ሰሞኑን በዲያስፖራ የፓልቶክ የውይይት መድረኮች፣ የአጼ ሚኒሊክንና እና ቴዲ አፍሮን በሚደግፉና በሚቃወሙ፣
በመቶዎች በሚቆጠሩ ታዳሚዎች መሃከል ይካሄድ የነበረውን ውንጀላና፣ መከላከልን እኔም ለጥቂት ቀናት እያዳመጥኩኝ
ስከታተል፣ ሁኔታው እንዳሳዘነኝ የገባት ባለቤቴ፣ ወንበሯን ስባ ተጠግታኝ፣ እሷም በእንግሊዘኛ የሚጻፈውን ቴክስት
ለማንበብ እየሞከረች “ሰሞኑን ደሞ ምን ተፈጠረ? ደስተኛ አትመስልም!“አለችኝ፡፡ እኔም ጠቅለል ባለ መልኩ፣ አዲስ
በተከፈተው ”የጄኖሳይድ……..ክፍል” በአጼ ሚኒሊክና በአርቲስት ቴዲ አፍሮ ላይ ይካሄድ ስለነበረው “ዘመቻ“፣
የሰማሁትን በመጠኑ ነገርኳት፡፡ በተላይ በንግግርና በቴክስት ይመላለሱ የነበሩትን አንዳንዶቹን እንክኳን ለሷ ልነግር
ለራሴ መስማት ዘግንኖኝ እንዳላየ ባልፋቸውም፣ ..........
እሷ ግን አጠገቤ ተቀምጣ የሚጻፈውን ቴክስት ማንበብ ቀጠለች፡፡ስከታተል፣ ሁኔታው እንዳሳዘነኝ የገባት ባለቤቴ፣ ወንበሯን ስባ ተጠግታኝ፣ እሷም በእንግሊዘኛ የሚጻፈውን ቴክስት
ለማንበብ እየሞከረች “ሰሞኑን ደሞ ምን ተፈጠረ? ደስተኛ አትመስልም!“አለችኝ፡፡ እኔም ጠቅለል ባለ መልኩ፣ አዲስ
በተከፈተው ”የጄኖሳይድ……..ክፍል” በአጼ ሚኒሊክና በአርቲስት ቴዲ አፍሮ ላይ ይካሄድ ስለነበረው “ዘመቻ“፣
የሰማሁትን በመጠኑ ነገርኳት፡፡ በተላይ በንግግርና በቴክስት ይመላለሱ የነበሩትን አንዳንዶቹን እንክኳን ለሷ ልነግር
ለራሴ መስማት ዘግንኖኝ እንዳላየ ባልፋቸውም፣ ..........
ይካሄድ የነበረው ዘመቻ ሆነ ብለው ነገሩ እንዲባባስና ልዩነቱ እንዲሰፋ ጽንፈኛ አመለካከት በነበራቸው ግለሰቦችና
ቡድኖችም ጭምር እንደታጀበም አልደበኳትም፡፡ አንዱ አጼ ሚኒሊክን ብቻ ሳይሆን ያወግዙና ይከሱ የነበሩት፣ አንዱ
የሌላውን ዘር በወራሪነት፣ በጨካኝነትና በመጤነት የሚካሱና እራሳቸው እዛች ሐገር ውስጥ፣ ከመሬትና ከድንበር ጋር
አብረው ተፈጥረው፣ ተዘርተው እንደበቀሉ፣ የሚያምኑ እንዳሉና፣ የማይፈልጉትን ከአካባቢያቸው እነስወጣለን እያሉ
የሚዝቱና የሚያስፈራሩትን በተደጋጋሚ አንብባ ሲበቃት እራስዋን ነቅንቃ ጥያቄ ጠየቀችኝ፡፡ “እንዴት እነዚህ ሰዎች
ሰሞኑን እንኳን የሱዳንንና፣ የሴንትራል አፍሪካን ሬፑብሊክ እየተካሄደ ያለውን የእርስ በእርስ እልቂት፣ ሕዝቦች ሲፈናቀሉ፣ ሕጻናት
ሳይቀር የሚታረዱበት ዘግናኝ ቀውስ እየተካሄደ ካለበት ሁኔታ መማር አይችሉም? ደግሞስ አንድ ሕዝብ ሆነው አንዱ ከሌላው
በላይ ለምን የባለቤትነት ስሜት ይሰማቸውል? ደግሞስ ከሐገራቸው ወዴት ነው የሚሄዱት? አልገባኝም“ብላ እራስዋን ነቀነቀች፡
እውነትም አንዳንዶቹ እንደፈለጉ የመጣላቸውን የሚናገሩ ናቸው ባይባልም፣ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርተው
ሳይሆን፣ ታሪክን እራሳቸው ሊያምኑ በሚፈልጉበት መንገድ እየትረጎሙ፣ በስሜትና በእልህ በመነሳሳት ለረዥም ጊዜ
መሪዎቻቸው ያስተማሩዋቸውን፣ ተከታዮቻቸው ወደ ተግባር ለመቀየር የሚፈተኑበት ወቅት ይመስላሉ፡፡ ይህንን አደገኛ
አካሄድ ለመከላከልና ስህተቱን ለማሳየት ብዙ ታዳሚዎች በአግባቡ፣ ታሪክ እያጣቀሱ ስህተቱን ሊያመላክቱ ይስተዋሉ
የነበሩትና፣ በተጨማሪ ሌሎችም ሆነ ብለው ይህንን ችግር ለማባባስ፣ በሁለት ቦታ የወገኑ መስለው፣ ችግሩን
የሚያቀጣጥሉ ተላላኪዎች፣ ያባብሳል ብለው የሚገምቱትን ነገር ሁሉ “እሳት ውስጥ እየወረወሩ ሊያጫርሱ ሲራወጡ“
ማየት የሚያያሳዝን ተውኔት ነበር፡፡ ይመታ የነበረው የጦርነት ከበሮ በአማራው ሕዝብ ላይ ያነጣጠረውን፣ መነሳሳት
የሚያበረታታ አደገኛ አካሄድ ነበር፡፡ ይህንን የተሳሳተና ሐገራችንን ሊያፈርስ የሚችል አካሄድ፣ ወደ ሕዝባችን ለመግፋት
እየሞከሩ ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ ስለሆነ ዝም ተብሎ ተንቆ ሊታይ አይገባውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ጉዳይ አስፈጻሚ
እንጂ፣ “ሰንቀው“ የሚልኳቸው ከኋላቸው ሌሎች እንደሆኑ ግልጽ ነው፡፡ አከአገዛዙ ጀምሮ ይህንን መከፋፈል
የሚፈልጉ የሐገራችንን እድገትና መረጋጋት እንዲኖር የማይፈልጉ የአካባቢው መንግስታት ጭምር ከዚህ ተንኮል ጀርባ
በትጋት ቀንና ሌሊት ተግተው ስለሚሰሩ፣ እንደነዚህ አይነት በጥላቻ የታወሩን ቡድኖችን በቀላሉ እንደ መሳርያ
ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ፡፡
ብዙ ለጆሮ የሚቀፉ፣ በሕዝባችን፣ በታሪካችንና፣ በዕምነታችን ላይ ያነጣጠረ ውንጀላ፣ ስድብና፣ ማስፈራራት በስፋት
ይነገር ነበር፡፡ ይህንን ሁሉ የሚያደርጉት በሐገርና በሕዝብ ስም፣ እየማሉና እየተገዘቱ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ አሳፋሪ ውንጀላ
አልበቃ ብሎ አንዱ ሌላውን፣ ከሌላ ፕላኔት እንደመጣ፣ “መጤ“ እያሉ በዓለም ላይ እንደሚካሄዱት አስቀያሚ በዘርና
በሃይማኖት ምክንያት እንደሚካሄዱት እልቂቶች፣ እኛንም ተመሳሳይ እልቂጥ ውስጥ ሊከቱን፣ የማይቆፍሩልን ጉድጓድ
የማይፈጥሩልን አዲስ ታሪክ አልነበረም፡፡ “ለኦሮሞ ሕዝብ እንቆረቆራለን“ ከሚሉ ዘረኛ ምሁሮች የሚነገራቸውን
በማመን የሰሜኑን ክፍል ወገኖቻችንን ከአረብ ሐገር እንደመጡና፣ የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ እውነተኛ አፍሪካዊ እንደሆኑ፣
ለማሳመን የማያጣምሙትና የማይደልዙት ታሪክ አልነበረም፡፡ በተቃራኒውም “ለአማራው እንቆረቆራለን“ የሚሉትም
እንደዚሁ፣ ኦሮሞውን ሕዝባችንን “ከማዳጋስካር ፈልሶ የመጡ ስለሆነ፣ ካላረፉ እናባርራቸዋለን´´ ቅስቀሳ እያካሄዱ፣
ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን እያራገቡ፣ ሕዝባችንን ሊያራርቁና፣ አንድነታችንን ሊንዱ ሲሞክሩ መስማት ያሳፍር ነበር፡፡
የምሰማውን በሙሉ ለባለቤቴ መንገሩ አስፈላጊ ሆኖ ባላገኘውም፣ እነዚህ ክፍሎች በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን፣
“እንደ የመሳፍንት ዘመን“ በዘር ክልል አጥር ወስጥ ተገድበው፣ በጥላቻ ተውጠው፣ የተጀመረው እሰጥ እገባ እየተካረረ
ከሄደ ሊያስከትልየሚችለውን አደጋ፣ ምን መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል አለመገመታቸው እንዳሳሰበኝ አልደበኳትም፡፡
ባለቤቴም “ለእነዚህ ላልገባቸው ሰዎች፣ ለምን ምሁሮቻችሁ ስለ የሰው ዘር ግኝት፣ እድገትና፣ የአሰፋፈር ታሪክ አያስተምሩም?
እንኳን እንናንተ የመጀመርያውና የሰው ልጅ ዘር(ሆሞሳፒያንስ….) መኖር ከጀመረበት ምስራቅ አፍሪካና፣ መካከለኛው ምስራቅ
…..አካባቢ፣ እስከ አሁን ድረስ የምትኖሩ ሕዝቦች ቀርቶ፣ እኛ አውሮፓውያን እንኳን፣ ከናንተ አካባቢ እርቀን የምንገኘው ቀደምት
ሃረጋችን ከእናንተ አካባቢ ነው ብለን ነው የምናምነው፡፡ በመለው ዓለም ተሰራጭቶ ያለ የሰው ዘር፣ መጀመርያ እንደ ሰው መኖር
የጀመረው ከናንተ አካባቢ ለመሆኑ፣ በቂ የአርኪዮሎጂና የሳይንስ መረጃዎች ቀርበው ሁሉም የተስማማበት ነው፡፡ ቦኋላ ነው ቀስ
በቀስ ወደ መላው ዓለም የተሰራጨው፡፡ እኛ ፈረንጆቹ መሠረታችን ከምስራቅ አፍሪካ አባይ ተፋሰስ አካባቢ እያልን፣ እንዴት
እናንተ አንድ ሕዝብ እዚያው ከመሠረቱ ያልራቃችሁ፣ አንተ ከዚህ እሱ ከዚያ መጣ ትባላላችሁ? አረብም ይሁን ማዳጋስካር፣
ባጠቃላይ የዓለም ሕዝብ ከእናንተ አካባቢ ተነስቶ በመላው ዓለም ተሰራጨ እንጂ፣ ማንም ከውጪ ወደ እናንተ የተገላቢጦሽ
የመጣ የለም፣ ሊሆንም የታሪክ እውነታው አይፈቅድለትም“ ብላ ትንሽ አስቃኝ ውይይቱን ቀጠልን፡፡
እኔም እንዴት ላስረዳት እንደምችል ግራ ገብቶኝ፣“ችግሩ እኮ ሳያውቁ ወይም ሳያነቡ ቀርተው አይደለም፡፡ ሁለቱም ወገኖች
ማመን የሚፈልጉት ያለውን ሃቅ ሳይሆን፣ የሚመኙትን ነው፡፡ ዋቢ የሚጠሩትም ሆነ፣ የሚያነቡት ማስረጃ፣ ለነሱ ተመችቶ ማሸነፍ
የሚችሉበትን እንጂ ቀናነትማ ቢኖራቸው፣ አንቺ እንዳልሸው ከሰው የፍጥረት ዘመን የመጀመርያ ታሪክን ማጣቀስ አሻፈረን
ብለው፣ ከአስራ አምስተኛው የኦሮሞ መስፋፋት ዘመንና፣ ከአስራ ዘጠነኛው ዘመን ከአጼ ሚኒሊክ የሐገር ግንባታ፣
(ከዘመንና ከታሪክ፣ ወገብ) ላይ የሚጀምሩት ወደ መስማማት እንዳይቀርቡ ነው፡፡ ከተስማሙ እኩል መብት ሊኖራቸው ስለሆነና፣
ሁለቱም ወገን፣ ሥልጣንንም ሆነ ጥቅምን ለራሳቸው ማዳላት ስለሚፈልጉ፣ ላለመስማማት ነው የሚያካሄዱት ክርክር ፡፡ ከአአዳም
የመጀመርያው አባታችን ጀምረው ሁላችንም የአንድ ግንድ ዘር ነን ብለው መስማማት ሲገባቸው፣ አንዱ ከአብረሃም ሌላው
ከኢስማኤል፣ አንዱ ከሰለሞን፣ ሌላው ከገዳ…ወዘተ እያሉ በታሪክ ወስጥ እየተደበቁ የግል ፍላጎታቸውን ሊጭኑብንና ያረገዙትን
ጥላቻቸውንና፣ ዘርኝነታቸውን እንድንቀበላቸውና በነሱ የጥፋት ጎዳና እንድንተባበር ነው የሚጥሩት፡፡ ይሁንና ቀድሞ እንደነገርኩሽ
ይህንን የነዚህን አክራሪዎች ስሜት አብዛኛው የኦሮሞው ወገናችንም ይሁን የአማራ፣ የትግሬውም ይሁን የጉራጌው ሕዝባችን
አይጋራቸውምና አትስጊ“ ብዬ ጉዳዩን በቀላሉ ላስረዳት እንደማልችል ገብቶኝ ውይይቱን ዘጋሁት፡፡ በእርግጥ እኛ አሁን
ያለንበት ሁኔታ ፈረንጆች ከመቶዎች ዓመታት በፊት ያለፉበት መንገድ ቢሆንም፣ የአሁኑ ትውልድ አፍሪካውያኖችንን
በጥቅሉ የሚመለከቱት “በጎሳ፣ በዘር፣ በድንበር፣ በግጦሽ፣ በእምነት ልዩነት“ እንደምንጣላ ያውቃሉ እንጂ፣ የዘር ጥላቻ
ሲጦዝ፣ እራስን ከሰውነት ደረጀ ዝቅ አድርጎ አዕምሮን እንዴት ሊያሳውር እንደሚችል ብዙዎቹ ሊገባቸው አይችልም፡፡
ችግሩን ለባለቤቴ ቀለል አድርጌ ለማስረዳት እንደሞከርኩት አልነበረም ውስጤ የተሰማኝ፡፡ በመገረም፣ በሃዘን በብስጭት
ነበር የተወሰኑ ቀናት አልፎ አልፎ አዳምጣቸው የነበረው፡፡ ክፍሉን ከፍተው የተቆጣጠሩት በጥላቻ የታወሩ
አክራሪዎችም ቢሆኑም፣ አልፎ አልፎ በጎ አመለካከት የነበራቸውና፣ አስታራቂ ሃሳብ ሊያቀርቡ የሚሞክሩ፣ገንቢ
አስተያየት የሚሰጡ፣ ሚዛናዊ(ሞደሬት) አቀራረብ የነበራቸውና፣ ነገሩን ለማብረድ ይጥሩ የነበሩ፣ የቁርጥ ቀን የሐገር
ልጆች ስለነበሩ፣ እስከ ተወሰነ ደረጃ አልፎ አልፎ እየከበደኝም ቢሆን እየገባሁ ማዳመጤንና፣ በቴክስት መሞነጫጨሬን፣
በልቤ የማስበውን ለሚናገሩ አውራ ጣቴንና፣ በነጻ የሚቀጠፈውን የፓልቶክ አበባ ከመበተን አልቦዘንኩም ነበር፡፡ ከነዚህ
የዘር ጥላቻ ከተናወጣቸው ሰዎች ጎን፣ የመከፋፈሉን ሁኔታ በደንብ ለመጠቀም፣ የኦሮሞ ተቆርቋሪ መስለው አማራውን
የሚሳደቡና፣ የአማራው ደጋፊ መስለው ኦሮሞውን የሚሳደቡ፣ ኦሮሞው መጠራት በማይፈልግበት ስምና፣ አማራውን
ያበሳጫል ብለው በሚገምቱት ስድብ፣ ሁሉንም ዘር የሚሰድቡ፣ ሦስተኛና አምስተኛ እረድፎች በትጋት ለማጣላት
ሲሞክሩና፣ በሚነደው እሳት ላይ ቤንዚን ሲያርከፈክፉ ማየትና ማዳመጥ የሚያሳፍርና የሚያሳዝን ነበር፡፡ እነደነዚህ
አይነት የታመሙ ሰዎች መሃከላችን እንዳሉ ብንገምትም፣ አንዳንድ የምሰማቸውና የማነባቸው ስድቦች ከግምቴ በታች
በጣም ዝቅ ስላሉብኝ፣ ከሁለት ምሽት ማዳመጥ ቦኋላ፣ እራሴን ከዛ ሰፈር አገለልኩኝ፡፡
ይህ መረን የለቀቀ የጅምላ ስድብና ማስፈራራት፣ በምንም አይነት ሚዛን፣ በውይይት ወይም በመወቃቀስ መስፈርት
ሊቀመጥ የማይችል አጸያፊ የጥላቻ ዘመቻ ስለነበረ፣ በመጀመርያ ማዘን ያለብን እንደ እነዚህ አይነት በጥላቻ ለታወሩና፣
በምንም ነገር ውስጥ፣ በጎ ነገር ማየት ለሚሳናቸውን ሰዎች ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ከዚህም ትልቅ ትምህርት
የምንወስደው፣ ዘረኝነት ከሮ ሲጦዝ፣ የሰው ልጅ ምን ያህል ከሰውነት ደረጃ ዝቅ እንደሚልና፣ ጥላቻና እልህ፣
የማመዛዘኛ ህዋሳቶቻችንን እንደሚያመክን ነው፡፡ ዘረኝነት ልክ እንደ “ሴክት“ እራሳቸውን ከውጪው ነባራዊ ሁኔታና
ክስተት ገድበው፣ በግል ማሰብንና ማመዛዘን አቁመው፣ መሪዎቻቸው የሚነግሯቸውን ብቻ እንደ አንድ ሰው ሆነው
እየተቀበሉ፣ መልሰው ያንኑ እንደወረደ ሌላውን ለማሳመን የሚለፉት፡፡ በሰለጠነው ዓለም ግለሰቦች እዚህ ደረጃ ላይ
እንደደረሱ በቤተሰቦቻቸውም ሆነ በወዳጆቻቸው ምልክቶቹን ሲያዩዩ፣ በእንደዚህ አይነት በሽታ የተጠቁትን እራሳቸውን
እንዳይጎዱም ሆነ ኅብረተሰቡን ለመከላከል፣ አስቸኳይ እርዳታ ነው ገለል ተደርገው እስከሚድኑ የሚሰጣቸው፡፡

”ሁሉም አይነት አክራሪ መስመሮች ይጎዱናል!!! ” ላይ የተወሰደ
ከብስራት ኢብሳ (ሆላንድ)
ከብስራት ኢብሳ (ሆላንድ)
source - http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2014/01/Minlik24-01-14.pdf
No comments:
Post a Comment