BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 26 November 2013

ጠጉረ ልውጥ የተባለው ያው አንዱ ሕዝብ አይደል?

ኢትዮጵያውያን ለተለያዩ ጉዳዮች በአገሪቱ ማለትም በሃገራቸው ይዘዋወራሉ፡፡ 

በተለይ በአዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መነሃሪያ ነች፡፡ ኢትዮጵያም ሆነች 

አዲስ አበባ ትንሽ መንደር አይደሉም፡፡ 



ስለዚህም የሰውን  ‹‹ጠጉረ ልውጥ›› መሆን አለመሆን እንዲሁ ማወቅ 

አይቻልም፡፡ ‹‹መንግስት›› የፈለገው ግን ይህኛውን አይደለም፡፡ 


በተቃራኒው ከእሱና ከደጋፊዎቹ አንጻር የ ‹‹ፖለቲካ ልውጥ››፣ የ‹‹ ብሄር 

ልውጥ››፣ የ‹‹እምነት ልውጥ›› ያላቸውን ነው በአጠቃላይ ከርሱ በተቃራኒ 

ያሉትን ነው ጠቁሙን የሚለው፡፡ 


ሽብር እንዲህ በወሬ ሳይጦዝ ከ30ና 40 አመት በላይ የኖሩትን አርሶ 

አደሮችንም ‹‹ጠጉረ ልውጥ›› አድርገው አፈናቅለው አባርረዋቸዋል፡፡ 

አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ 

እንዲህ ከሆነ ጠጉረ ልውጥ ያልሆነ የለምና ከጥቂቶቹ  በስተቀር 

ኢትዮጵያውያን በሙሉ እስር ቤት ውስጥ ሊታጎሩ ነው፦


*በትኩረት ለተመለከታት ኢትዮጵያ ኮ! ሙሉዋን እስር ቤት ሆናለች ። ። ።

No comments:

Post a Comment