BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Friday, 24 January 2014

አያሌው ጎበዜ ቀለሉ “ለሱዳን መሬት እንዳይሰጥ አልፈርምም ስላለ ነው የተነሳው የሚባለው ውሸት ነው”

ከኢሳያስ ከበደ

ከአማራ ክልል ፕሬዚዳንትነት በፈጣን ተነስተው የጡረታ ጊዜያቸውን በአምባሳደርነት እንዲያሳልፉ የተሾሙት አቶ አያሌው ጎበዜ በአንዳንድ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ትልቅ ክብር ይሰጣቸው እንደነበር ከሚሰሙ መረጃዎች ሰምተን ነበር። ክብር አሰጥጧቸዋል የተባለውም ጉዳይ “ለሱዳን ተቆርሶ የሚሰጠውን መሬት አልፈርምም ብለዋል፤ እርሳቸው አልፈርምም ያሉትን በወቅቱ ምክትላቸው የነበሩት አቶ ደመቀ መኮንን ፈርመዋል” በሚል ነበር። ዛሬ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋር በሰጡት ቃለ ምልልስ ግን ያደንቋቸው፤ ያከብሯቸው የነበሩትን ሁሉ አንገት አስደፍተዋል። መቅለል ማለትም ይኸው ነው። አቶ አያሌው “በአመራር መተካካት በድንበር ምክንያት በከፍተኛ አመራሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተፈጸመ በማስመሰል የተነዛው ወሬ ጸረ ሰላም ሃይሎች የክልሉን ልማት ለማደናቀፍ የፈበረኩት ሴራ ነው” ሲሉ መናገራቸው አድርባይነታቸውን የሚያሳይ ነው ተብሏል። ይህም ደጋፊዎቻቸውን “ጸረ ሰላም ኃይሎች” የሚል ስያሜ እንዲሰጣቸው አድርጓል።...........

እርስዎ ሙሉውን ከዋልታ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ያንብቡትና ፍርድ ይስጡ – እኔ በበኩሌ አቶ አያሌው ቀለዋል ብያለሁ።
አምባሳደሩ በተለይ ከዋልታ ኢንፎርማሽን ማዕከል ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መተካካቱ የተከናወነው የአገሪቱን ህዳሴ ዳር ለማድረስ የተነደፈውን የመተካካት መርህን ተከትሎ ለመልቀቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው።
የአማራ ክልል ከሱዳን ጋር ባለው ድንበር የተነሳ ከአንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት በአስቸኳይ ጉባኤ የተነሳሁ በማስመሰል የተነዛው ወሬ የክልሉን ልማትና ሰላም ለማደናቀፍ የታቀደ ነው ብለዋል።
አምባሳደር አያሌው አያይዘውም ጸረ ሰላም ሃይሎች በብአዴን ከፍተኛ አመራሮች መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነትንና መተማመንን ለመሸርሸር፣ አመራሩን ለመነጣጠልና ሕዝብን ለማደናገር የፈጠሩት አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል።
በአማራ ክልል አመራሮች መካከል ድንበርን አስመልክቶ ውይይትና ክርክር የተደረገበት፣ ልዩነት የተፈጠረበት፣ አጀንዳ ሆኖ የቀረበበት ጊዜ አንዳልነበረም አምባሳደሩ ተናግዋል።
በሁለት አገራት መካከል የሚፈጠር የድንበር ጉዳይን የመወሰን ስልጣን ያለው የፌዴራል መንግስት እንጂ የክልል መንግስታት ስልጣን አለመሆኑን የገለጹት አምባሳደር አያሌው በፌዴራል መንግስት በኩልም ተላልፎ የተሰጠ መሬት የለም ብለዋል።
መንግስታችን መሬትን አሳልፎ የመስጠት ባህሪና ፍላጎት እንደሌለው የገለጹት አምባሳደሩ ተላልፎ የተሰጠ መሬት እንደሌለ ከሱዳን የሚዋስኑ የቋራ፤ የአርማጨሆና የመተማ አካባቢ ህዝቦች የሚያውቁት ጉዳይ ነው ብለዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ በርካታ አዳዲስ አመራሮች በነባር አመራሮች መተካታቸውን የጠቆሙት አምባሳደር አያሌው የአማራ ክልልም በተቀመጠው የመተካካት መርህ መሰረት በወጣት አመራሮች እንዲጠናከር መደረጉን ገልጸዋል።
የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ሰኔ መጨረሻ፣ በጥቅምት ወርና መንፈቀ ዓመት ላይ እንደሚደረግ ጠቁመው በጥቅምት ወር መካሄድ የነበረበት ጉባኤ የ2006 ዓ/ም እቅድ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ድረስ በማውረድ ከአርሶ አደሩ ጋር በመስኖ ልማት፣ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና በሚኖረን አደረጃጀት የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ የተሰራው ስራ ሰፊ ጊዜ በመውሰዱ ጉባኤው ወደ ታህሳስ ወር መገፋቱን አምባሳደሩ ተናዋል። አምባሳደር አያሌው ጎበዜ በአማራ ክልል ለ21 ዓመታት በከፍተኛ አመራርነት ቆይታቸውም ደስተኛ እንደነበሩ ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment