ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ዳር እስከ ዳር እንደ ባቢሎን ሰዎች ከመግባባት ወደ አለመግባባት ፣ ከመፋቀር ወደ መቃቃር ፣ ከመከባበር ወደመናቆር ፣ ከአንድነት ወደ ልዩነትና ከኢትዮጵያዊ ህብረት ወደ ክልላዊ ስሜት እንዲያዘነብሉ ያደረገ የጥፋት መንግሥት ነው::
ይህ መንግሥት ቀደም ያሉት ታሪካዊና ወርቃማ ዘመናት በትውልዱ ዘንድ እንዲጠሉ ለማድረግ......
አንዱን ጨቋኝ ሌላውን ተጨቋኝ በማስመሰል ጥላቻን የሰበከ ፍቅርን ያቀዘቀዘ ብሔርን ከብሔር ጎሳን ከጎሳ በማናከስ ጥንት ተጋብቶና ተዋልዶ በሥጋና በደም የተሳሰረውን ሕዝብ በደም ያፋታና ደም ያቃባ ሐሳዊ መሲህ መንግሥት ነው:: ለምሳሌ ጥቂቶቹን እንኳ ብንጠቅስ በደቡብ የጉጂና የደራሳን (ጌድኦን) ብሔረሰብ ፣ የኮንሶንና የቦረናን ብሔረሰቦች ፣ በወለጋ የኦሮሞን ሕዝብ ከአማራና ከጉሙዝ ብሔረሰብ ፣ የጋምቤላንም ሕዝቦች እርስ በእርሳቸው በማጋጨት በሺህ የሚቆጠር ሕዝብ ያስጨረሰ የደም መንግሥት ነው::
No comments:
Post a Comment