BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Friday, 31 January 2014

የጎሠኛነት ሥርዓት ካመጣብን ጣጣ ዋኖቹ የአስተሳሰብ ችግሮች እነዚህ ናቸው


Addis Asfaw

የጎሠኛነት ሥርዓት ካመጣብን ጣጣ ዋኖቹ የአስተሳሰብ ችግሮች እነዚህ ናቸው፤ የቡድን መብትን መሠረታዊ አድርጎ የግለሰብን መብት ጨፍልቆ የተነሣው የወያኔ የጎሣ ሥርዓት ከሃያ ዓመታት በኋላ በስንት ጥረት የደረሰበት አሁንም የተዛባ ድምዳሜ የቡድን መብትንና የግለሰብ መብትን ጎን ለጎን አቁሞ እኩል ናቸው ማለትን ነው፤…ሳትቧደን አትገጥምም ስለዚህ የራስህ ክልል ባንዲራና ቋንቋ አላህ ብቻ ተቧደን አለበለዚያ ‘ ልዩነታችን ውበታችን አይቀጥልም! “አንድነታችን ድምቀታችን የድሮ ሥርዓት ናፋቀነት ነው። “በአንድነት ውስጥ ያሉት የፊውዳሉ ልጆችና የልጅ ልጆች አማራዎች ናቸው እነሱ ይምሩን”አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በግላቸው በኅብረት ቋንቋ ሲተረጎም ” ህወአት ዝም አትበል አንድነትን አጥፋው ማለት ነው።” የሥልጣን ጉልበትና የሥልጣን ምኞት ተጽእኖ እንደአንድነት ያለውንም የፖሊቲካ ፓርቲ ፐሮግራሙን እንዲለውጥና የግለሰቦችንና የቡድን መብቶች በአንድ ደረጃ ላይ እንዲያስቀምጥ ተደርጎአል። ከቡድን ውስጥ ግለሰቦች ሁሉ ሙልጭ ብለው ሲወጡ ስለቡድን መብት የሚያወራ (በድን) ይሆናል። በድን ይናገራል!?...........

የአቶ ለገሠ መለሰ አመራር የቡድን ነበር ሲሉ (የአንድ ክልል ጎሳ፣ ዘመዳሞች፣ ጋብቻሞች፣አብሮ አደግና፣ታማኞችን አካትቶ ነበር) የአቶ ኅይለመለስ ደስአለኝ አመራር የኅብረት(አመራር በደቦ) ( ከኋላም ከፊትም ሆናችሁ ደግፉኝ…በጠ/ይ ሚ/ር ማዕረግ የብሔር ብሔረሰቦች ሊ/መንበርና የሻቢያህወአት የውጭ ጉዳይ አስፈፃሚ መልዕክተኛ)


“ጎሠኛነት ምን ጊዜም የትም ቦታ እንደግራ ፖሊቲካ ተፈርጆ አያውቅም።” “አድሃሪዎችን አውድመን አሁን ቀኝ መንገደኞች፣ ጠባብ ብሔርተኞች፣ ወንበዴዎች ፣ድልድይ አፍራሾች፣ የኤምፕሪያሊስት መልዕክተኖች ዙሪያውን ተብትበውናል ይወድማሉ!” አሉ ሌ/ኮል መንግስቱ ኀይለማርያም አሁንማ ጨዋታው ተቀይሮ “መሀል ገብተው አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አረንጓዴው ልማታዊ መንግስት ሆነዋል። የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለዘለዓለም ያለባቸው ችግር በ፹፬ ቋንቋ የሚናገሩት ግን አድማጭ አቱለት ነገር ቢኖር….ዘር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ሀብትና ሌላ ማናቸውንም ነገር ከቁም-ነገር ሳይቆጥሩ ለማንም ሰው በሰውነቱ ብቻ ማግኘት የሚገባውን መብት እንዲያገኝ መሠረታዊ ፍላጎታቸው እንዲሟላላቸው ነው። የፖለቲካ ተንታኝና ፀሐፊያን ሙግት እንደ መንዝ በግ በፀጉር፣ በላት፣ በቀንድ፣በሽንጥ፣ በክብደት፣ በድምፅ፣ በቀለም፣ መዝኖ ቆይቶ መደባለቅ (የእግዝሐብሔሩን አምሳያ ፍጡር የሰውንም ልጅ ) እየለካ የቡድን መብትንና የግለሰብ መብትን ጎን ለጎን አቁሞ እኩል ናቸው ማለትን ነው፤(ግን ፀጉር፣ ቀንድ፤ ላት፣ ሌለው በግ) ከምግብነት ይቀራል። ዘር ነገዱን ብሄሩን ያልጠራ ሰው ዜግነቱን ይነፈጋልን? ተቧድኖ ያልተሰለፈ ከሰው መሆን ደረጃ የሚያንስ ፍጡር ይሆናል?

No comments:

Post a Comment