ወጣቱ ትውልድ ራሱን ከፅንፈኞች ማራቅ ታሪካዊ ግዴታው ነው !
ኢሕአፓ ወክንድ – መግለጫ
ከጠባቦችና የግንጠላ አራማጆቸ ጎራ እንደሚስተጋባው ከንቱ ታሪክ አገራችን ኢትዮጵያ በድንገት የዛሬ መቶ አመት የተከሰተች ሳይሆን በብዙ ዘመናት የዜጎች መስዋዕትነት የተገነባች አገር ናት። ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ለማድረግ የብዙ ሚሊዮንና የአያሌ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ህይወት ተገብሮባታል። ........
ይነሰም ይብዛም፣ ይጉላ ይደብዝዝ፣ ሁሉም ህዝብ ለዚያች አገር ግንባታ አሰተዋፅኦ አድርጉአል። በሌሎች አገሮች ታሪክም እንደተከሰተው ሁሉ በኢትዮጵያም ታሪክ ጦርነት የሀገር ግንባታው ሂደት አካል ሆኖ ተገኝቷል። በሂደቱ ለጠፋው ህይወትና ለደረሰው በደል የዛሬው ትውልድ ከቶም ተጠያቂ ሊሆን አይችልም ብሎ ኢወክንድ ያምናል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
No comments:
Post a Comment