ማንኛውም አንድን ሃገር እመራልሁ የሚል …የበላይ መመሪያ እና ህዝብን የሚያስተዳድርበት ህገመንግስት አለው:; የወያኔ ጁንታም በራሱ የፓርቲ ፕሮግራም መሰረት ተደርጎ አለማቀፍ ህጎች ተዋህደውት በራሱ ካድሬዎች ውክልና እና ስብስብ የጸደቀውን ህገመንግስት ለህገወጥ ተግባር እያዋለው ነው:: አንድ ህዝብ ህግን ሊያከብር የሚችለው ራሱ ወይንም ተወካዮቹ ባረቀቁለት ህግ እና ህገመንግስት መሆኑ እሙን ነው::ጨዋው ይሪትዮጵያ ህዝብ ግን እንደፈለጉ የሚያመጡለትን ህግ አንገቱን ሰብሮ በማክበር ሲኖር ገዢዎቹ ግን ራሳቸው ያወጡትን ህግ ሀገወጥ መሆኑን በአደባባይ ያስመሰከሩበት አጋጣሚዎች እጅግ ብዙ ናቸው::............
በሃገሪቱ ህገመንግስታዊ መዋቅር እና መነባበብ የሌሉባቸውን ያለፍት ህገወጥ 22 አመታቶች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበላይነት የተዳደሩ ወይንም ያለፉ የሰው ልጆችን ይወክላሉ የሚባሉ ህጎችን ማግኘት አስቸጋሪ ነበር::ምንሊክ ሳልሳዊ በዘፈቀደ የበላይ የፓርቲ አመራሮች በሻቸው ሰአት ህጎችን በማውጣት እና በማጽደቅ ህዝብ ላይ እንደፈለጉ ይጨፍራሉ:: ህዝብ ለህገመንግስቱ ያለ ግንዛቤ አናሳ መሆኑን እና ማን እንዳወጣው እንዴት እንደወጣ ስለሚያውቁት ህዝቡ ያሌለበት ተሳትፎ እንደሆኑ ስለሚረዱት እንዳሻቸው ህገመንግስቱን ይጥሉታል ያነሱታል:: የወረቀት ላይ እይታ ብቻ አድርገው በማስቀረት ህገወጥነትን አስፋፍተዋል::
በወያኔ ውስጥ ተስፋፍቶ የሚገኘው መንግስታዊ ህገወጥነት ከእይታ ያልተሰወረ ሲሆን ህዝብ በህገመንግስቱ መሰረት ፍትህ ማግኘት ሲገባው ፍትህን አቶ እየተንደፋደፍ ይገኛል::ህዝብን በፍትህ እጦት የታረደ ዶሮ ያደረገው ወያኔ የፍትህ አከላት ከህገመንግስቱ ውጪ ህገወጥ የሆኑ ያልተጻፉ ህጎችን ሲጠቀሙ ያየ ወይንም ለምን ያለ መንግስት የለም::የፍትህ አከላቶች ህገን ለማስከበር እና ህግን ለመተርጎም የተቋቋሙ አካላት ሆነው ሳለ በፖለቲክ ትብትቦሽ ተይዘው ሕገ መንግሥቱን በሚያሽመደምድ ሕጎችን በሚጥስ መንገድ እነ ..እንዳይጠየቁ ወይም እንዳይከሰሱ፣ ከተከሰሱም እንዳይሸነፉ የሚንቀሳቀስና የሚሯሯጥ በፍትህ አከላት ውስጥ በድብቅና በሕገወጥ የተገነባ አካል በይፋ በትንንሽ መመሪያዎች እና ትእዛዞች ህገመንግስቱን ደፍጥጦታል::
ሌላው በወያኔ ጁንታ ውስጥ እየተደረገ ያለው ህገመንግስታዊ ህገወጥ ንቅዘት የዜጎች የመኖር ህልውና እና ሰርቶ የማደር ጉዳይ ሲሆን አለማቀፍ ድንጋጌዎችን የጣሰ እና ህገመንግስቱት የጣለ ከፍተኛ የሆነውን ህዝብ ለስደት ያበቃ የጸረ ህልውና እንቅስቃሴ በገሃይ እያየን ነው::ይህ ደሞ የወለደው የወያኔ ባለስልታናት በሚያደርጉት ህገወጥ የኢኮኖሚ ወረራ ምክንያት ህዝቦች በሃገራቸው እንዲሽመደመዱ ሲያደርግ ሰርቶ የመኖር ህልውናን ገደል ከቶታል::ባእስልጣናቱ ህዝቦች በፈለጉት የስራ መስክ እንዳይሰማሩ ሙስናን እና ንቅዘትን በስፋት በስራ ላይ አውለውታል::
እነዚህ የተፈጠሩ መንግስታዊ ህገወጥነቶች ሕዝብ መንግስት እንዳሌለ አምኖ እንዲቀበል አድርገውታል፡፡እኩልነት እንዳሌለ አረጋግጠዋል፣ ሕገ መንግሥቱም አለኝታዬ አይደለም እንዲል አድርገውታል፡፡ ምክንያቱም ሕግ አክብሩ ከሚባሉ ዜጎች ጎን ለጎን ከሕግ በላይ የሆኑና ተመልሰው መንግሥትን የሚጫኑ፣ የሚይዙና የሚያስፈራሩ ሌሎች ዜጎች እንዳሉ ሕዝብ በተግባር አይቷል፡፡ እነሱንማ ማን ይነካቸዋል እያለ መንግሥት ዜጎችን ከሕግ አንፃር በእኩልነት ያያል የሚለው እምነቱ ተሟጧል፡፡የተቃወሙትን መብታቸውን የጠየቁትን ሁሉ ልማቱን ያደናቅፋሉ፡፡በማለት… የወያኔ ባለስልጣናት ከአገርና ከሕዝብ በላይ ነን ብለው አገር ለእነሱ በምትስማማበትና በምትገዛበት መንገድ እንድትጓዝ ይፈልጋሉ እንጂ ከእነሱ ጥቅም፣ ክብርና ዝና ውጭ ህዝቦች በህግ ተዳደሩ አልተዳደሩ አጀንዳቸው አይደለም፡፡ለምን ቢባል ጥይት እንዲገዛቸው ይደረጋል:: እነዚህ ሕገወጥ የወያኔው ቡድኖች አገርን እየዘረፉ፣ የአገር ገንዘብ እያሽከረከሩና የሰው ልጆችን መብት እየጣሱባለበት ወቅት ህዝብ በቃኝ ብሎ ሕገወጥነትን ለማፈራረስ ሲረባረብ በጥይት ይቆላል ይወነጀላል::
ወያኔ ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ወደ ልማታዊ ዲሞክራሲ ተለውጫለሁ በማለት እያጭበረበረ ነው፡፡ ሕዝቡን ከድህነት ለማላቀቅ፣ ሙስናን ለመዋጋት የቆምኩና የቆረጥኩ ነኝ በማለት እያደናበረ ነው፡፡ የሕግ የበላይነት የሚለውን አባባልም በየዕለቱ ለሚዲያ ፍጆታ እየዋለ ነው፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነትን እና አደርባይነትን ማውገዝ ከዕለቱ የሜትሮሎጂ ሪፖርት በላይበተጋነነ መልኩ በተደጋጋሚ የምንሰማው ነው፡፡ በወያኔ መዋቅሮች ውስጥ ተሰግስገው ያሉት ሕገወጥ ንቅዘቶች ግን የማይፈርስ መሰረታቸውን ተክለው እየተንቀሳቀሱ ነው::ይህን ለነገ አደጋ እንዳለው ያልተረድው ወያኔ ራሱን ማዳን ወደማይችልበት አዘቅት ውስጥ እንደገባ እሙን ነው:;
(ምንሊክ ሳልሳዊ)
No comments:
Post a Comment