አቶ አለማየሁ ለፌቦ የተባሉ በሲዳማ ጭሬ የአንድነት ፓርቲ አባል ከፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ወደ ክልሉ ሲመለሱ አርሲ ሚጣ ነሴቦ ወረዳ ወርቃ ከተማ ታህሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም እንደተያዙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከታሰሩበት ወረዳ ያንተ ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ ስለሆነ እዚህ አይታይም በማለት ጥር 9 ቀን ወደ ሻሸመኔ ዞን ፖሊስ ተወስደው ታሰሩ፡፡
ፖሊስ ጣቢያውም እንድትለቀቅ ከፈለግክ 1ኛ እስከዛሬ የታሰርኩበትን አልጠይቅም 2ኛ ከዚህ በኋላ ወደ ፖለቲካ አልገባም 3ኛ በተፈለኩኝ ሰዓት እቀርባለሁ ብለህ ..........ፈርምና ውጣ የሚል ቅድመ ሁኔታ ቢያቀርብላቸውም አቶ አለማየሁ ግን በሰላማዊ መንገድ የሚታገልና በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አባል ነኝ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም፣ በፍጹም አልፈርምም ብለዋል፡፡
በ 5 ክስ ከሰንሃል 4ቱን ውድቅ አድርገናል በአንዱ ግን እንከስሃለን በሚል ለማስፈራራት ቢሞክሩም አቶ አለማየሁ በአቋማቸው ጸንተዋል፡፡ የሻሸመኔ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተጫን ለምን እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡ አቶ አለማየሁ በአሁኑ ሰዓት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሻሸመኔ ዞን ፖሊስ ጣቢያ በአደራ ታሰረው የሚገኙ እስረኛ ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment