግድ መርከቦቿም በውቅያኖሶችና ታላላቅ ወደቦች ይንሳፈፉ ነበር። ያ ሁሉ ዛሬ፤ ነበር ሆኖ አልፏል ! " የነበር ሲያወሩት ይመስላል ያልነበር፤ የኢትዮጵያ ጠረፍ ውቅያኖስ ነበር ! " እያሉ መናገር፤ የዕለት -ተዕለት ቁዘማ ሆኖ ቀርቷል ! ታሪካዊና ነባራዊ ሀቆች ግን እነኝኽ ናቸው ! ዜጎቿም በነኝህ ተፈራራቂ ሥርዓተ- ማኅበራትና ስልተ-ምርቶች ሂደት ተጉዘዋል። ያም ሁሉ ሆኖ እስካሁን ደረስ፤ የራሳቸው ዕድል ባለቤቶችና ወሳኞች አልሆኑም።
Tuesday, 5 July 2016
ምሣር የበዛበት የመገናኛ ብዙሃን [Chopping Our Free Media]
ከአምሳለ ዓለሙ
ሰኔ 2008 ዓ.ም
የመገናኛ ብዙሃን፦ የሕትመት ውጤቶች (ጋዜጣና መጽሔት)በሬድዮና በቴሌቭዥን የሚተላለፉ እንዲሁም በኢንተርኔት የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦች ማለት ነው።
የሃሳብ ነጻነትና የመገናኛ ብዙሃን መከበር የመብት ጥሰቶችን ለማጋለጥና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሰረት ነው። ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት ለሰው ልጅ የተሰጠው ተፈጥሮአዊ ችሮታ ሲሆን ሰብአዊ መብትንና ክብርን የማስጠበቂያ መሳሪያ ነው።
ዜና የማግኘት መብት መኖር በተለያየ ደረጃ ለመልካም አስተዳደር መስፈን፣ የመንግሥት ተግባር ግልፅነትና የተጠያቂነት ግዴታ እንዲኖርበት አስተዋፅዖ ያበረክታል። በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ችሎታ ቢስ ባለሥልጣናትን በነቂስ ለማውጣት፣ የሀገር ሀብት በባለሥልጣናት እንዳይባክን በአባላቱም እንዳይዘረፍ ነቅቶ ለመጠበቅና ለመከታተል፤ ከዚሁ ጋር በማያያዝም ሙስናን፣ ፍርደ ገምድልነትን፣ አድሎዎአዊነትን ለማጋለጥ ይረዳል። ከዚህ በተጨማሪ የተቀላጠፈ አስተዳደር ሂደትና የእድገት ጅማሮዎች ለፍሬ እንዲበቁ እንዲሁም ለተሻለ የኤኮኖሚ፣ የአስተዳደር አገልግሎትና ለተሻለ የሕግ ዋስትና መሰረት ይጥላል።
Wednesday, 29 June 2016
የወያኔ ስርአት ዋነኛ የጀርባ አጥነት የብሔራዊ መረጃ በዘረፋና በሽሽት ተጠምዷል
የልዑል ዓለሜ ዘገባ
እራሱን የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን እያለ የሚጠራዉ የወያኔ ስርአት ዋነኛ የጀርባ አጥነት የብሔራዊ መረጃ በዘረፋና በሽሽት ተጠምዷል።
በሰሞኑ ይኸው የብሔራዊ መረጃ 9 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ በአለም ዙሪያ የሚገኙ የህወሃት የመረጃ ክንፍ ቀድሞ የሰየማቸዉንና በስለላ ስራ ላይ ተሰማርተዉ የነበሩ የሌላ ብሔር አባላቶችን በሙሉ መልሶ ወደ ሐገር ቤት በማስገባት በምትካቸዉ ከ 242 የሚጠጉ የአንድ ብሔር ብቻ ተወላጅ የሆኑ የመረጃ ሰራተኞችን እየተካ ይገኛል።
Friday, 24 June 2016
Monday, 6 June 2016
Ethiopian journalist: 'I was jailed and tortured' Date 12.05.2016
He is one of Ethiopia’s most critical journalists. Muluken Tesfaw is in Europe and too scared to return. He doesn’t want to share his location, but talked to DW about press freedom declining dramatically in his country.
According to a report by the Committee to Protect Journalists (CPJ), released late last year, the number of journalists imprisoned in Iran, Vietnam, and Ethiopia increased in 2015. The report said that in all three countries a climate of fear for the media persists, with many of those released continuing to face legal charges or harsh restrictions, including forced exile.
Sunday, 29 May 2016
A Race to the Bottom: Is Proud Ethiopia at Risk?
By Aklog Birara (PhD)
May 29, 2016
Regardless of our political, religious and ethnic differences and the formidable odds Ethiopia continues to face, most ordinary Ethiopians agree Ethiopia has a remarkable and long history as a free and independent multiethnic and multi-religious nation. Although we claim and believe in this fundamental principle, we are so afraid, timid, fractured and reluctant to express Ethiopia’s inviolability in the strongest terms possible that we are setting the country for Balkanization. For instances, those who believe in one Ethiopia, one country, one diverse but unified population in which---as a matter of right and not privilege--each person is endowed with the legal right to live anywhere safely, express, voice, participate in the socioeconomic and political regardless of tribe, religion and location have failed to collaborate and speak with one voice. It is not uncommon these days for political elites and intellectuals to speak with two voices depending on their audiences. As a result, the voices of tribalism and secession dominate the political scene. This suits the ruling party.

Friday, 27 May 2016
25 years that were never lived ያልተኖረበት 25ኛ ዓመት!
ግንቦት 19 2008 ዓ.ም
ከአምሳለ ዓለሙ
ዘረኛው ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አልሞ የተንቀሳቀሰው ገና እንደ ድርጅት ሳይዋቀር ሳይቀፈቀፍ በዕንቁላልነቱ እያለ ነበር። የማንን ዓላማ የማንን ምኞት ለማስፈጸም ነው የሚለው ጥያቄ የሃገሩን ታሪክ በገረፍ ገረፍ ለሚያውቀው እንኳ የተሰወረ አይደለም። ወያኔነት ፀረ አገር፣ ፀረ ሕዝብ፣ ፀረ ታሪክ፣ ፀረ ሃይማኖት፣ ፀረ ሁሉም ጥሩ፣ ደግ ነገር ሲሆን፤ የመጨረሻ ደረጃው (ለመከሰቱ ምንም ጥርጣሬ የማይኖረን) ደግሞ በአሰቃቂ ሁኔታ ይህ ከይሲ ቡድን ሊጠፋ፣ እንደ ጉም ሊበን፣ እንደ አዋራ ሊበተን ጉዞው መጀመሩ ነው። ግንቦት 19 ብለን ወደ 21 እንዳንዘልና ግንቦት 20ን ወደ ቀን መቁጠሪያው ለመመለስ ከመቼውም በበለጠ አንድ ሆነን ኃይላችንን አስተባብረን ፀረ ወያኔ ትግላችን መፋፋም አለበት።
ገና ከጅምሩ የተባበረ ክንድ ድል የመንሳቱ እውነት ያሳሰበው ወያኔ በ-የአውቅልሃለሁ ብሂል ሽፋን ሁሉም ብሄር የራሱን ከፈሎ ከጣራ በታች እንዳለ አምፑል ለራሱ ቤት ብቻ እንዲጠቅምና እርሱነቱ እንዲገደብ፣ ተከልሎ እንዲኖርና የእኔ የበላይነት ስሜትን በማጫር የህብረትን ዓላማ አዳክሞ አመለካከትን ልምሾ የማድረግ ስልቱ ጥቂት የጠቀመው ቢመስልም፤ የሰፊው ሕዝብ የእርሱነቱ መለያ፣ የመኖሩ ዋስትና፣ ማንነቱ ያዋሐደው እርሱነት አለውና ልክ የአንድን ሰው አካል በየክፍሉ ገነጣጥሎና ለይቶ በሕይወት ኑር የማለት ያህል አዳጋች ሆኖበታል።
Subscribe to:
Posts (Atom)