የሆነው ሆኖ ኢህአዴግዬ ሰጠች ስለተባለው መሬት ማብራሪያ እንዲሰጡ ሰማያዊዎቹ በጠሩት ስብሰባ ላይ የተገኙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪም፡፡ ኢህአዴግ መሬቱን ለሱዳን መስጠቷን የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ የለም ካለ፤ ይሄ መሬት ተሰጥቷል ብላችሁ እስቲ በካርታ ላይ አሳዩን ብለው ሰማያዊዎቹን ሞገቷቸው፡፡ አክለውም ይሄ ጉዳይ ለበርካታ ጊዜያት ሲያጨቃጭቅ መቆየቱን እና ጥርት ያለ ምላሽ እንዲገኝለት ጥርት ያለ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል ለዚህም ማንም ሳይሆን ራሳችን ሃላፊነት መውሰድ አለብን አሉ…..
ፕሮፌሰር መስፍን ማለት እንግዲህ እንዲህ ናቸው፡፡ ኢህአዴግዬ (እርሳቸው ወያኔ ይሏታል) “የጭፍን ጥላቻ ፖለቲከኛ” ከሚለው አንስቶ የማትላቸው ነገር፣ የማትሰጣቸው ስም የለም፡፡ እርሳቸው ግን ሁላችንም ከምንላቸው በላይ ናቸው፡፡ በተለይ ኢህአዴግን ይከብዷታል! ኢህአዴግ ልብ ቢኖራት የፕሮፍን ነገረ ስራ ጥሞና ሰጥታ በመከታተል እግራቸው ስር ተንበርክካ ይቅርታ መጠየቅ ከዛም ወፈር ወፈር ባሉ ጉዳዮች ላይ እንደ ሱዳን ድንበር እንደ አባይ ግድብ የመሳሰሉት ላይ ምን ይበጃል ብላ ብታማክራቸው ለራሷም ለእኛም ጥቅም ነበር፡፡ (እኛ ተብሎ የተጠቀስነው ሰፊው ህዝብ ነው)
ፕሮፍ ብዙ ብዙ ያኑሮት!
(ማስታወቂያ፤ በቅርቡ ድረ ገፃችን በአግባቡ የምናወጋባት እንደምትሆን እየተናገርን እስከአሁን ለተፈጠረው እንዝላልነት ይቅርታ እንጠይቃለን)
No comments:
Post a Comment