BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 21 January 2014

ነፃ-ፕሬስ የሌለው መንግስት ኩራዝ በሌለው..................

ነፃ-ፕሬስ የሌለው መንግስት ኩራዝ በሌለው ጨለማ ቤት ውስጥ የሚኖር ግለሰብ እንደማለት ነው፡፡ ነፃ-ፕሬስ 

የሌለው ህዝብ በሃገሩ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ እንዳያውቅ የተፈረደበት ህዝብ ነው፡፡ ነፃ-ፕሬስ ለነፃነት፣ 

ለፍትሕና ለእኩልነት የሚያደርገውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዥዎች ፕሬሱ ለአምባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች 

ስለማይሆን ይፈሩታል፤ ይጠሉታል፤ ያጠፉታል፡፡ ...........ኢህአዴግም እያደረገ ያለው ይሄንኑ ነው፡፡ ነፃው ፕሬስ ለህዝቡ 

የፖለቲካ ንቃተ ህሊና መዳበር የሚያደርገውን አስተዋጽኦ፣ ህዝቡ ባሪያ ከሚያደርግ አስተሳሰብ እንዲላቀቅ፤ 

ከአምባገነኖች የሚደርስበትን ጫና አልቀበልም እንዲልና የኑሮው ሁኔታ እንዲሻሻል (improve people’s 

standard of living) የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንደ ኢህአዴግ አይነቱ ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ አምባገነን 

አይፈልገውም፡፡ ስለዚህ የማጥፋት ዘመቻ ያካሂዱበታል፡፡ 

ገዢ ፓርቲ የሆነው ኢህአዴግ ለ9ዐ ሚሊዬን ህዝብ የሚመጥን ነፃ ፕሬስ እንዲኖር ባለማድረጉ አገዛዙ ያልተሳካለት 

እንደሆነ አመላካች ነው፡፡

No comments:

Post a Comment