BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Wednesday, 29 January 2014

ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወጣት ክንፍ ድርጅት(ኢወክንድ) የተሰጠ መግለጫ


ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወጣት ክንፍ ድርጅት(ኢወክንድ) የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ወጣቱ ትውልድ ራሱን ከፅንፈኞች ማራቅ ታሪካዊ ግዴታው ነው !


ከጠባቦችና የግንጠላ አራማጆቸ ጎራ እንደሚስተጋባው ከንቱ ታሪክ አገራችን ኢትዮጵያ በድንገት የዛሬ መቶ አመት የተከሰተች ሳይሆን በብዙ ዘመናት የዜጎች መስዋዕትነት የተገነባች አገር ናት።........
ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ለማድረግ የብዙ ሚሊዮንና የአያሌ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ህይወት ተገብሮባታል። ይነሰም ይብዛም፣ ይጉላ ይደብዝዝ፣ ሁሉም ህዝብ ለዚያች አገር ግንባታ አሰተዋፅኦ አድርጉአል። በሌሎች አገሮች ታሪክም እንደተከሰተው ሁሉ በኢትዮጵያም ታሪክ ጦርነት የሀገር ግንባታው ሂደት አካል ሆኖ ተገኝቷል። በሂደቱ ለጠፋው ህይወትና ለደረሰው በደል የዛሬው ትውልድ ከቶም ተጠያቂ ሊሆን አይችልም ብሎ ኢወክንድ ያምናል ።
የዘመናት በደልና ቁርሾን ዛሬ ህይወት ሰጥቶ በማናፈስና በማመርቀዝ የህዝብ ግኑኝነትን፣ አነድነትና፣ ትስስርን ለማፍረስና ህዝብን እርስ በርስ ለማናቆር መጣሩ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው። ለነገሩማ ዛሬ ህፃን፣ ሽማጊሌ፣ ሴት ፣ወንድ ሳይለዩ በጭፍን ጥላቻ የሚጨፈጭፉ የሚያርዱና ገደል የሚጥሉ ሁሉ ያለፈ ታሪክን ገድል በመጥቀስ ከወንጀላቸው ነፃ ሊሆኑ አይችሉም።
ለሀገር አንድንትና ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር የሚካሄደው ትግል ክግቡ እንነዲደርስ ከተፈለገ ወጣቱ ትውልድ ጠባብ ብሄረተኝነትና ትምክህተኝነት የአንድ ሳንትም ሁለት ገፅታዎች መሆናቸውን ተረድቶ መራቅና አንድነቱን ለመጠበቅ መታገል ግዴታው ነው። በአንድ ፅንፍ የሚታየው ጎጂ አቋም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ክዶ በመብት ሽፋን ግንጠላን አያራገበ በአሶሳ፤በአረካ፤ በአርባጉጉ፤ በሎቄ፤ በአሰቦት በበደኖ ፤በጋምቤላ፤ በቡርጂ፤ በበቦረና፤ በጌዲዎ፤ወዘተ የተከሰቱ እልቂቶችን አስከትሏል። በዚህ ጎጠኛ ቡድንና በመሰሎቹ እየተራገበ ያለው የአንድንት፣ የዘርና የሃይማኖት ጥላቻ እንዲሁም የክፍፍል እሳት ታሪክን እየካደ የዕርስ በርስ ግጭትን እያስፋፋ የአንድነትንና የአብሮነትን ስረ- መሠረት እየነቃቀለ ህዝብን በብሄረሰብ፣ በክልል እና በሃይማኖት ደረጃ በልቶና ሸንሽኖ አሽመድምዶ ለማጥፋት የሚደረግ የፀረ-አነድነት ሴራ ነው።
ይህ የፀረ- ኢትዮጵያ ጽንፈኛ አቋም መገንጠልና ማስገንጠል በሚለው ወያኔያዊ ተግባሩና መፈክሩ ይገለጣል። የሕዝብን ማንነትና የቆየ የጋራ ታሪክ ይሰብራል። በኢትዮጵያዊነት ላይ ሳይታክት ይዘምታል። ዘረኝነትን እንደፀጋ ተላብሶ፤ ለዴሞክራሲ አፍአዊ ግብርን እየከፈለ፤ ክፍፍልንና ጥላቻን ያነግሳል።
ሌላኛው ፅንፋዊ አቋም ደግሞ ራሱን እንደ የአንድነት አባውራ ሰይሞ በጥቅል መፈክር ተጨባጭ ሁኔታን እየካደ በህሊናውም በጆሮውም ላይ የተኛና ለውጥ ፈላገውን የህብረተሰብ ክፍል እያወገዘ ህዝቡ ምን እንደሚያስፈልገው እኛ እናውቅለታለን በሚል የወያኔን የጥላቻ ፖለቲካ በመገልበጥ አንድን ህዝብ በጅምላ እያወገዘ ፈለግሁት የሚለውን አንድንተ ማጅራት ይመታል። በጎጠኞችና በጨቋኞች ላይ እንደመዝመት ፈንታ ለጭቆና መፍትሔ የሚሹትንና መብት ይከበር ያሉትን ክፍሎች በምሬት ያወግዛል። ስለሆነም ሁለቱም ከፋፋይና ጎጅ ፅንፎች ናቸው።
የሀገር አንድነትን ክግዛታዊ ክልል ባሻገር ከህዝብ ጥቅምና አንድነት ጋር በማዋሀድ ከገለፅነው የጠባቦቦች መጠቀሚያ የሆነውን የጥላቻ አከርካሪት ልንሰብረው እንችላለን። ለሀገር አንድነት የሚደረገው ታሪካዊ ገድል ከብሔርተኝነት ጋር መፋጠጡ የማይቀር ሀቅ ነው። ስለዚህም ኢትዮጵያ እንድትዳከምና እንድትጠፋ ማለትም ህዝቧ በጎሳና በሃይማኖት ተከፋፍሎ ወደ ዕርስ በርስ አስከፊ ጦርነት እንዳይገባ የታሪክ ባለአደራ የሆነው ኢትዮጵያው ወጣት ትውልድ ቀን ቀጠሮ ሳይሰጥ መደራጀትና መታገል ይገባዋል።
ሀገርን ከጥፋት ለማዳን እየተደረገ ያለው የትግል ተልዕኮ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው አንድነትን ከዲሞክራሲያዊ መብት ጋር አጣምረን ይዘን ከተገኘን ብቻ ነው። የምንታገልላት ኢትዮጵያ የሁሉም ብሔረሰብ መብቱ፤ ቋንቋው፤ ባህሉ ሃይማኖቱ ተከብሮለት፣ ዴሞክራሲ በተጨባጭ እውን ሆኖ፤ የሲቪክ መብቶች ሁሉ ተከብረው ለዜጎች ሁሉ እኩል ሀገር ሆና ለምትገኝ ኢትዮጵያ መሆኑ በግልፅ ሊቀመጥና ሊታመንበት ይጠበቃል።
ኢ-ወክንድ ዛሬም እንደትናንቱ ብዙሀኑ በጋራ ለኢትዮጵያ ህልውና ለመታገል ዝግጁ ናቸው ብሎ ያምናል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ህያው ሆነው ያሉና የሚቀጥሉ ናችው። ኢሕአፓ ወክንድ የብሔረስብ፣ የሃይማኖትና የፆታ ልዩነት ለማይከሰቱባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በጋራ እንታግል ብሎ ጥሪውን ሲያስተጋባ የሀገር አንድነትን ለማስጠበቅ ጠንቅ የሆኑትን ጠባብ ብሔረተኝነትንና ትምክተኝነትን አምርረን እንታገል ከሚል ጭምር ነው።
እናችንፋለን !
ጥር 2006ዓ.ም

No comments:

Post a Comment