BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Saturday, 25 January 2014

ለኢሳት መረጃ አቀብሏል የተባለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ::!


ለኢሳት መረጃ አቀብሏል የተባለው
ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በአሸናፊ ደምሴ

ከአሜሪካን፣ ከኔዘርላንድና ከእንግሊዝ በመላው ዓለም ለሚሰራጨው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢሳት) በኢትዮጵያ ተቋማት፣ ድርጅቶችና ዜጎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል መረጃን አቀብሏል ሲል የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሰረተበት በኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የጋምቤላ ኤርፖርቶች የጥበቃ ዋና መምሪያ ሠራተኛ የሆነው አቶ ሚኪያስ ንጋቱ በፈፀመው የስለላ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ4 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ከትናንት በስቲያ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፎበታል።
እንደዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ከሆነ ተከሳሹ፣ ቀኑና ወሩ በውል ባልታወቀ ነገር ግን ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ በጋምቤላ ክልል በሚገኘው የኤርፖርቶች ድርጅት የጥበቃ ዋና መምሪያ ሠራተኛ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት ስርጭቱን ከአሜሪካ፣ ከኔዘርላንድ እና ከእንግሊዝ በማድረግ የአሸባሪው የግንቦት 7 ልሳን እንደሆነ ለሚነገርለት ኢሳት በተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ውስጥ ከሚሰራው ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ጋር ግንኙነት በመፍጠር መረጃዎችን ሲያስተላለፍ ቆይቷል ይላል። .............
        ለዚህም ውለታው 4460 ብር በመቀበል፤ ለስራ ተመድቦ በሚያገለግልበት የጋምቤላ ክልል ውስጥ በተለያየ ዘርፍ ኢንቨስተሮች ሆነው ግድያ ስለተፈፀመባቸው የውጪ ዜጎችና 19 በሚደርሱ የክልሉ የግብርና ኮሌጅ ተማሪዎች ላይ ተፈፅሟል ስለተባለው ግድያ በተመለከተ በፎቶ የታገዘ መረጃን ከማቀበሉም ባሻገር፤ በክልሉ መንግስት ስር የተካሄደውን ሹምሽር በተመለከተም በምስልና በፅሁፍ አስደግፎ በኢ-ሜይል እና በስልክ መረጃዎችን በማስተላለፉ በፈፀመው የስለላ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል ሲል ዐቃቤ ሕግ በክስ መዝገቡ በዝርዝር ያትታል።
በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩ በመታየት ላይ የነበረው ተከሳሹ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበበትን ከኢ-ሜይል ሳጥኑ የተሰበሰቡ 10ገፅ የፅሁፍ ማስረጃዎችና ከስልኩ የተወሰዱ ሶስት ፎቶግራፎችን አስመልክቶ በአግባቡ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ያለው ሲሆን፤ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሹ የኢትዮጵያን መንግስትና ህዝብ አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል መረጃን ለአሸባሪ ቡድን አባላት ከማስተላለፉም በተጨማሪ የሙያውን ስነምግባር በሚፃረር መልኩ በፅሁፍና በፎቶ የታገዘ መረጃዎችን ሲያስተላልፍ በመያዙ እንደቅጣት ማክበጃ ይወሰድልኝ የሚል ሀሳብ አቅርቧል።
          የተከሳሹ ተከላካይ ጠበቃ በበኩላቸው ግለሰቡ ከዚህ በፊት የፈፀመው ምንም አይነት ወንጀል አለመኖሩንና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን፤ እንዲሁም በአካባቢው የወጣት ማዕከላት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የነበረውና የመልካም ባህሪይ ባለቤትነቱን በመጥቀስ ቅጣቱ እንዲቀልለት ጠይቀዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ፍርድ ቤቱም፤ ተከሳሽን ጥፋተኛ ነው ባለው መሰረተ በ4 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ከትናንት በስቲያ ጥር 12 ቀን 2006 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፏል።

No comments:

Post a Comment