“ኦክስፋም” በመልካም ሥራቸው ከታወቁ ትላልቅ ዓለም ዓቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አንዱ ነው። በቅርቡ አንድ መቶ ሀያ አምስት አገሮችን ያካተተ ከምግብ አቅርቦትና አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ አራት ዝርዝርና አንድ አጠቃላይ አመላካቾች አሉት። 1. አመላካች አንድ: የምግብ እጥረት ይህ አመላካች “በየአገሮቹ ምን ያህል ለበላተኛው የሚበቃ ምግብ አለ?” የሚለውን ይለካል። በጥናቱ ውጤት መሠረት በምግብ እጥረት እጅግ የተጎዱ የመጨረሻዎቹ አስር አገሮች የሚከተሉት ናቸው: – ቡሩንዲ፣ የመን፣ ቻድ፣ ኢትዮጵያ፣ ማዳጋስካር፣ ናይጄሪያ፣ ላኦስ፣ ባንግላዴሽ፣ መካከለኛዉ አፍሪካ ሪፑብሊክ እና ህንድ። ኢትዮጵያ አገራችን ከመጨረሻ አራተኛ ናት። 2. አመላካች ሁለት: ለምግብ የመክፈል አቅም (Affordability) ይህ አመላካች “የአገሩ ሕዝብ በአገሩ ዋጋ ምግብ ገዝቶ ለመብላት ምን ያህል አቅሙ ይፈቅድለታል?” የሚለውን የሚመልስ ነው። .........
BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!
Thursday, 30 January 2014
“ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው የውጭ ገበሬዎች የሚያስፈልጓቸው? ምንድን ነው ይዘውልን የሚመጡት?” አቶ ግርማ
"አንድም ሰው ከቀዬው እንዲፈናቀል አልተደረገም" ሚኒስትር ዴኤታ
- “ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንቶች እንደታሰቡት ውጤታማ አልሆኑም” መንግሥት
- መንግሥት የውጭ ባለሀብቶች የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያን አይመለከትም አለ
የውጭ ባለሀብቶች በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወስደው እያለሙ እንጂ፣ መሬት ለመቀራመት ብለው ወደ ኢትዮጵያ አልገቡም ሲል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
“መሬት መቀራመት ኢትዮጵያን ጭራሽ አይመለከታትም፤” ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ የመሥሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማው ማክሰኞ ዕለት ሲያቀርቡ፣ ሰፋፊ መሬቶች ወስደው በግብርና ላይ ኢንቨስት እያደረጉ ስለሚገኙ የውጭ ባለሀብቶች ትክክለኛ ማብራሪያ እንዲሰጡ በተጠየቁበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት፡፡...........
በጎንደር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የቅስቀሳ ቡድን አባላት በፖሊስ ታሰሩ፡፡
የጎንደር ነዋሪ ህዝብ የፖሊስ ጣቢያውን በመክበብ የታሰሩት እንዲፈቱ እየጠየቀ ይገኛል፡፡ ጥር 25 2006 ዓ.ም.
የኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለልን ህገወጥነት በተመለከተ በጎንደር መስቀል አደባባይ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ
አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የተጓዘው የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ሉኡካን ቡድን በዛሬው እለት
በጎንደር ከተማ በቅስቀሳ ላይ እንዳሉ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው ሲሆን ጎንደር የገባው ቡድን በጠቅላላ በእስር
ላይ ይገኛል፡፡ .................................
Ethiopian lady raped by a gang of six Sudanese detained
ESAT News
ESAT has managed to obtain a video clip that shows an Ethiopian lady named Kedria Endris being sadistically raped by a gang of six Sudanese youth; the lady is under police custody in Sudan.
Arega, the Head of Diaspora Section at the Ethiopian Embassy in Sudan, has admitted that the lady has been ‘raped’ but he said higher officials need to give him permission in order to give much information.
The lady had contacted the youth in October last year looking for a place to rent. The youth, promising to find her a place took her to a room where they sadistically raped her, fooled around her naked body and also video recorded their acts.
Embassy insiders told ESAT that the Sudanese government that has been worried of its own images has detained Kedria in Morgan Police Station; the Embassy official said the lady is in a good condition. The Sudanese Court is attempting to protect the State from being responsible by blaming the victim of not reporting the incident when it happened......
የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ
በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት ሊከሰቱ የሚችሉ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋዎች ይፋ ሆኑ፡፡ በርካታዎቹ በአፍሪካ አገራት ሲሆኑ አደጋው ካንዣበበባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
በአሜሪካ የፖለቲካ ሳይንቲስት የሆኑት ጄይ ዑልፌልደር የተለያዩ የሒሳብ ስሌቶችን በመጠቀም የ2014ዓም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያቸውን ሰጥተዋል፡፡ እንደ እርሳቸው ትንበያ ከሆነ 40 አገራት ቀይ የአደጋ ምልክት በርቶባቸዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩ መፈንቅለ መንግሥት እንዲሆን የሚመኙት ነገር ባይሆንም የመከሰቱ ጉዳይ ግን መነገር ያለበት ነው ይላሉ ምሁሩ፡፡
በተለያዩ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጦች ላይ የተዘገበው ይኸው ጥናት እንደሚያመለክተው በዓለማችን ላይ 40 አገራት ከፍተኛ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋ ያነጣጠረባቸው መሆናቸውን በጥናቱ ተገልጾዋል፡፡ አብዛኛዎቹም ከአፍሪካ መሆናቸው አሁንም አህጉሪቱ ለበለጠ ቀውስ የተጋለጠች መሆኗን የሚያሳይ ነው፡፡
Wednesday, 29 January 2014
የኢትዮጵያ መንግስት የግንቦት7 መሪዎችን ኮምፒዩተሮች በዘመናዊ የስለላ መሳሪያዎች ሲሰልል እንደተደረሰበት አንድ አለማቀፍ ተቋም አጋለጠ
ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዝቦችን ደህንነት ከመንግስታት ጥቃት ለመከላከል የተቋቋመው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ተቋም ለእንግሊዝ መንግስት የገቢዎቸና ጉምሩክ መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ “ጋማ ኢንተርናሽናል የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ በአለም ላይ የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ለሚታወቁ አገሮች ኮምፒይተሮችን፣ የሞባይልና የስካይፕ የስልክ ግንኙነቶችን እንዲሁም የኢሜል ልውውጦችን በርቀት ሆኖ ለመከታተል የሚያስችለውን ፊን ፊሸር ወይም ፊን ስፓይ በሚል ስም የሚጠራውን የመሰለያ መሳሪያ ከአውሮፓ ህብረት ውጭ ላሉ አገሮች በመሸጥ ዜጎች እንዲሰለሉና ደህንነታቸው አደጋ ላይ እንዲወድቅ በማድረጉ ምርመራ እንዲጀመር” ሲል ጠይቋል።.......
የታመቀው የኢትዮጵያውያን ምሬት፡ የሕይወት ማሽቆልቆልና በፍርሃት መሽማቀቅ አፋጣኝ መፍትሄ ይሻል
by The Ethiopia Observatory
ኢትዮጵያ በሕወሃት ዘመነ አመራር የታወቀችባቸው ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ብዙ “እንዴ!”የሚይሰኙ ጥሩ አሳቦችም ፈልቀዋል – አፈጻጸማቸው እትይለሌ ቢሆንም። ከነዚህም መካከል መሠረተ ልማት፡ በጤናና በትምህርት መስኮች መሻሻሎች መታየታቸው ወዘተ መልካም ይነገርላቸዋል – የቢል ጌትስን የራስ ተጠቃሚነትና ኢምፓየር ግንባታ ወደጎን ትተን! በዕጦት ደረጃም በሀገራችን የስብዓዊ መብቶች አለመክበር፣ የፍትህ አለመኖርና ለአብዛኛው ሕዝባችን የምግብ ዕጦት ዋና ዋና ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው።
ለምሳሌም ያህል፡ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 30 ስላማዊ ስልፍ የማድረግንና መንግስትን መቃወምን ግልጽ ቢያደርግም፡ እሁድ ዕለት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ለመሰጠት ለመቃወም: ለሚመለተው አሳውቀው ስላማዊ ስልፍ ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ ሲሉ የአዘጋጁ የስማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ጎንደር ውስጥ ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ መንገድ ትግራይ ውስጥም የአረና አመራሮች ሕዝቡን ቀሰቀሳችሁ በሚል ውንጀላ አዲግራት ውስጥ አመራሩና አባሎቹ ክፉኛ ተደብድበዋል – ጉዳት የደረሰባቸውም ሕክምና ለመሻት ተገደዋል። ይህንኑ አስመልክቶ፡ አንዱ ተደብዳቢ መምህር አብርሃ ደስታየሚከተለውን ጽፏል፡
- “ህወሓቶች በተግባራቸው ሊያዝኑ ይገባል። ህዝብን ፖለቲካ እንዲያውቅና ራሱ ከጭቆና እንዲከላከል ለማገዝ በምንሞክርበት ግዜ መንግስት ወደ ተራ የሽፍትነት ተግባር መሰማራቱ የሚያስደምም ነው … እኛ ለህዝብ ነፃነት ነው የምንታገለው። ትግላችን ሰለማዊ ነው።.......
Subscribe to:
Posts (Atom)


