BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!
Thursday, 23 January 2014
በጣም እጅግ በጣም ያሳፍራል አንድ ሀገርን እየመራሁ ነው ከሚል ምንግስትና ደጋፊዎች እንደዚህ አይነት ርካሽና አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸም ማየትም መስማትም እንዴት ያሳፍራል
ጥዋት በለቀኩት የአንድነት ለፍትህ ፓርቲ አባል ሆኑት ክብር አቶ/ አለማየሁ ለፌቦ ላይ ስለደረሰባቸው እንግልት እና ጉዳት አንድ ባከባቢው የሚገኝ ጓደኛዬ የነገረኝን እንዲህ አቅርቤዋለሁ ‹‹‹ይህ ገጓደኛዬ አሁን የሚገኝው አቶ/ አለማየሁ ከሚገኙበት ሲዳማ ዞን ቺሬ ወረዳ ነው፡፡ አቶ/ አለማየሁ ከታሰሩበት 7 ኪሎ ሜትር እንደ ምንጩ ዘገባ ከሆነ የታሰሩበት ምክንያት አቶ/ አለማየሁ ከዶዶላ በመኪና ተሳፍረው በመምጣት ላይ እያሉ ስለ መንገዱ መጥፎነት አስቸጋሪነት ሲያወሩ ድንገት ከጎናቸው የተቀመጠው ሰው “ አሁን ሊሰራ ነው ብዚህ አመት“ ሲላቸው እናንተ ምርጫ በተቃረበ ቁጥር ይሰራል ይሰራል እያላችሁ ህዝቡን ታታልላላችሁ“ በማለት አቶ አለማየሁ ይመልሱለታል>> ከዛ በኋላ ዎረካ ጌቶ የሚባልበት ምሳ በልተው ሲወጡ ሶስት ሲቪል የለበሱ ሰዎች መጥተው ‹‹መታወቂያ አምጣ›› ይሉታል ..አቶ/ አለማየሁ ማንነታችሁን ሳለውቅ መታወቂያዬን አልሰጣችሁም በማለት ይናገራሉ ››› በመቀጠል እነዚህ ሲቪል ለበሰው የመጡጥ ሰዎች አቶ/ አለማየሁን እየገፈታተሩ ........
እየጎተቱ በማመናጨቅና በማዋከብ ወደ እስር ቤት በመውሰድ እስር ቤት በሩ ጋ ከደረሱ በኋላ አቶ/ አለማየሁ ስልክ ለመደወል ሲሞክሩ ከጃቸው ላይ ሞባይላቸውን በመቀማት እስር ቤት አስገብተውታል ››› በመቀጠል ላብቶፕን በመክፈትና እላዩ ላይ ያስቀመጡትን የግል መረጃዎችን በመበርበር ላይ እንዳሉ ‹‹የአንድነት ለፈትህና ለዴሞክራሲን አርማ›› ከተመለከቱ በኋላ ‹የአሸባሪ ቡድን አባል ነው በማለት ተሳድበዋል.
የግል አስተያየቴን ከታች አሰፍራለሁ
<<ስለ ዴሞክራሲ ያልገባቸው ዴሞክራቶች ስለነጻነት ያልገባቸው ነጻ አውጪዎች>> ይሏችኋል እንዲህ ነው
በመጀመሪያ ሠውዬው የመሰላቸውን ነገር የመናገር የመተቸት የመቃወም የመደገፍ ህገመንገስታዊ መብት አላቸው ስለመንገዱም መጥፎነት ሆነ ስለሌላ ጉዳይ
ሁለት እንደ ተቀናቃን ተቋሚ ድርጅት አባልነታቸው ትክክል ያልሆነን አግባብነት የሌለውን ነገር የመናገር ለህዝብ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ‹<አውነት ነው ምርጫ ሲመጣ ሽርጉድ ያበዛሉ ይህ የወያኔ መገለጫ ነው>>፡፡
ሶስት ማንነታቸውን ላላሳወቁ ሰዎች መታወቂያቸውን የማሳየትም ሆነ የመስጠት ግዴታ የለባቸውም ህጋዊ ሰዎች እንኳን ቢሆኑ ማንንታቸውን አሳውቀው ሊወስዱት ይገባል እንጂ አናሳይም በማለት ህገወጥ ተገባር መፈጸም ተገቢአይለም (ለነገሩ ኢህአዲግ እራሱ ህጋዊ ድርጅት አይደለም)
አራት ሰውን ምንም (ባለጠፉት በመናገራቸው ምክንይት) እያንገላቱ እየደበደቡ እየጎተቱ መውሰድ ኢፍትሀዊ ህገወጥ አገባብነት የሌለው ድርጊት ስለሆነ ተቀባይነት የለውን
አምስት እኚህ ሰው የአንድ ፖለትካ ድርጅትና አመራር ናቸው በሳቸው ላይ የሚወሰደው መንኛውን ነገር ከወከላቸው ድርጅት ጋር ቀጥታ ይገናኛል
ስድስት አንድ በህጋዊተትና በፍቃድ የሚንቀሳቀስ ድርጅትን አሸባሪ ብሎ መሰየምና የድርጅቱን አባል የአሸባሪ ድርጅት አባል ብሎ መሰየም ጋጠወጥነት ከህገ ባላይ መሆን ነው ::
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment