የወያኔ ፍትሻ ባህርዳርንና ኗሪዎቿን አማረረ
የዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ካድሬዎች፤ ፖሊሶችና የጸጥታ ሀይሎች ለግዜዉ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በባህርዳር ከተማ ዉስጥ ከፍተኛ ፍተሻ እያካሄዱ መሆኑን ባህርዳር ዉስጥ የሚገኙ የግንቦት ሳበት ድምጽ ዘጋቢዎች በስልከ በላኩልን ዜና ገለጹ። በተላይ ከሳምንቱ መግቢያ እስከ ሳምንቱ አጋማሽ በነበረዉ ግዜ ዉስጥ በከተማዋ መውጪያና መግቢያ በሮች ላይ የጸጥታ ሀይሎች ተሳፋሪዎችን ከአዉቶቡሶችና ከግል መኪናዎች ዉስጥ በግድ ጎትተዉ እያወረዱ ጥብቅ ፍተሻ አንዳደረጉባቸዉ ለማወቅ ተችሏል። አዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ይህንን የወያኔ በድንገት የመጣ ፍተሻ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ ከመጣዉ የአማጽያን እንቅስቃሴ ጋር ሲያያይዙት ሌሎች ደግሞ በቅርቡ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የደረሰዉን አይነት የቦምብ ፍንዳታ ከወዲሁ ለመከላለክ ነዉ ይላሉ፤ ሆኖም እንዚህ ወገኖች አገዛዙ ለምን ባህርዳር ላይ እንዳተኮረ የሰጡት ምንም አይነት ምክንያት የለም።
የጸጥታ ኃይሎቹ በሚያካሂዱት ፍተሻ ባህርዳርና አካባቢዋ ዉስጥ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ስራና ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች የተስተጓጓሉ ሲሆን ህዝቡም በከፍተኛ ደረጃ እየተንገላታ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች በመናገር ላይ ይገኛሉ። የወያኔ አገዛዝ በህዝብ ላይ ለመፈጸም ለማያስባቸዉ ጭፍጨፋዎች ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት እንዲህ አይነት እርምጃ መዉሰዱ የተለመደ ነዉ ያሉት አንድ ስማቸዉ እንዲገለጽ ያልፈለጉ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን ይስ የሰሞኑ የባህርዳር ፍተሻ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ አገዛዙን በማስጨነቅ ላይ ያለዉን የወጣቶች እንቅስቃሴ ለማፈንና አባላቱን ለመግደል የታቀደ እንደሆነ ገልጸዋል። ዊኪሊክስ የተባለዉ ሚስጢር አጋላጭ ድርጅት የዛሬ ሁለት አመት ይፋ ያደረገው መረጃ በግልጽ እንዳሳየዉ የአሜሪካ ኢምባሲ የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ የሽብር አደጋ አለ ለማስባል ሆን ብሎ ፍንዳታዎችን ያቀናብራል ብሎ እንደሚያምን መግለጹ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በባህርዳር አንድ የባጃጅ ሹፌር በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ ተገኝቷል። በወጣትነት እድሜ ክልል የሚገኘዉና የቀበሌ 7 ነዋሪ የሆነው ይህ ወጣት በከፍተኛ ሁኔታ የተደበደበ ከመሆኑም በላይ ሁለት አይኖቹ በአሳቃቂ ሁኔታ ወጥተዉ ከተጣለበት ቦታ ከሁለት ቀ አይኖቹ ወጥተው ከቀናት በሁዋን በኋላ ነው በፍለጋ የተገኘዉ። ኢሳት ሬድዮና ቴሌቪዥን በግድያዉ ዙሪያ የባሀርዳርን ፖሊስ ኮሚሽን ለማናገር ያደረገዉ ሙከራ እንዳልተሳካ ለማወቅ ተችሏል።
G7 November 2, 2013
No comments:
Post a Comment