BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Friday, 31 January 2014

አባይ፣ ግድቡና ሽኩቻው፡

የህዳሴ ግድብ የመገንባት ሀሳቡ ሲፀነስ ለሀገር ልማት ታስቦ ነው የሚሉ ቢኖሩም አብዛኛው ሰው በዋናነት ለፖለቲካ ፍጆታ ታስቦ የታቀደ እንደነበር ያምናል፡፡
ግድቡ እንዲሰራ ተወስኖ የተጀማመረ ሰሞን መስከረም 2004 ዐ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ግቢ ውስጥ የተካሄደ አንድ ትልቅ የዘርፉ ታላላቅ ሙሆሮች ያደረጉትን ሙሁራዊ ውይይት በአንድ ታላቅ ሙሁር ታድሜ ውይይቱን ተከታትየ ነበር፡፡.........
ቢልዮን ዶላሮች የሚወጣበት ግድብ ብዙ የእርሻ ስራዎችም የማይካሄዱበት ድንበር አካባቢ ከመስራት በዛው ብር ከ5-6 መካከለኛ ለሀይል ምንጭነትም የመስኖ ስራዎችም የሚውሉና ብዙ ግጭቶች የማያስከትሉ ግድቦች በአባይ መጋቢ ወንዞች፣ አዋሽና ሌሎች መስራቱ እንደሚሻል ነበር ድምዳሜያቸው፡፡ እኔም እምነቴ ያ ነው፡፡
የሆነስ ሆነና አሁን ግንባታው ተጀምሮ ወደ 1 ቢልዮን ዶላር ገደማ ወጥቶበት እውነት ከሆነ 30% ገደማ ደርሷል ተብሏል፡፡ ካሁን በኃላ ወደ ኃላ ማለት የለም፡፡ የግድቡ ግንባታ የተነሳበት ሀሳብና ዐላማ ምን ይሁን ምን ዋናው ግድብ ነው፡፡ ግድቡ ፍፃሜ ላይ ማድረስ አለብን፡፡ የግድቡ ተጠናቆ ስራ መጀመር ሁላችንም ይጠቅመናል፡፡ ይህ ሁሉ ወጪ ወጥቶ ወደ ኃላ መመለስ አንችልም፡፡
ግብፆች በህገ-መንግስታቸው የኣባይን ውሃ ማንም አንዳይነካባቸው ብለው በድፍረት ማስፈራቸው( አንቀፅ 44) እንዲሁም ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ እንድታቆም እንዲያስገድድላቸው የተባበሩት መንግስታት መሄዳቸው ይኸ ሁሉ ማንኛውም አማራጭ በመጠቀም ይኸንን ግድብ ለማስቆም ቆርጠው መነሳታቸው ግልፅ አድርጎታል፡፡
ግብፅ ታሪካዊ ጠላታችን ነች፡፡ እንዲህም ሁና ሺ ዐመታት ዘልቃለች፡፡ ለወደፊቱም ይቀጥላል፡፡ ይህንን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ መቸም የለም፡፡
የተለያዩ ተላላኪዎቿን በመጠቀም ዛሬም እንደሁልጊዜው ኢትዮጵያን ለማተራመስና አቅጣጫችንን ለማሳት መሞከሯ ትገፋበታለች፡፡ አንዲያውም ዐይነቱንና መቼቱን መገመት ቢከብድም ግድቡ ላይ የሚደርስ ጥቃት( በቀጥታ ወይም በተላላኪዎቻቸው) እንዳለ ለመገመት ከባድ ምርምር አያሰፈልገውም፡፡
ስለዚህ፡
1. ግብፆቹ የሚያደርጉትን ደባ እንደሀገር፣ እንደህዝብ በንቃት መከታተል አለብን፡፡ የግብፅ ታሪካዊ ጠላትነት ሳንረሳ በማንኛውም መንገዱ( በቀጥታም በተዘዋዋሪም) ሊያጠቁን የሚሞክሩበት እድል ሰፊ ስለሆነ ህዝቡ አካባቢውን በንቃት ይከታተል፡፡
2. ገዢው መንግሰት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራዎች ማድረግ ግድ ይለዋል:
3. ጉዳዩ ከዲፕሎማሲ አልፎ ወደ ሀይል እርምጃ ሊሸጋገር የሚችልበት እድል ሰፊ ስለሆነ ሁለ-ገብ ዝግጁነት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በተለይም ጠንካራ Missile Defense system መገንባት ግድ ይላል፡፡
4. ከኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ሌሎችም ሊመጣ የሚችል ማንኛውም ዐይነት ትንኮሳ በንቃት መከታተል፡፡
ከላይ እንደገለፀኩት ግድቡ ላይ ከአነሳሱ ጀምሮ ብዙ እይታዎችና ተቃርኖዎች ቢኖሩም አሁን ስራው እዚጋ ደርሶ ምንም ዐይነት መሰናከል እንዳይደርስበት በንቃት መከታተል አለብን፡፡

No comments:

Post a Comment