BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Saturday, 25 January 2014

በትግላችን ውስጥ ሊኖር የሚገባ ቅደም ተከተል....... !!!

አምሳለ አለሙ(ከኖርዌይ)
ይህን ለመፃፍ ያነሳሳኝ  በተለያዩ የሕዝብ መገናኛ መስኮቶች የምመለከታቸው የሕዝብ እይታዎች ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን እየመራ ያለው የወያኔ መንግሥት  ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ሊያጠፋ የተነሳ መንግሥት መሆኑን ሁላችን የምናውቀው የአደባባይ ምሥጢር ነው። ነገር ግን «የሕዝብ መከፋፈል ለአግዛዝ ያመቻልና» ሁሉም በየአቅጣጫው ላለው ተጠሪነት ኃይሉን ሲከፋፍል ኢህአዲግ የግዞት አገዛዙን ዘመን ያራዝማል።
ኃይላችንን በሙሉ በጎሳ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ድርጅት መለያየት ላይ ያደረግን በሙሉ ለምንከውናቸው ቀዳሚ ተግባራት ቁንጮዋ ሃገር ናትና ቆም ብለን ልናስብ ይገባናል። «ቅድሚያ መቀመጫዬን» እንዳለችው የኢትዮጵያ ህልውና ከሌለ እንደ ዳቦ ተቆራረሳ ካለቀች ነገ በማን ላይ ቆመን ነው ይህን ሁሉ ለመከወን የምንችለው?» ብለን በጥልቅ ልናስብ ይገባናል።  ልናስቀድም የሚገባን የትግል ምዕራፍ የሃገራችን ሕልውና ተከብሮ የመኖሩ ጉዳይ ነውና።........



የኢትዮጵያና የሕዝቦችዋ ሕልውና መዝባሪ የሆነው ኢሀአዴግ በየእለቱና በየሰዓቱ ለሚፈበርካቸው እቅዶቹ ተፈፃሚነት የሕዝቡን ልቡና በተለያየ ሁኔታ መከፋፈልና መስለብ ቅድሚያ ተግባሩ ነው። ይህንንም ባሳለፍናቸው ሁለት አሥርት ዓመታት ለትምህርት ያይደለ በቅጣት እያንገሸገሸን ተግተነዋል።
የኢህአዲግ ሤራው የሚጀምረው ሕዝብ ወደ መንግሥት ድክመት እንዳያስተውል ከማድረግ ነው። አስቀድሞ ተግባብቶና ተከባብሮ የሚኖርን ሕዝብ በጎሳ ከፋፈለ፣ በአንድነት የሚኖርን ሕዝብ በልዩነት ማዳበር ጀመረ። በልዩነት ያፈላውን ችግኝ ለመቁረጥ እንዲመቸው አራርቆ ተክሎ በማግስቱ የያዘውን እቅድ «መብት እስከመገንጠል ድረስ» እቅዱን በተግባር ላይ አዋለ።

ይህ አካሄዱ ቀድሞ ገብቶአቸው «ለምን?» የሚል ጥያቄ ያነሱትን ብቻ ሳይሆን ሊያነሱ ይችላሉ ያላቸውን ሁሉ በማፈን በማሰቃየትና በመግደል የእልፎችን ቤት ከነመሠረቱ መንግሎ ጣለ።  «ለማያውቅሽ ታጠኚ» እንዲሉ ለነጮቹ የዲሞክራሲን ጭንብል ለብሶ ሕዝቡን ማቅ አልብሶት እንዳይበራ አጥፍቶት እንዳይሞቅ አክስሞት እስካሁን አለ።

ማብቂያ በሌለው ጥፋቱ እንደ እርሱ ሃገር በመሸጥ ያላለፉትን የአኩሪ መሪዎችን ንፁህ ታሪካዊ ውለታን በጥላሸት መለወስና ተነባቢነቱን ማበላሸት ነው። ይህንንም ከዳር ለማድረስ መዘውር አድርጎ የሚጠቀመው ይህንኑ ሕዝብ ነው። 

«መልካም ሥራቸውን» በየእገሌ ጎሳ ይህንን ጎሳ በደለ በማለት ሕዝቡን እርስ በርስ በማበጣበጥ፣ የሕዝቡ ዓይኖች ወደ እርሱ ችግር ተመልክተው ጥያቄ ለማንሳት እንዳይፈናፈን መያዣው የጥበብ መንገድ ነው።
ለሃገር ለድንበራቸው ሲሉ መሠረቱ በደማቸው ተቦክቶ፣ በአጥንታችው ሳጋን ስገው፣ ሥጋቸው ግድግዳ ሆኖ ያቆይዋትን እናት ሃገር ሸንሸኖ መቸርቸር ከጠላትም ያለፈ «የጀግኖች ደመኛ» መሆን እንጂ.......። 

ጀግና መሆን ባይቻል የጀግኖችን ሥራ መዘከርም እኮ ታላቅነት ነበር...። 

ለሃገርና ለሕዝብ ህልውና ዋጋ የማይሰጠው ኢህአዲግ ዛሬም ሃገር ቆርሶ ለመሸጥ መደራደሩን፣ እስከ ግዛቱ ዘመን ፍፃሜ ድረስ ህልውናዋን ለማጥፋት የማይተኛውን እንዲሁም ሌላኛውን ተፈፃሚ እቅዱን እድል ለማሳጣት ነው ለትግላችን ቅደም ተከተል የመኖሩ አስፈላጊነት።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!!





No comments:

Post a Comment