BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Thursday, 23 January 2014

ዲሞክራሲ በምርጫ ሳጥን ብቻ ሳይሆን፤ በኑሮአችን ድርና ማግ ውስጥ ሁሉ የሚኖር መሆን አለበት፡፡

 ሁሉን ጐራሽ የሆነ አሠራር ከተከተልን ፖለቲካውም ሆነ ባህሉ ልሙጥ ይሆናል፡፡ ይህም ህዝብን ሽባ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ይሰውረን፡፡ ሥልጣንን ማጋራት፣ ሥራን ማከፋፈል ይቻለን ዘንድ ትምህርታችንን ይግለጽልን! የችግር ጊዜ ሁኔታዎች ይለዋወጣሉ፡፡ የላዩ ታች የታቹ ላይ ቦታ ሊቀይር ይችላል፡፡ በደስታው በተድላው ጊዜ የሚደረገው ሁሉ ይቀራል፡፡ ድህነት ጥላውን ሲጥል ማጀት ጓዳው መራቆቱ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብም ይራቆታል፡፡ ዕምነት ይመነምናል፡፡ ጀግንነት ይኮሰምናል፡፡ ቆራጥነት ይከሳል፡፡...... የሌለው ላለው ያድራል፡፡ ተገዢ ገዢውን ከልኩ በላይ እጅ ይነሳል፡፡ አድር ባይነት የዕለት የሠርክ ጉዳይ ይሆናል፡፡

ኢሕኣዴግ ሆይ...ሁሌ በተለመደው የፖለቲካ መንገድ መሄድ ለህዝብ ዕድል አይሰጥም፡፡ ሽንፈትን መቀበል ትልቅ ፀጋ ነው፡፡ ሽንፈትን ለመቀበል ዝግጁ የሆነ ሲያሸንፍ ጉራ አይነዛም፡፡ንቅዘት ብቻ ነው ጉዞው፡፡ የዓለም ታላቅ ኃይለም ያሸንፍ አገራዊ ኃይል፤ በምን ሁኔታ አሸነፈን እንጂ፤ አልሸነፍም ማለትን መመርመር አለብን፡፡ የማረከውን ሰው በሰብዓዊ መንገድ ለመያዝ የሚችል ተዋጊ ጀግንነትን ከጭካኔ በመለስ ማየት አይሳነውም፡፡ ምህረት ለማድረግም ፍርሃትና ሥጋት አይኖርበትም፡፡ “የተጠማ ከፈሳሽ፣ የተበደለ ከነጋሽ” የሚለው ምሣሌያዊ አነጋገር በቀላሉ ይገባዋል፡፡ ምርጫ፣ በተለይም በአገራችን፣ በሚካሄድበት ጊዜ የሚያጋጥመን የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽ፤ 1ኛ/ የተሸናፊው ሽንፈትን አለመቀበል እና 2ኛ/ የአሸናፊው ዘራፍ ባይነት ነው፡፡ ይህ ማለት ከምርጫው በኋላ አሸናፊና ተሸናፊ አይጥና ድመት ናቸው ማለት ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ዐይን መተያየት ቀርቶ እንደ ዜጋ መተሳሰብም ይቀራል፡፡ “የማትወልደውን ሶሻሊዝም ሲያማምጡዋት፤ ከነ ካፒታሊዝሟም አስወረዳት!” እንደተባለው ነው፡፡ አዲስ ሥርዓት መፍጠር ቀርቶ አሮጌውንም ማጣት አለ፡፡ ቁልቁል ማደግ የሚባለው ዓይነት! ዲሞክራሲ በምርጫ ሳጥን ብቻ ሳይሆን፤ በኑሮአችን ድርና ማግ ውስጥ ሁሉ የሚኖር መሆን አለበት፡፡ ሁሉን ጐራሽ የሆነ አሠራር ከተከተልን ፖለቲካውም ሆነ ባህሉ ልሙጥ ይሆናል፡፡ ይህም ህዝብን ሽባ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ይሰውረን፡፡ ሥልጣንን ማጋራት፣ ሥራን ማከፋፈል ይቻለን ዘንድ ትምህርታችንን ይግለጽልን! የችግር ጊዜ ሁኔታዎች ይለዋወጣሉ፡፡ የላዩ ታች የታቹ ላይ ቦታ ሊቀይር ይችላል፡፡ በደስታው በተድላው ጊዜ የሚደረገው ሁሉ ይቀራል፡፡ ድህነት ጥላውን ሲጥል ማጀት ጓዳው መራቆቱ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብም ይራቆታል፡፡ ዕምነት ይመነምናል፡፡ ጀግንነት ይኮሰምናል፡፡ ቆራጥነት ይከሳል፡፡ የሌለው ላለው ያድራል፡፡ ተገዢ ገዢውን ከልኩ በላይ እጅ ይነሳል፡፡ አድር ባይነት የዕለት የሠርክ ጉዳይ ይሆናል፡፡ ሁሌ በተለመደው የፖለቲካ መንገድ መሄድ ለህዝብ ዕድል አይሰጥም፡፡ ሌላው ይቅርና ለፖለቲከኛው ለራሱም ዕድል አይሰጥም ፡፡ እስከንቅዘት ብቻ ነው ጉዞው፡፡ ወደ አዲስ አይን መክፈት አያመራም፡፡ የትኛውም ዘመን በየትኛውም ፓርቲ አንድና አንድ መንገድ ብቻ ልከተል ባለ ሰዓት የሚከሰት ችግር ነው፡፡ የታየ፣ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው!! “እወርካ ሥር የገደለ፣ ዘወትር እወርካ ሥር ያደፍጣል” የሚባለው እንዲህ ሲሆን ነው! ጦርነት ሰልችቶናል፡፡ ከዚህ ቀደም በተካሄደው ጦርነታችን ብዙ ሰው አልቆብናል፡፡ ብዙ ንብረት ወድሞብናል፡፡ ኢኮኖሚያችን ደቅቋል፡፡ ስለዚህ ሌላ ጦርነት ይጎዳናል እንጂ ምንም አይፈይደንም!

No comments:

Post a Comment