ወያኔ እግሩ አዲስ አበባን ከረገጠበት ግዜ ጀምሮ የጭቆና ተቋሞቹን በየቦታዉ ተክሎና ተደላድሎ ህዝብን እንዳሰኘዉ መርገጥ እስከጀመረበት ግዜ ድረስ አንዴ ሰዉ በላዉን የደርግ ስርዐት አስወገድኩላችሁ እያለ ሌላ ግዜ ደግሞ ፌዴራል ስርዐት መስርቼ ብሄር ብሄረሰቦችን ነፃ አወጣሁ እያለ ለተወስነ ግዜም ቢሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ቀልብ መሳብ ችሎ ነበር። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ያ በፌዴራሊዝም፤ በዲሞክራሲና በይስሙላ ምርጫ የተሸፈነዉ የወያኔ አስቀያሚ ገበና ይፋ እየሆነ መጥቶ ወያኔ አርግጫዉንና ግድያዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ትግሉን፤ እስሩንና ስደቱን ተያያዙት።
BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!
Monday, 30 June 2014
እያበበ የመጣዉ ህዝባዊ ትግል
ጊዜ የማይሠጥ ሀገራዊ ጥሪ አለብን!
ራሱን “የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር” ብሎ የሰየመው ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት (ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት)፤ ሀገራችንን ዕለት ከዕለት ወደ ባሰ አዘቅት እንድትገባ እየጎተታት ነው። የፖለቲካ ፍልስፍናውና የአስተዳደር መመሪያው የሀገራችንን ሕልውና በንጥልጥል ላይ እንዲቀመጥ ሌት ከቀን እየጣረ ነው። በአንፃሩ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ በመቆም፤ በተለያዩ ድርጅቶች ከፍተኛውን መስዋዕትነት በመክፈል፤ ከዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተዋደቁ ያሉ ታጋዮች አሉ። ይህ በዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥትና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል እየተደረገ ያለው ግብግብ፤ ለረጅም ዘመን እንዳለ ሆኖ፤ ፀረ-ኢትዮጵያዊው መንግሥት የፈለገውን እያደረገ ያለበትና፤ በታጋዩ ወገን ያለው ክፍል ደግሞ ላለፉት ፳ ፫ ዓመታት ባለበት የሚረግጥበት ሁኔታ አልተለወጠም። ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት የሚጠናወተው ክፍል እየበዛ፤ በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቱ ይኼው ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ሊቆጣጠረው በማይችልበት ቀውስ ውስጥ ልትገባ አዝምማለች። ከዚህ እንድታቀና ሁላችን እንፈልጋለን። ይኼን ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ማስወገድ ሁላችን እንፈልጋለን።
Sunday, 29 June 2014
ከምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ፍትህ አሁንም ድረስ አለማግኘታቸውን ገለጹ
ኢሳት ካነጋገራቸው የተፈናቃዮች ተወካዮች መካከል አንዳንዶች እንደገለጹት የአማራ ክልልም ሆነ የፌደራሉ መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ አንገባም በሚል ምክንያት ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች አልሆኑም።
ከመንግስት የሚሰጠው መልስ ተስፋ እንዳስቆረጣቸውም ተፈናቃዮች ገልጸዋል
የተፈናቃይ ተወካዮች እንደሚሉት ከፍተኛ ችግር ከነበረበት ከሚያዚያ 22 እስከ ግንቦት2 በነበረው ጊዜ ለደረሰው የሰው ህይወት እንዲሁም ለጠፋው ከፍተኛ ንብረት የአካባቢው ባለስልጣናት እና በክልሉ ተሰማርቶ የሚገኘው ልዩ ሃይል እጅ አለበት። ባለስልጣናቱ የችግሩ አሳሳቢነት ሲነገራቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን የተፈናቃዮች ተወካዮች ተናግረዋል።
በተለይም ጉዳዩን እንዲያጣራ በቅርቡ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ማስረጃዎችን አስቀድሞ ይፋ እያደረገና የምስክሮችንና የጠቁዋሚዎችን ስሞች አስቀድሞ ይፋ እያደረገ ህዝቡ በድጋሚ እንዲጋጭ ጥረት እያደረገ ነው በማለት ተወካዮች ገልጸዋል።
በጊምቢና በቄለም ያሉ ዘመዶቻቸውን በስልክ ለማግኘት መቻላቸውን የሚናገሩት ተፈናቃዮች፣ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራራቱ እንደቀጠለ መሆኑን እንደነገሩዋቸው አስረድተዋል።
ከኦሮምያና ከፌደራል የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ማክሰኞ ወደ ጊምቢ በማቅናት ነዋሪውን እያነጋገሩ ነው። እስካሁን ድረስ በመንግስት በኩል ተፈናቃዮችን በተመለከተ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።
በጊምቢ ተነስቶ በነበረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲወድም፣ አንድ ፎቅና ሁለት መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በርካታ ቤቶችም ተዘርፈዋል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/31736
ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ ”ሞት ሊበየንበት ይችላል” -በሽብርተኝነት ክስ ሞት ተፈርዶባቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁ 127 ሰዎች ኣሉ
በኖርዌይ ሃገር ውስጥ በኖርዌጂያንኛ የሚታተመው ዳግብላደት የተባለው ጋዜጣና ድረ-ገጽ ”ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን” ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ በሚቀጥለው ሳምንት ሞት ሊበየንበት ይችላል” ሲል ኣውጥቶኣል።
”ባለፈው ሳምንት ለማወቅ እንደተቻለው ዕድሜው 52 የሆነና ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ የተባለ ኖርዌጂያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል።” tiltalt for terror በማለት የጀመረው የኖርዌዩ ዳግብላደት ሲቀጥልም…”የኢትዮጵያ መንግስት ቃለ ኣቀባይ እንደሚለው ገንዘብ ኣሰባስቦና ኣጥቂ ቡድን መልምሎ ኣደጋ ለማድረስ ሲሞክር ያዝነው በማለት መከሰሱን ያትትና በበኩላቸው የኖርዌዩ የሰብኣዊ መብት ጥበቃም ሆኑ የዓለም ኣቀፉ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን በጥብቅ ያወገዙት ሲሆን፣ ኣያይዘውም ለዚሁ ድረ-ገጽ ታሳሪው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ከወትሮው የከፋ እንደሆነም ስጋታቸውን እንደገለጹለት ያወሳል።
ኢትዮጵያንም ሆነ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት፣ በኣሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ የሚገኙትን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ ”በሚገባ ያውቃሉ” ያሉዋቸውን የሰብኣዊ መብት ተሟጋችና ኖርዌጂያን ፈሊክስ ሆርነ ን ኣነጋግሮ ድረ-ገጹ ያገኘው መልስ ”ኖርዌጂያኑን ኦኬሎ በሚቀጥለው ሳምንት የሚሰየመው ችሎት ሞት ሊበይንበት ይችላል” በማለት የገለጹ ሲሆን ኣክለውም፣
”በሃገሪቷ ውስጥ በሽብር ወንጀል የሚከሰሱት ዜጎች የሚገጥማቸው የሞት ፍርድ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሞት የሚፈረድባቸው ዜጎች ምንም ማስረጃ ያልቀረበባቸው ናቸው።
መዝገቦቹ መልሰው ተቀራረቡ የእምነት ክህደት ቃል በኃይል አስፈርመዋቸዋል
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በስድስቱ ጦማሪያንና በሦስቱን ጋዜጠኞች ላይ የፌደራል ፖሊስ የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቀጠሮ የሚያራዝመውን ሁለት መዝገብ አንዴ ሲያቀራርበው መልሶ ደግሞ ሲያራርቀው ቆይቶ አሁን ደግሞ መዝገቦቹን መልሶ አቀራርቧቸዋል፡፡እስረኞቹ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ኹኔታ ፖሊስ ያረቀቀውን የእምነት ክህድት ቃል ተገደው እንዲፈርሙ አድርጓቸዋል፡፡
የሦስቱ ብሎገሮች አቤል ዋበላ፣በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን ቀጠሮ ለዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ የሚል የነበረ ሲኾን ከጠዋት ጀምሮ ችሎቱን ለመታደም የመጣውን ቤተሰብ፣ጓደኞቻቸው፣ጋዜጠኞች፣ዲፕሎማቶችና የወጣቶች ደጋፊዎች በአጠቃላይ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጋ ሰው ከችሎት ውስጥ የሚሰማውን አዲስ ነገር ለመጠበቅ በግቢው ውስጥ ቆመው ነበር፡፡ ከጠዋቱ አራት ሰዓት አካባቢ የእስረኞቹ ጠበቃ አቶ አመኃ መኮንን ተጠርተው የመዝግብ ቤት ጸሐፊዋ ስለሌለች ችሎቱ ለከሰዓት በኋላ እንደተዛወረ ይነገራቸዋል፡፡ እርሳቸውም ችሎቱን ለመከታተል ለቆመው ሰው መልዕክቱን ያስተላልፋሉ፡፡ ጥቂት ሰዎችም ይህን መልዕክት ሰምተው ግቢውን ለቀው ይወጣሉ ብዙኃኑ ግን እዛው እንደቆሙ መጨረሻውን ለማየት መጠባበቅ ይጀምራሉ፡፡
የሦስቱ ብሎገሮች አቤል ዋበላ፣በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን ቀጠሮ ለዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ የሚል የነበረ ሲኾን ከጠዋት ጀምሮ ችሎቱን ለመታደም የመጣውን ቤተሰብ፣ጓደኞቻቸው፣ጋዜጠኞች፣ዲፕሎማቶችና የወጣቶች ደጋፊዎች በአጠቃላይ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጋ ሰው ከችሎት ውስጥ የሚሰማውን አዲስ ነገር ለመጠበቅ በግቢው ውስጥ ቆመው ነበር፡፡ ከጠዋቱ አራት ሰዓት አካባቢ የእስረኞቹ ጠበቃ አቶ አመኃ መኮንን ተጠርተው የመዝግብ ቤት ጸሐፊዋ ስለሌለች ችሎቱ ለከሰዓት በኋላ እንደተዛወረ ይነገራቸዋል፡፡ እርሳቸውም ችሎቱን ለመከታተል ለቆመው ሰው መልዕክቱን ያስተላልፋሉ፡፡ ጥቂት ሰዎችም ይህን መልዕክት ሰምተው ግቢውን ለቀው ይወጣሉ ብዙኃኑ ግን እዛው እንደቆሙ መጨረሻውን ለማየት መጠባበቅ ይጀምራሉ፡፡
የከፍተኛ 15 ቀይሽብር ተዋንያን ከፍያለኝ ዓለሙ 22 ዓመት እሥራት ተፈረደበት
ቀን ፡ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ ሺህ ፮ ዓ.ም. (May 23, 2014)
ከ«ያ ትውልድ ተቋም» የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
የከበረ ሰላምታችንን በቅድሚያ አያቀረብን፤
May 23, 2014 (ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ ሺህ ፮ ዓ.ም.) በሰሜን አሜሪካ
ዳንቨር ኮልራድ የአረመኔውን ከፍተኛ 15ቱ ቀይ ሽብር ተሳታፊ
ከፋለኝ ዓለሙን ጉዲይ የመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የፍርድ ቤቱ
ችሎት ከጠዋቱ 9፡30 ተሰየመ። ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩት ጠበቆችና
የሚመለከታቸው ተገኝተዋል። ከፋለኝ ዓለሙን ለመጀመሪያ ጊዜ
በዳንቨር ኮልራድ በመመልከት ወደ ፍርድ ይቀርብ ዘንድ ከፍተኛውን
ድርሻና ኃሊፊነት የተወጣው የዳንቨሩ ነዋሪ አቶ ክፍለ ከተማን ጨምሮ
በነሐሴ ፬ ቀን ፪ ሺህ ፭ ዓ.ም. በዳንቨር በተካሄደው የፍርድ ቤት ውሎ
በአካል በመገኘት በከፋለኝ ዓለሙ በከፍተኛ 15 እሥር ቤት በ1970/71
ዓ.ም. በጊዜው ወጣቶች፣ ሕፃናትና አዛውንቶች ላይ የፈጸመውን
አሰቃቂ ግርፋት፣ ግፍና ግድያ በመመስከር ተገኝተው የነበሩት ወ/ሮ
አበበች ደምሴ ከሳንሆዜ፣ አቶ ብርሃን ዳርጌ ከዋሽንግተን ዲሲ፣ ድር ሳሙኤል ከተማ
ከዳንቨር እና አቶ ነሲቡ ስብሐት ከቨርጂንያ ሲገኙ አቶ አሳየኸኝ ፈለቀ ከቦስተን በሥራ
ምክንያት አልተገኙም።
Thursday, 26 June 2014
አብዛኛው ህዝብ ለመንግስት ጥላቻ አለው” ሲል አንድ ከኢህአዴግ የወጣ ሰነድ አመለከተ
ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ለሚገኙ አመራሮችና አባላት የተደረገውን ስልጠና አስመልክቶ ከብአዴን ጽህፈት ቤት በቁጥር ብአዴን 145/10/ኢህ/06 ለኢህአዴግ ጽ/ቤት አዲስ አበባ በሚል የተጻፈው ደብዳቤ “አብዛኛው ህዝብ አሁንም ለመንግስት ከፍተኛ ጥላቻ” ማሳየቱን ገልጿል።
የብአዴን አመራር እና አባላቱ ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ አለመምጣቱን፣ ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ግድ እንደሌላቸው፣ እንዲሁም መንግስትን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ በሰነዱ ላይ ተዘርዝሮ ቀርቧል።
“የኢትዮጵያ ህዝቦችና አገራዊ ህዳሴያችን” በሚለው የማጠቃለያ ግምገማ ሰልጣኞቹ ” ስለአገራቸው ታሪክ ብዙ ትምህርት መቅሰማቸውን፣ የህዳሴውን ጉዞ ለማሳካት ድርጅቱ እየከፈለ ያለውን መስዋትነት፣ የኢትዮጵያ ገናና ስልጣኔ ለምን እንደወደቀ፣ የህዳሴ ጉዞውን ሊያሳካ የሚችል መንግስት ያለ መሆኑን፣ የብዝህነትና እኩልነት ሀገራዊ ጠቀሜታ ፣ የአማራ ገዢ መደብ ሌሎች ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ብቻ ሳይሆን አማራውን ጭምር እንደጨቆነ” የሚያሳይ ትምህርት መውሰዳቸውን ሰነዱ ያመለክታል።
Subscribe to:
Posts (Atom)

