BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Thursday, 30 January 2014

የተጋረደ የማይለቅ በጥቅም የታወረ የፖለቲካ ጭፍንነት ከየትኛው ...ወደ የትኛው የአደጋ ቀጠና እያመራን ነው???


የተጋረደ የማይለቅ በጥቅም የታወረ የፖለቲካ ጭፍንነት ከየትኛው ...ወደ የትኛው የአደጋ ቀጠና እያመራን ነው??? 


ምንሊክ ሳልሳዊ:- ስሜታዊ እና በጥቅም የታወሩ የፖለቲካው ብስለቱ ያሌላቸው እንደመሰላቸው የሚጓዙ እና ላም ባልዋለበት ኩበት ለመልቀም 

የሚዳዳቸው የተጋረዱ እውር ካድሬዎች ሃገሪቱን እና የሃገሪቱ እውነታ በማድበስበስ ህዝብን እያጭበረበሩ በመኖር ላይ መሆናቸውን ስንመለከት 

አገራችን ከየትኛው ወደ የትኛው የአደጋ ቀጠና እያመራች መሆኑ መገንዘብ አያዳግትም::.........

በገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች በኩል የምናየው ያልበሰሉ ካድሬዎች መበራከት አገሪቷን አደጋ ውስጥ እየከተታት መሆኑን ሲታወቅ በስልጣናቸው መከታ በመሆን እና በታገሉት የመስዋትነት ልክ ትእቢት በመሞላት ከመንግስት እና ከህግ በላይ የሚያላዝኑ ባለስልጣናትን መሸሸጊአ በማድረግ 

የጀመሩት የጥቅም ዘረፋ እንዳይጓደልባቸው በጭፍን የፓርቲ ካድሬነት የሚገሰግሱ ሳያውቁት የሆዳቸውን መሙላት ተከትለው የሚያጨበጭቡ 

በርካታ ዜጎችን ሃይ የሚል መንግስት መጥፋቱ አሁንም በድጋሚ ያለንበት የአደጋ ቀጠና እየሰፋ መምጣቱን ያመለክታል::

ልማትን ተገን አድርገው ፓርቲውን ብርሃናዊ እያሉ ወደ ጨለማ የሚወስዱ እና ሃገርን ወደ ገደል የከተቱ የገዢው ፓርቲ አባላት የአመራር እጦት 

እና የአስተዳደር ብልሹነት በገሺዎቹ ውስጥ መከሰቱን እና የጭፍንነት በሽታ መስፋፋቱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል::በሃገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ሂደት በሚዛናዊ መልክ መመልከት ያቃታቸው የህዝብን ብሶት እና ድምጽ መስማት የተሳናቸው አመራሮች/ባለስልጣናት የፈጠሩት የካድሬዎች ትንንሽ ቡድን ሃገሪቱዋን ወደማትወጣበት አዘቅት ስለከተታት ማጣፊአው አጥሯቸው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ላይ ይገኛሉ::እነዚህ 

ፓርቲያቸውን እና መንግስታቸውን ገፈታትለው ህዝብን አስቀድመው ወደ ጉድጓድ የጨመሩትን የሃገር ደህንነት እና እድገት ማሞካሸት እና ማድነቅ 

ብቻ የሚመስላቸው ነገን የማይመለከቱ አካላት የሚቆጣጠራቸው በመጥፋቱ የተቦረቦረች ሃገርን ወደ ዝግምተኛ ባዶነት ቀይረዋታል::

ተቆጣጣሪ በማጣታቸው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ከየፕሮጀክቱ በመዝረፍ የራሳቸውን የዘራፊ ማፊያ ቡድን በመገንባት ህዝብን 

እያስለቀሱ በአገሪቱ ስንት መንግስት እና ስንት ህግ አለ እስከሚባል ድረስ ትዝብት እና ጥላቸ ውስጥ የወደቁ ካድሬዎች ድክመቶቻቸውን ይዘው 

ሃገሪቱን ካለችበት የፈንጂ ወረዳ ወደባሰ የፈንጂ ወርዳ ከተዋታል ሊታሰብበት ይገባል::


ምንሊክ ሳልሳዊ:

No comments:

Post a Comment