BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!
Thursday, 30 January 2014
በጎንደር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የቅስቀሳ ቡድን አባላት በፖሊስ ታሰሩ፡፡
የጎንደር ነዋሪ ህዝብ የፖሊስ ጣቢያውን በመክበብ የታሰሩት እንዲፈቱ እየጠየቀ ይገኛል፡፡ ጥር 25 2006 ዓ.ም.
የኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለልን ህገወጥነት በተመለከተ በጎንደር መስቀል አደባባይ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ
አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የተጓዘው የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ሉኡካን ቡድን በዛሬው እለት
በጎንደር ከተማ በቅስቀሳ ላይ እንዳሉ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው ሲሆን ጎንደር የገባው ቡድን በጠቅላላ በእስር
ላይ ይገኛል፡፡ .................................
የቅስቀሳው አባላት በጎንደር ከተማ እና በተለያዩ ቦታዎች ቅስቀሳውን እንደጀመሩ የፓሊስ አባላት ፈቃድ ስለሌላችሁ መቀስቀስ አትችሉም ያሏቸው ሲሆን አባላቱም በህጉ መሰረት ማሳወቅ እንጂ ማስፈቀድ የሚጠበቅብን ስላልሆነ
ለሚመለከተው አካል ያሳወቅን በመሆናችን ህጋዊዎች ነን በማለታቸው ፓሊስ በማዋከብና በመደብደብ
ጎንደር ከተማ በሚገኘው ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ መጉላላትና እንግልት እያደረሱባቸው
ይገኛል፡፡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችም ፖሊሶቹን ምን አደረጓችሁ በማለት እና ይህ ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው በማለት
አባላቱን ከፖሊስ ለማስለቀቅ የተቻላቸውን ያደረጉ ሲሆን ፖሊስም ሐይል በመጨመር ህዝቡን በዱላ
በማባረር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የቅስቀሳ ቡድኑን እንዲሁም የጎንደር የፓርቲው መዋቅር አባላትን
ጨምሮ አስረዋቸዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የጎንደር ነዋሪ ህዝብ የፖሊስ ጣቢያውን በመክበብ የታሰሩት እንዲፈቱ
እየጠየቀ ሲሆን ሰልፉ በተያዘለት ቀን እንዲደረግ ለማድረግ ሌላኛው የሉኡካን ቡድን ከአዲስ
አበባ በዛሬው እለት መንቀሳቀሱ ታውቆአል፡፡
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment