BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Thursday, 23 January 2014

የወቅቱ አራት ስህተቶች............


አንድን ችግር ለመቅረፍ የችግሩን ምንነትና መንስኤውን በሚገባ መረዳት ይገባል። ሰው ታሞ ወደ ሃኪም ቤት ሲሆድ ምኑን (ምን ላይ) እንደሚያመው ማወቁ አንድ ነገር ነው። ሆዱን እየቆረጠው ራሴን እያዞረኝ ነው ብሎ ለሐኪም የሚነግር ከሆነ ከሐኪሙ መፍትሔ የማግኘት ዕድሉ በጣም የመነመነ ነው። ከዚህም በላይ ሐኪሙ ለገንዘብ ብሎ ወይም አያውቅም ላለመባል (ለክብሩ ብሎ) ወዘተ… በጥርጣሬ ብቻ የሌለበትን በሽታ እንዳለበት አድርጎ ሊያስብና ያማይሆን መድሃኒት ለመስጠትም ያበቃው ይሆናል። .....
  • በአገርን ላይ የሚመጣን ችግር በሚመለከትም ይህን መሰል ነገር ሊያጋጥም ይችላል። ደርግ ከሚወጉት ቡድኖች በብዙ ነገሮች እየበለጠ ለሽንፈት በቅቶ አገራችንንም ለውድቀት የዳረጋት የገጠመትን ችግሮች በትክክል ካለመረዳት፣ ከሚዋጉት ቡድኖችና ከውስጡ ለሚመጡ ችግሮችን ተገቢ ያልሆኑ መፍትሔዎችን በግብታዊነት ስለሚወስድ ለሽንፈት መዳረጉን እናስታውሳለን። አንድ የኤርትራ የሽምቅ ውጊያ መሪ ደርግ በአንድ ወቅት በምርጥ ጀኔራሎቹ ላይ የወሰደውን የማስወገድ (የመግደልና ከማዕረግ የማውረድ) እርምጃ “በትልቋ መርከብ ላይ ትልቅ ሽንቁር መፍጠር” ብለው ገልፀውታል። ሰውየው አክለውም በውቅያኖስ መካከል ከማዕበል ጋር የምትታገል መርከብ ከተሸነቆረች መቼ ትሰጥማለች የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ቀላል ባይሆንም መስጠሟ አይቀሬ መሆኑን ግን በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል ሲሉ ገልፀውታል። እኝህ ሰው ይህን ሲናገሩ የመንግስቱ ኃይለማርያም አመራር የፈጠራቸው ተደጋጋሚ ስሕተቶች ለነሱ (ለሻእቢያና ለወያኔ) ድሎች ወሳኝ የሆነ ጠቀሜታ እንደነበራቸው ለማስረዳት ነው።
    በዚህ ዘመንም የዚህ አይነት ስህተቶች ማለትም ችግሮችን በደንብ ካለመረዳት በተሳሳተ ጎዳና በመሄድ ከችግሩ ለማመለጥ ሲሞከር ማየት የተለመደ ነው። ይህ ነገር የወያኔ ጉጅለን በሚታገሉና በሚቃዎሙ የኢትዮጵያ ሚዲያዎችና ተቃዋሚ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ይታያል። አንዳንዴ ይህ ስህተት ህዝብንም ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ሲመራ ይታያል።....... በዚህ ወቅት አራት ስህተቶች ጎለተው በመታየት ላይ ያሉ ይመስለኛል። ለመመካከርና ለመግባባት ይረዳሉና ለመወያየት ባቀርባቸው መልካም ነው ብዬ ስላሰብኩ እንደሚከተለው አቌባቸዋለሁ። ከተሳሳትኩ ለመታረም ዝግጀ ነኝ እያልኩ።
    ስህተት ቁጥር ፩- የወያኔው ቡድን ድሮ በገባው ቃል መሰረት መሬት እየሰጠ ነው።
    ወያኔ ለስልጣን እስኪበቃ የመገንጠል አላማን አንግቦ ሲዋጋ እንደነበር በተደጋጋሚ ከዘዚህ ቡድን ተለይተው የወጡ ሰዎች ሲናገሩ ሰምተናል። በ1981/82 ትግራይ ነፃ ሆናለች እንገንጠል - አይደለም - ኢትዮጵያን መቆጣጠር አለብን በሚል ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቶ ብዙ ሕይወት ቀጥፎ የወያኔው አላማ ተቀይሮ የኢትዮጵያ ገዥ ለመሆን እንደበቃ ይታወቃል። ስለዚህ ቢያንስ እስከዚህ ጊዜ ድረግ ወያኔ የመሬት ግብር እሰጣለሁ ብሎ ለመደራደር ፍላጎት ይኒረዋል ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር ነው። ለምን ቢባል አጀማመሩ ላይ በይፋ ያነገቡት አላማ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ ከኤርትራ ጋር ተዋህዶ መጓዝ ወይም ራስን ችሎ ኖር የሚል ነበር። ቆየት እያለ ግን የአቶ ኢሳያስ ቡድን ኤርትራና ትግራይን በአንድ አገር ማየት በሚለው አባባል ላይ ‘የት እንተዋወቃለን’ የሚል አይነት ማብጠለጠል ስላሰሙ የትግራይ ሪፓብሊክን መመስረት የወያኔ አላማ ሆኖ ዘልቋል።
    ከዚህም ሌላ በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ ሱዳን ውስጥ በነበርን ሰዎች ላይ ከፍተኛ ሁከት ተጋርጦብን ነበር። ይህ የሆነው የሱዳን መንግስት የኔ ነው ወደሚለው ምድር በመተማና በሁመራ በኩል ጦር አስገብቶ ተቈጣጥሮት ስለነበር፣ የሱዳን ገበሬዎችም ጦራቸውን ተከትለው ገብተው መሬት እያረሱና ደን ጨፍጭፈው ከሰል እያከሰሉ ስላስቸገሩ ነው። በዚህ ጊዜ መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ጦር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሶ ሱዳኖች ሲጨፍሩብን ነበር፤ ቆየት ብሎ ግን የኢትዮጵያ ጦት በጀርባ በኩል ገብቶ ባልታሰበ ሰዓት የሱዳንን ጦር ከበቦ ስለደመሰሰው ሱዳን ውስጥ በነበርን ሀበሾች ላይ ከፍተኛ ችግር ተፈጥሮ ነበር። ያገኘን ሰው ሁሉ ይደበድበን ነበር፣ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ስንሄድም እኛው እንታሰር ነበር፣ ሂድ ውጣ የሚለን ሱዳናዊ በዝቶ ነበር። የዚያን ጊዜ ጦርነት በትክክል የመሬት ወይም የድንበር ጥያቄን የተንተራሰና መሬታችንን የወሰደውን የሱዳን ጦር የደመሰሰ መሆኑን በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ሰምተናል።
    ታዲያ አቶ መለስ ምን ዞረባቸውና ራሳቸው ተየተዋጉለትን መሬቱ የሱዳን ነው ብለው ለመከራከር በቁ ብለን እንጠይቅ። አንደኛ አቶ መለስ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ፍቅር ኖሯቸው ባያውቅም ከ1997 በኋላ (ይህን ሕዝብ አታልየዋለሁ፣ ቸ ጉቬራ ሆኛለሁ ብለው ተስፋ አድርገውበት በነረበት ወቅት አፈናውን ላላ አድርገው ባካሄዱት ምርጫ ሽንፈትን ከተከናነቡ በኋላ) ይበልጡን ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ጠላት ሆነዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኤርትራ ውስጥ ያሉና የታጠቁ ተቃዋሚዎቻቸው ሊመጡ የሚችሉበት ዋናው መንገድ በሱዳን ነውና ይህን ለመግታት ለሱዳን የእጅ መንሻ ማቅረብ አለባቸው። ግንቦት ሰባት ቁርጡን በይፋ ሲናገርና ረቂቅ ጭንቅላት ያላቸው ምሁራን ቡድኑን መምራታቸው ሲሰማ የወያኔ ጉጅሌና ጭፍሮቹ በስጋት ስለጠናጡ የአቶ መለስ ወራሾች በፊርማቸው መሬት ለማስረከብ ወደ ሱዳን ተሯሯጡ።
    ስህተት ቁጥር ፪- ምርጫ ሲመጣ ወያኔ ተሸበረ።
    ወያኔ በምርጫ ይሸበራል ማለት ዞር ብሎ ካለማየት የሚመጣ ስህተት ነው። የወያኔው ቡድን ምርጫን ወደ ዋጋ ቢስ ድራማነት በመቀየር የተካነ ቡድን ነው። አይን ባወጣ ማጭበርበር የፈለገውን ያደርጋል። ሕዝቡም ይህን ያውቃል። በ2002 በተካሄደው ምርጫ ድምፅ መስጠት የሚቻለው ‘የኤክስ’ ምልክት በማድረግ ወይም በእጣት በመፈረም ነው የሚል ደንብ በመጨረሻ ሰዓተ ላይ አውጥቶ ነበር። ይህ ደንብ በወያኔ በሚዲያዎች ከተነገረ በኋላ በየሰፈሩ በካድሬዎች አማካኝነት ከዚያም ጥርጣሬ በገባቸው ሰዎች ተቃዋሚን የመረጠ ‘በአሻራው’ ይታወቃል፣ ይደረስበታል፣ ይታሰራል የሚል ወሬ በመንዛት ሽብር ተፈጥሮ ነበር። ከዚህም አልፎ በምርጫ ቦታ ‘ኤክስ’ ማስቀመጫ እስክርቢቶ እንዳይኖር በማድረግ አሻራን ብቻ ጥቅም ላይ በማዋል ያሻውን ፈፅሟል። ከዚህ በኋላም ያሰኘውን ያደርጋል። የምርጫ ታዛቢዎችን በሚመለከት ለሱ የሚመች አሰራር በመተብተብ፣ ተቀናቃኝ ተወዳዳሪዎችን ሕዝባዊ መድረክ በመነገፍ፣ ካስፈለገም በመግደል ምርጫውን ይቆጣጠራል። የቀጣዩን ምርጫ ውጤት ከፈለገ 100% አድርጎ ‘ምን ታመጣለህ’ ይላል ወይም 70% እና 80% አገኝቼ አሸነፍኩ ብሎ ‘ሻል ያለ ምርጫ አደረገ’ ተብሎ እንዲንጨበጨብለት ያደርጋል። አዎን ፈረንጆች ዲሞክራሲ እያበበ ነው ብለው ያንጨበጭባሉ። 
    ስህተት ቁጥር ፫- ወያኔ ፈረንጆችን ለማታለል ምርጫ ያካሂዳል።
    ይህ የተለመደው ስህተት ነው። ፈረንጆች አይታለሉም። ሁሉን እያወቁና ነገሮችን ሁሉ ከነሱ ግብ አንፃር እያዩ የተታለሉ መስለው ሊታዩ ይችላሉ ወይም ሃሰተኛ ምስክር ሆነው ቁጭ ይላሉ። አጭበርብሯል ቢሉ እንኳ ባጭበረበረ ቡድን (መንግስት) ላይ ሊወሰድ የሚገባውን እርጃ አይወስዱም። 
    በ1997 ምርጫ የተከሰቱ ሁለት ነገሮችን እንዘክር። ከአሜሪካ ከመጡ የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች አንዱንና ተፅእኖ አሳዳሪ ነው ተብሎ የሚታመንበትን ቡድን መርተው የመጡት ጂሚ ካርተር ምርጫው ከተካሄደ በኋላ ወደ አሜሪካ ለመመለስ ቦሌ ላይ ተገኝተው በነበሩበት ወቅት የተናገሩትን መለስ ብለን እንየው። ምርጫው ውጤት ሊቀይር የሚችል እንከን እንሌለበት መስክረዋል። የአፍሪካ ታዛቢ ቡድንና የካርተር ቡድን ቦሌ ላይ የሰጡት መግለጫ ተመሳሳይ ነበር። 
    አነ ጂሚ ካርተር ሌላው ቢቀር ወያኔ ራሱ የአውራ ባለስልጣናቱን (የአባዱላ፣ የጀኔዲን ሳዶ፣ የበረከት ወዘተ) ሽንፈት ለመሸፋፈን ተቃዋሚዊች ምርጫ አጭበረበሩ ብሎ መክሰሱንና ድጋሚ ምርጫ ማካሄዱ ይታወሳል። በሌላ በከል ደግሞ የአዲስ አበባው ውጤት ከታወቀ ግንቦት 7/1997 ከዘጠኝ ሰአት ጀምሮ ለሊቱን በሙሉ በመላ ኢትዮጵያ የኮረጆ ግልበጣ፣ የኮረጆ ዝርፊያ፣ ኮረጆ የማጨቅ ሰፊ ዘመቻ መከተሉ ለነ ሚስተር ካርተር ምንም መልእክት አልነበረውም። አቶ መለስ ግንቦት 7/1997 ከምሸተ 2 ሰዓት ላይ ‘ወታደራዊ’ አዋጅ ማወጃቸውና የታጠቀው ሃይል ሁሉ በእሳቸው ቁጥጥር ስር ሆኖ የሚሰራመሆኑን በማሳወቅ በጠቂቱም ቢሆን ሰብሰብ ብሎ መታየት እንደሚያስገድል ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ለነ ጂሚ ካርተር አሳሳቢ ሆኖ አልታየም። ሚስተር ካርተርና የቡድናቸው አባሎች ያንን በጨዋነት ድምፁን ሲሰጥ የዋለ ሕዝብ በጥይት እቆላሃለሁ የሚል ማስጠነቀቂያ ሲሰነዘርበት ምንም ተቃውሞ አላሰሙም። አቶ ካርተር ተታለለው ነው ካልን ራሳችንን ነው የምናታልለው። ታማኝ ተላላኪያቸውን የወያኔው ቡድን ማጣት አልፈለጉም። 
    ከዚህ ሌላ የአውሮፓ ታዛቢ ቡድንንም እናስታውሰው። የወያኔን ጉጅሌ አጭበርባሪበት ራቁቱን ለማውጣት የክብርት አና ጎሜዝ የግል አቋም ወሳኝነት ነበረው። የመሩት ቡድንም ሆነ የላካቸው የአውሮፓ ህብረት የሳቸውን ያህል በቆራጥነት ወያኔውን ለመጋፈጥ የቆመ አልነበረም። ለዚህ ነው አቶ መለስና የወያኔ ባለስልጣናት አና ጎሜዝን የአባታቸው ገዳይ አድርገው የሚያዩትና ከርካሽ አእምሮ የሚወጣ ስድብ በመለጠፍ ሴትዮዋን ለማቃለል ላይ ታች ያሉት። 
    የአሜሪካና የአውሮፓ አምባሳደሮች ተቃዋሚዎችን ዝም ለማሰኘት እንዴት ይረባረቡ እንደነበር ማሰታዎስም ተገቢ ነው። ነፃ ሚዲያዎችን ለመደለልና ዝም ለማሰኘት ከእነዚህ ኤምባሲዎች አንዳንዶቹ ምን ያደርጉ እንደነበርም አይዘነጋም።
    ስህተት ቁጥር ፬- የቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣናት የኤርትራን መገለል ለማቆም መንቅሳቀስ ጀመሩ።
    ይህም ሌላው ስህተት ነው። የነ ሚስተር ኸርማን ኮል እንቅስቃሴ ከግል ፍላጎታቸው የመጣ ነው ወይም የአሜሪካ መንግስት የቤት ስራ ሰጥቷቸው ብለን ራሳችንን እንጠይቅ። ከዚህ በላይ የተልኳስቸው ግብ ምንድን ነው ብለን እንጠይቅ። የነሱ ተልእኮ ኤርትራን ሳይሆን የወያኔ ጉጅሌን ለማዳን ነው። 
    ኤርትራ የወያኔን ተቃዋሚዎች ማስጠለሏን፣ መርዳቷን፣ ማሰልጠኗንና ማስታጠቋን እንድትተው ለማድረግ ያለመ ግብ መሆነን ልናሰምርበት ይገባል። የወያነ ጦር በዚህ የዘረኛ አደረጃጀቱና ከአንድ ብሄር በተውጣጡ ሰዎች የሚመራ መሆኑ የተራዘመ ጦርነት ሊዋጋ የማይችል እንደሚያደርገውይታወቃል። ስለዚህ ወያነን ለማዳን ውጊያዎችን ማስቀረት ይገባል። ይህን ለማድረግ የወያኔ ተቃዋሚዎችን የምትረዳውን ብቸኛ ጎረቤት አገር ከዚህ ስራዋ ዞር ማድረግ ብቸኛው አማራጭ ነው። የወያኔ ባለስልጣናት ደጋግመው እርቅን የሚለምኑት ኤርትራ እንደ ሱዳን፣ ጅቡቲና ኬንያ የወያኔን ተቃዋሚወዎች እየያዘች የምታርሰክብ ወዳጅ እንድትሆን፣ ተቃዋሚዎችን ማስታጠቋንና መንደርደሪያ መስጠቷን እንድተራቆም ለማድረግ ነው። ወያኔዎች ባድመን መስጠት የሚከብዳቸው አይደዐሉም ነገር ግን ባድመን ከማስረከባቸው በፊት በሃያል አደራዳሪ ፊት ኤርትራ እንድተገባው የሚፈልጉት ቃል ስላለ ነው። ኤርትራ ይህን አቆማለሁ ብላ ትፈርምላቸው ዘንድ የሚመኙት አሳሳቢ ነገር ስላለ ነው። ይህም ተቃዋወሞችን መድረሻ ለማሳት ያለመ ነው። 
    ነገር መዝጊያ!!!
    ወያኔ መሬት ለሱዳን የሰጠው፣ አፋኝ ደንብና መመሪያ ያበዛው፣ ሚዲያዎችን መፈናፈኛ ለማሳጣት የሚውተረተረው፣ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጣልቃ ገብነት የተማፀነው፣ በጎረቤት አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን እያስያዘ ወደ እስር ቤት የሚያስገባው፣ ወደ ጎቤት አገራት የሚወስዱ መንገዶችን በከፍተኛ ጦር ማስጠበቅ የጀመረው ግንቦት ሰባትን ለማዳከም (ከተቻለም ለማጥፋት) መጠጊያ ለማሳጣት፣ በሰው ሃይል እንዳይደረጅ ለማድረግ ነው።

No comments:

Post a Comment