BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Friday, 8 November 2013

በረከት ስምኦን የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ቦርድ ኃላፊነቱን ቦታ ለሬድዋን ሁሴን አስረከበ




የወያኔዉ ፓርላማ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊነት ያቀረበዉን ሹመት ተቀብሎ ማጸደቁ ተሰማ። ይህ አንቅልፋምና ከአገዛዙ የቀረበለትን ነገር ሁሉ ከማጽደቅ ዉጭ ሌላ ምንም አይነት አማራጭ እንዳለዉ እንኳን የማያዉቀዉ ፓርላማ የኢትዮጵያን ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለረዥም ጊዜ በቦርድ ኃላፊነት የመራዉ በረከት ስምኦን በሬድዋን ሁሴን እንዲተካ የቀረበለትን ጥያቄ እንዳለ ተቀብሎ አጽድቋል። ሹመቱ በአማካሪዎችም ሆነ በካቢኔ ደረጃ ምንም አይነት ዉይይት ሳይካሄድበት በድንገት የተደረገ ሲሆን በዚሁ ሬድዋን ሁሴን በሚመራዉ ቦርድ ዉስጥ በቅርቡ ለረዥም ጊዜ ካገለገለበት የብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃላፊነቱ ተነስቶ በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የሕዝብ ተሳትፎ አደረጃጀት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆነው የተሾመዉ ደስታ ተስፋውና አማኑኤል አብርሃም፤ ዓቢይ መሐመድ ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል፣ አቶ ገበየሁ በቀለ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አባል፣ መጋቢ ዘሪሁን ደጉ ከእምነት ተቋማት ፣ አቶ ዘርዓይ አስገዶም ከኢቲቪ የቦርዱ አባላት በመሆን ተሹመዋል። የፓርማዉ አባልና በተሰናባቹ የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ በአባልነት ያገለገሉ አንድ ስማቸዉ እንደነገር ያልፈለጉ ግለስብ የፓርላማዉን ሹመቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ሹመቱ ግልጽነት የጎደለው መሆኑን በመጥቀስ ማብራሪያ እንዲሰጣቸዉ ጠይቀዋል። እንደእሳቸው አባባል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተጠሪ የሆኑ የመንግሥት የሚዲያ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መሆናቸውን በማስታወስ ለሁለቱ ተቋማት 4ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሹመት መስጠቱን አስታውሰዋል። ይህንኑ ማብሪያያ ይሰጠኝ በሚል ከፓርላማዉ የተነሳዉን ጥያቄ የፓርላማዉ አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ጠ/ሚኒስትሩ በማንኛውም ጊዜ ሚኒስትሮችን ሲያነሱ ማብራሪያ እንደማይጠየቁ ሁሉ የቦርድ አባላትንም ሲሰየሙ ማብራሪያ ለመስጠት እንደማይገደዱ በመናገር አግባብ ያለዉን ጥያቄ በተለመደዉ የቃላት መዶሻዉ ደብድቦት አልፏል።

Ginbot 7 November 2, 2013 

Tuesday, 5 November 2013

ግንቦት 7 አድባር ትከተልህ!

November 4, 2013
ይሄይስ አእምሮ
ምን ብዬ ከየት እንደምጀምር አላውቅም፡፡ ሁሉም ነገር ተምታትቶብኛል፡፡ መፈጠሬ ራሱም አስጠልቶኛል፡፡
ግንቦት ሰባት ሆይ! እንደሰውም እንደድርጅትም ልብ ብለህ ስማኝ! በቃ፤ በቃ ማለት በቃ ነው፡፡ ከሰሞነኛ አንድ ኢትዮጵያዊ ውርደት በኋላ አቋሜን ሙሉ በሙሉ ለውጫለሁ፡፡ እናም በስሜት ግንቦት ሰባት ሆኛለሁ፤ በተግባርም እሆናለሁ፡፡ ያበጠው ይፈንዳ፡፡ ማንም በኔ አያገባውም፡፡ ግንቦት ሰባት የማይሆንን ተቋምም ይሁን ግለሰብ አወግዛለሁ – የማወግዘው የኔም የቤተሰቤም ውርደት እንዲቀጥል ፈቃደኛ መሆኑን ከመገንዘብ አኳያ ነው፡፡ በወጡ ሳይወጠወጥ የሥልጣን ጥማቸውን የውይይት መድረክ ላይ ፊጥ የሚያደርጉ ዜጎች ከአሁን በኋላ አንደበት የላቸውም፡፡ መድረክ ላይ መደስኮር ሌላ ነው – እኛ ያለንበትን መከራና ስቃይ ማጤን ደግሞ ሌላ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ ግንቦት ሰባትን የሚቃወም የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት እንደሆነ አድርጌ እወስዳለሁ፡፡ አሁን የራሴ እንጂ የማንም አፈቀላጤ አይደለሁም፡፡  ብርሃኑ ነጋን በግል መጥላት ይቻላል፡፡ አንዳርጋቸው ጽጌን በግል መጥላት ይቻላል፡፡ ኤፍሬም ማዴቦን በግል ማጥላት ይቻላል፡፡ ሌሎቹንም የድርጅቱን ሰዎች መጥላትና ሲያጠፉም መገሰጽ ይቻላል፡፡ ግንቦት ሰባት አንግቦት የተነሣውን ዓላማ ማውገዝና መጥላት ግን የወያኔ አባል – ደጋፊ አላልኩም – የወያኔው ቀንደኛ አባል መሆንን በጉልህ የሚያመለክት ነው፡፡ እዬዬም ሲዳላ ነው፤ ዕንባም የሚመጣው ሲመች ነው፡፡ ምርጫም አማራጭ ሲኖር ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ቀልድ አብዝተናል፡፡ በተለይ በስደት ዓለም እየተንፈላሰስን የምንኖር ኢትዮጵያውያን በሕዝብ ቁስል እንጨት ብቻ ሣይሆን ጨውና ሚጥሚጣ እየጨመርን በሚመር ቀልድ መዝናናት ቀጥለናል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን የቄሣርን ለቄሣር የእግዜርን ለእግዜር ብለን እንነሳለን፤ አላጋጮችንና አምቧታሪዎችን እናጋልጣለን፡፡ በሕዝብ ስቃይ ደስታን የሚገዙ ሀዘን አምላኪዎችን ዝም ማለት ለተጨማሪ ሰቆቃ ከመዳረግ በስቀር አይጠቅመንምና ዝም አንበላቸው፡፡ የተከፋፈለች መንግሥት አትጸናም፡፡ እውነት ነው፡፡ መከፋፈላችን ከየት ወደየት እንዳመጣን እያየን ነው፡፡ ስለዚህ በረት በጥባጭ ኮርማዎችንና ወይፈኖችን በተቻለ መጠን አውግዘን እንለያቸው፡፡ በሕዝብ ስም የዐዞ ዕንባ ማንባት ሊቀር ይገባዋል፡፡

Ethiopia’s New PM and the Succession deal

nm
by Leta T. Bayissa (OPride)–
I would like start by congratulating Ethiopia’s newly appointed Prime Minister, Hailemariam Desalegn, on breaking that country’s political glass ceiling, and achieving an unforeseen success. Desalegn’s meteoric rise to the highest office in the land is historic in many respects.
Desalegn hails from a marginalized ethnic minority, the Wolayta, who occupy low social status and are seen as inferiors by powerful groups from the north. Given his marginal political base within the ruling elite, protestant background, and Ethiopia’s history where political power is dominated by Orthodox northerners, Desalegn’s emergence is inconceivable.
Hailemariam’s prominence is credited to the late dictator, Meles Zenawi. But in a lot of ways, his selection by Zenawi’s heirs was also a political gamble. By appointing Zenawi’s deputy, EPRDF, Ethiopia’s ruling party, is seeking to register a rather unusual history of peaceful transfer of power in Ethiopia. The exercise, they say, marks the dawn of a new era for Ethiopia by sending a signal that Ethiopia’s multi-ethnic federalism is now deeply rooted.
EPRDF’s posturing is also aimed at cementing the end of a long-drawn succession talks and rumors of power struggle. However, the TPLF, Zenawi’s mother party, didn’t really choose Hailemariam out of its own volition. Desalegn was needed to placate the mounting anecdotes of likely fallout among core TPLF elites.
Zenawi’s divided legacy

ሰማያዊ ፓርቲ 

Semayawi Party


Semayawi party
One more chance to unite Ethiopians for Democracy::

ራዕይ፣ ተልዕኮና ዓላማ


የሰማያዊ ፓርቲያችን ፕሮግራም የፓርቲያችንን ራዕይ፣ ተልዕኮና ዓላማ እንደሚከተለው በዝርዝር አስፍሯል፡፡


ራዕይ



የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ የተከበሩባት፤ ለሕዝብ ፍላጎት መሟላት በኃላፊነትና በተጠያቂነት መንፈስ የሚሰራ መልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፤ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ ብልፅግና የሰፈነባት፤ ለዜጎቿ ሁሉ አለኝታና መኩሪያ የሆነች፤ለዓለም ሕዝብ መልካም ግንኙነት የበኩሏን አስተዋፅዖ የምታደርግ ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡

ዓላማ



ሀ.     የዜጎች ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩና ተፈፃሚም ኢንዲሆኑ በጽናት መቆም፡፡
ለ.     ለዜጎች አስተማማኝ የማሕበራዊ ደህንነት ዋስትና አገልግሎት ማቅረብ፡፡
ሐ.     በኢትዮጵያ ፈጣንና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ፡፡
መ.    የፖለቲካ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ነፃ፣ ፍትሃዊና ትክክለኛ በሆነ መንገድ ተወዳድረው የፖለቲካ  ሥልጣን የሚይዙበት የምርጫ ሥርዓት መመስረት፡፡
ሠ.     ራዕዩን ተግባራዊ ለማድረግ በነፃና ፍትኃዊ ምርጫ በህዝብ ድምፅ የፖለቲካ ሥልጣንመያዝ
ረ.     ሀቀኛ፣ ብቃትና ተጠያቂነት ባለው አመራር አማካኝነት ታታሪና የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ዜጎች መፍጠር፡፡
ሰ.     የሕብረተሰቡን የፖለቲካ ግንዛቤ በማሳደግ ዜጎች በሃገራቸው ጉዳይ በንቃት እንዲሳተፉ፣ ግዴታቸውንና ኃላፊነታቸውንም እንዲወጡ ማድረግ፡፡
ሸ.     የእያንዳንዱን ዜጋ ችሎታ በማሳደግ በሃገርና በዓለም ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን ያለውን  ምኞት ማሳካት፡፡
ቀ.     ከሀገራቸው ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊና ቁሳዊ አቅማቸውን ለሃገራቸው ልማት እንዲያውሉና ለሕዝብም ቁሳዊና መንፈሳዊ ሕይወት መሻሻል የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ማበርከት የሚችሉበት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ሥርዓት መመስረት፡፡
በ.     ዓለምን ለመረዳትም ሆነ የዓለም ሕብረተሰብ በአግባቡ እንዲረዳው ማድረግ የሚችልና በነፃነት የሚያስብ ሕብረተሰብ መመስረት፡፡
ተ.     የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ በራሱና በወረሰው መልካም ነገር እንዲኮራና በሕይወቱ ውስጥ ተስፋ እንዲኖረውና ለከፍተኛ ግብ እንዲሰራ ማደፋፈር፡፡

ተልዕኮ



ተልዕኮአችን ዓላማችንን ማሳካት ሆኖ በተለይ በሀገራችን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍንና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ዋስትና የሚሰጥ ከሕዝብ፣ በሕዝብ፣ ለሕዝብ የቆመ መንግስት በሰላማዊ መንገድ መመስረት ነው፡፡

ሀገራዊ ዕይታ



ሀ.     ኢትዮጵያ ሀገራችን በኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ ገዥነት ስር የሚገኘውን መሬት፣ ውሃ፣ የአየር ክልል፣ በከርሰ ምድርና በከርሰ ውኃ የሚገኘው ሃብት፣ በአየር ክልሉ ያለው የድምፅና የምስል ሞገድ ባለቤት ሉዓላዊ ሀገር ናት፡፡
ለ.     የኢትዮጵያ ያልተመለሱ የድንበርና የይገባኛል ጥያቄዎች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ የአስተዳደር ወሰን አሁን በኢትዮጵያ መንግስት ሥር የሚገኘውና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተመዘገበዉ ክልል ነው፡፡
ሐ.     በኢትዮጵያ ውስጥና በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአንድነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ናቸው፡፡
መ.    የኢትዮጵያ ሕዝብም በኢትዮጵያ ጉዳይ ባለሙሉ የሥልጣን ባለቤት ነው፡፡ ሃገሪቱን የማስተዳደር ሥልጣን ከሕዝብ ይመነጫል፡፡
ሠ.     የኢትዮጵያ አንድነትም ሆነ ሉዓላዊነት አይነጣጠሉም፤ለሌላም አይለቀቁም፡፡
ረ.     ኢትዮጵያውያን በግል ያላቸው የዜግነት መብትም ሆነ በወል የሚጋሩት የህግ፣       የፖለቲካ  የማህበራዊና የባህል መብት የአንድነታቸው ዓይነተኛ መሰረት ነው፡፡
ሰ.     ኢትዮጵያ ሀገራችን የረጅም ጊዜ አኩሪ ታሪክ፣ የበርካታ ገፀ-ምድርና  ከርሰ-ምድር ሃብት ባለቤት፣ አስደናቂ የተፈጥሮ ውበትና የሰው ልጅ ቀደምት ሥልጣኔ መገለጫ
የሆኑ ቅርሶች ያሏት ታላቅ ሃገር ናት፡፡
ሸ.     ሃገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ባህል፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ ወግና ሥርዓት አሸብርቃ የኖረች፣ በብዙ ዓይነት ሃረጎች ተሳስረውና በታሪክ ተቆራኝተው የጋራ አመለካከትና ኢትዮጵያዊ ማንነትን በማዳበር ለዘመናት ተቻችለውና ተከባብረው በአንድነት የኖሩ ዜጎች ሃገር ናት፡፡ እነዚህ ዜጎች በየዘመናቱ የተለያዩ አስተዳደራዊ በደልና ጭቆና ደርሶባቸዋል፡፡ ዛሬም ቢሆን የዜጎች የአስተዳደርና የፍትህ ጥያቄ በአግባቡ አልተፈታም ወይም መብታቸው አልተከበረም፡፡ በመሆኑም ሁሉም ዜጎች የዜግነት መብታቸው እንዲከበርና በሃገር ጉዳይ ላይ ተገቢው ድርሻና ተሳትፎ እንዲኖራቸው አሁንም ፅኑዕ ትግል የሚያስፈልጋት ሃገር ናት፡፡

ርዕዮተ ዓለም



እጅግ ውድ የሆነው የሰው ልጅ ሃብት ነፃነቱ በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ለግለሰብ ነፃነት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ ዜጎች በቡድን ሊያከናዉኗቸው የሚፈልጓቸው እንደ ሃይማኖት፣ ልማዶች፣ ቋንቋ፣ ማህበሮች እና የመሳሰሉት የጋራ መብቶች የግለሰብን በነፃነት የመወሰን መብት ሳይሸረሽሩ እንዲከበሩ የህግ ጥበቃ እንደሚያስፈልጋቸው ያምናል፡፡ በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ በለዘብተኛ ሊብራል ዲሞክራሲ መሰረታዊ መርሆች ይመራል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ለመለስ ፋውንዴሽን ጆሮዉንም አይኑንም አንደነፈገ ታወቀ


የህወሀት መስራችና የረጂም ግዜ መሪ የነበረዉ ዘረኛዉ መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት በተለየ በስምንት ወሩ ባለፈዉ መጋቢት መጨረሻ ላይ ይፋ ሆኖ የተመሰረተዉ የመለስ ፋውንዴሽን ከህዝብ ያገኛል ተብሎ የተገመተዉን የገንዘብ መዋጮ የሩቡን ግማሽም አለማግኘቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በሰልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገለጹ፡፡ በመለስ ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 781/2005 መንግስታዊ ተቋም ሆኖ የተመሰረተው ይህው ፋውንዴሽን ቤተመጻህፍትና ሙዚየም ለማቋቋም በማሰብ ሕዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ በየቀኑ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ቅስቀሳ ከተጀመረ ከአምስት ወራት በላይ ቢቆጠርም እየተዋጣ ያለው ገንዘብ እጅግ አነስተኛ መሆኑ ታውቋል፡፡

ህዝብ በያለበት ለመለስ ፋዉንዴሺን የገንዘብ መዋጮ ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆነዉ ፋውንዴሽኑን በበላይነት የምትመራዉና የሙስናዋ እመቤት በመባል የምታወቀዉ አዜብ መስፍንና ሟቹ ባለቤቷ ከህዘብ ዘርፈዉ በውጪ አገር ባንኮች ከፍተኛ ገንዘብ ማከማቸታቸዉን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና በውጪ አገር የሚገኙ የኢትዮጽያ መገናኛ ብዙኋን በተደጋጋሚ በመዘገባቸዉ እንደሆን ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ። ከዚህ በተጨማሪ አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛና የግሉ ዘርፍ ለህዳሴዉ ግድብ ገንዘብ እያዋጡ መሆናቸዉና ህዝቡ መለስ ዜናዊን ለመሰለ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ለረገጠዉ ጨቋኝና ከፋፋይ ሰዉ የገንዘብ መዋጮ ማድረግ ባለመፈለጉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የአዲሰ አበባ ምንጫችን ጨምሮም እንደገለጸዉ መዋጮው በውዴታ በባንክ ገቢ የሚደረግና ለጋሹ ስሙን ከማስመዝገብ በላይ መስጠትና አለመስጠቱ የማይታወቅ በመሆኑ ከፍተኛ የግንባሩ ካድሬዎችና ራሳቸውን የኢህአዴግ ደጋፊ ባለሃብቶች ነን የሚሉት ሳይቀሩ ለመዋጮው እጃቸውን አለመዘርጋታቸው መረጃው ያሳያል።

G7 November 2, 2013

የወያኔ ፍትሻ ባህርዳርንና ኗሪዎቿን አማረረ


የዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ካድሬዎች፤ ፖሊሶችና የጸጥታ ሀይሎች ለግዜዉ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በባህርዳር ከተማ ዉስጥ ከፍተኛ ፍተሻ እያካሄዱ መሆኑን ባህርዳር ዉስጥ የሚገኙ የግንቦት ሳበት ድምጽ ዘጋቢዎች በስልከ በላኩልን ዜና ገለጹ። በተላይ ከሳምንቱ መግቢያ እስከ ሳምንቱ አጋማሽ በነበረዉ ግዜ ዉስጥ በከተማዋ መውጪያና መግቢያ በሮች ላይ የጸጥታ ሀይሎች ተሳፋሪዎችን ከአዉቶቡሶችና ከግል መኪናዎች ዉስጥ በግድ ጎትተዉ እያወረዱ ጥብቅ ፍተሻ አንዳደረጉባቸዉ ለማወቅ ተችሏል። አዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ይህንን የወያኔ በድንገት የመጣ ፍተሻ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ ከመጣዉ የአማጽያን እንቅስቃሴ ጋር ሲያያይዙት ሌሎች ደግሞ በቅርቡ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የደረሰዉን አይነት የቦምብ ፍንዳታ ከወዲሁ ለመከላለክ ነዉ ይላሉ፤ ሆኖም እንዚህ ወገኖች አገዛዙ ለምን ባህርዳር ላይ እንዳተኮረ የሰጡት ምንም አይነት ምክንያት የለም።


የጸጥታ ኃይሎቹ በሚያካሂዱት ፍተሻ ባህርዳርና አካባቢዋ ዉስጥ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ስራና ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች የተስተጓጓሉ ሲሆን ህዝቡም በከፍተኛ ደረጃ እየተንገላታ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች በመናገር ላይ ይገኛሉ። የወያኔ አገዛዝ በህዝብ ላይ ለመፈጸም ለማያስባቸዉ ጭፍጨፋዎች ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት እንዲህ አይነት እርምጃ መዉሰዱ የተለመደ ነዉ ያሉት አንድ ስማቸዉ እንዲገለጽ ያልፈለጉ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን ይስ የሰሞኑ የባህርዳር ፍተሻ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ አገዛዙን በማስጨነቅ ላይ ያለዉን የወጣቶች እንቅስቃሴ ለማፈንና አባላቱን ለመግደል የታቀደ እንደሆነ ገልጸዋል። ዊኪሊክስ የተባለዉ ሚስጢር አጋላጭ ድርጅት የዛሬ ሁለት አመት ይፋ ያደረገው መረጃ በግልጽ እንዳሳየዉ የአሜሪካ ኢምባሲ የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ የሽብር አደጋ አለ ለማስባል ሆን ብሎ ፍንዳታዎችን ያቀናብራል ብሎ እንደሚያምን መግለጹ ይታወሳል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ በባህርዳር አንድ የባጃጅ ሹፌር በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ ተገኝቷል። በወጣትነት እድሜ ክልል የሚገኘዉና የቀበሌ 7 ነዋሪ የሆነው ይህ ወጣት በከፍተኛ ሁኔታ የተደበደበ ከመሆኑም በላይ ሁለት አይኖቹ በአሳቃቂ ሁኔታ ወጥተዉ ከተጣለበት ቦታ ከሁለት ቀ አይኖቹ ወጥተው ከቀናት በሁዋን በኋላ ነው በፍለጋ የተገኘዉ። ኢሳት ሬድዮና ቴሌቪዥን በግድያዉ ዙሪያ የባሀርዳርን ፖሊስ ኮሚሽን ለማናገር ያደረገዉ ሙከራ እንዳልተሳካ ለማወቅ ተችሏል።
 G7 November 2, 2013

Monday, 4 November 2013

                   ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ይሏታል ጅግራ


ባለፈዉ ዐርብ መስከረም 25 ቀን 2006 ዓ.ም. የወያኔዉ ሎሌ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አዲስ አበባ ዉስጥ ለአገር ዉስጥና ለዉጭ አገር ጋዜጠኞች በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በየእሁዱ ለሚጠሩት ሰልፍ ጥበቃ ማድረግና በየእሁዱ ተመሳሳይ ጥያቄ ማድመጥ መንግስትን ከሚገባዉ በላይ ያሰለቸዉ ስለሆነ እነዚህ አንድ አይነት ጥያቄ ያነገቡ ሰልፎች የሚቀጥሉ ከሆነ የተቃዉሞ ሰልፍ ማድረግ ይከለከላል በማለት ጌቶቹና ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች የመብትና የነጻነት ጥያቄ የሚያነሳ ማንንም ሰዉ ለማሰር፤ ለመደብደብና ለመግደል ያላቸዉን እቅድ በግልጽ ተናግሯል። የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ባቀረቡ ቁጥር መሪዎቻቸዉ የሚታሰሩባቸዉ፤ አባላቶቻቸዉ የሚደበደቡባቸዉና ቢሯቸዉ ተሰብሮ ንብረታቸዉ የሚዘረፍባቸዉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች አንድም ቀን ሰለቸን ሳይሉ ደብዳቢዉ፤ አሳሪዉና የተቃዋሚ ድርጅቶችን ቢሮ እየሰበረ ንብረታቸዉን የሚዘርፈዉ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍ “ሰለቸኝ” ማለቱ ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረግ ምንም አይነት ትግል የሱን የስልጣን “ዘለአለማዊነት” የሚጻረር መስሎ ከታየዉ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ የማይመለስ ፀረ ህዝብ ኃይል መሆኑን እንደገና አረጋግጧል።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም ቤት ውስጥ ሆነው ይጠይቁት የነበረውን ጥያቄ አሁን አደባባይ ወጥተዉ መጠየቅ መቻላቸዉ ዲሞክራሲያዊ ስኬት ነው ያለዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በሌላ በኩል ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ በችርቻሮ የሚሰጥ የወያኔ ችሮታ ይመስል ሰልፉ በየእሁዱ የሚቀጥል ከሆነ ሰልችቶናልና እንከለክላለን ማለቱ እንደ ግንቦት 7 እምነት ቀድሞዉንም ቢሆን ወያኔ ሰላማዊ ሠልፍ ማድረግ ይቻላል ብሎ ፈቃድ የሰጠዉ ለዲሞክራሲ ካለዉ እይታና እራሱ የጻፈዉን ህገ መንግስት ተከትሎ ሳይሆን እርዳታ ሰጪ ምዕራባዉያን አገሮችን ለማስደሰት ብቻ ነዉ።
አገር ዉስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከቅርብ ግዜ ወዲህ የተቀናጀ ትግል ማድረግ በመጀመራቸዉ ክፉኛ የተደናገጠዉ ወያኔ “ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” አንደሚባለዉ እነዚህን ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ፤ እኩልነትና፤ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የሚታገሉትን ፍጹም ህዝባዊና ፍጹም ሰላማዊ የሆኑ ድርጅቶች ለማጥፋት ሰበብ ሲፈልግ የተለመደዉን ግንቦት 7 የሚል ዘፈኑን መዝፈን ጀምሯል። የወያኔ አገዛዝ በአፉ አንደሚናገረዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስብና የሚጨነቅ ከሆነ ማድረግ ያለበት ከኢትዮጵያ ህዝብ ለሚቀርብለት ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ መስጠት ብቻ ነዉ። አለዚያ ህዝብ ጥያቄ ባነሳና ለመብቱና ለነጻነቱ በታገለ ቁጥር የሐይማኖት አክራሪዎች፤ የቀድሞ ስርዐት ናፋቂዎች ወይም የግንቦት ሰባት ተከታዮች ናችሁ እያለ ቢያቅራራ እንዲህ አይነቱ የተለመደ የአምባገነኖች ቀረርቱ ያ የማይቀረዉ ክፉ ቀን ሲመጣ ስንቅ እንደማይሆነዉና ከህዝባዊ ቁጣ እንደማያድነዉ ከወዲሁ ሊገነዘብ ይገባል። ደግሞም ግንቦት 7 አላማዉ፤ ለህዝብ ያለዉ ክብርና ለኢትዮጵያ አንድነት ያለዉ ቀናኢነትና የማያወላዉል አቋም በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ በአጭር ግዜ ዉስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አስገኝቶለታልና የወያኔን የዕለት በዕለት አስተዋዋቂነት በፍጹም አይሻም።
ግንቦት 7 አላማዉና ፍላጎቱ እንደ ስሙ ፍትህ፤ ነጻነትና ዲሞክራሲ ነዉና የህዝባዊ ትግላችን አላማ ወያኔንና ዘረኛ ስርዐቱን መደምሰስ ብቻ ሳይሆን አገራችን ዉስጥ የህግ የበላይነት ሰፍኖ ኢትዮጵያ ዛሬም ነገም ከሽብርተኝነት የነጻች አገር አንድትሆን ነዉና ወያኔ ያሰኘሰዉን ቢናገር ወይም እንዳሰኘዉ ቢፎክር ንቅናቄያችን ከዚህ ህዝባዊ አላማዉ ንቅንቅ እንደማይል ለወገንም ለጠላትም ማረጋገጥ ይፈልጋል። ግንቦት 7 የኢትዮጵያና የህዝቦቿ ዋነኛ ጠላት ወያኔ ነዉ ብሎ ያምናል፤ ስለሆነም የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ክንድ ያነጣጠረዉ በዚሁ በዋነኛዉ የህዝብና የአገር ጠላት ላይ ብቻ እንደሆነ ኢትዮጵያዉያንና ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ብልጽግና የሚመኙ ሁሉ እንዲገነዘቡለት ይፈልጋል።
ግንቦት 7 ህዝባዊ አላማ አንግቦ፤ ግብ አስቀምጦና ወዳስቀመጠዉ ህዝባዊ ግብ የሚያደርሰዉን የትግል ስልት በጥንቃቄ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ነዉ። ግንቦት 7 ወያኔና ዘረኛ ስርዐቱ ተደምስሰዉ ኢትዮጵያ በዜጎቿ ሙሉ ፍላጎትና ፈቃድ ብቻ የምትመራ አገር የመሆኗ ሀቅ የማይቀርና ምንም አይነት ምድራዊ ኃይል ገድቦ ሊያቆመዉ የማይችል ህዝባዊ ማዕበል ነዉ ብሎ ያምናል። ግንቦት 7 በዚህ አጋጣሚ በየዋህነት ተሳስተዉና ግዜያዊ ጥቅም አታሏቸዉ ከሚንቋቸዉና እንደ ቤት ዉስጥ ዕቃ ከሚጠቀሙባቸዉ ዘረኞች ጋር እጅና ጓንት የሆኑ እንደ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አይነቶቹ የዋሆች የበደሉትን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀዉ ህዝባዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ወገናዊ ጥሪ ያቀርብላቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ግንቦት 7 ባለፉት ሁለት አመታት በተለይም ከወያኔዉ ቁንጮ ሞት በኋላ ከወያኔ ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ዉስጥ የገባችሁ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችና በድርጅቶቹ ዉስጥ የምትገኙ የኢትዮጵያ ህዝብ ወገኖች ወያኔን ለማስወድ ከዛሬ የተሻለ ግዜ አይመጣምና ኑና በጋራ ጠላታችን ላይ እንዝመት የሚል ህዝባዊ ጥሪዉን ያስተላልፋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

  • facebook
  • google_buzz
  • twitter
  • rss
  • print
  • bookmark
  • email