BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 31 December 2013

በቁም እስር ላይ ያሉት ብጹእ ኣቡነ ማቲያስ አምጸዋል!!!

vv
ከአሜሪካን መልስ በደህንነት ቢሮ ለ72 ሰአታት ታስረው ነበር::

ትናንት ለሊት በአዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ

ትናንት ለሊት በአዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ አንድ ህንፃ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ ሆኗል.......


በደቡብ ክልል፣ በጋሞ ዞን በቁጫ ወረዳ፣ ከመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከ1ሺ በላይ ነዋሪዎች መታሰራቸውን “አንድነት” ፓርቲ ተቃወመ፡፡



ሙስናና ሥራ........


በኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ውስጥ በታየው ከፍተኛ የሙስና ወንጀል አገሪቱ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አጥታለች። ይህንን የሙስና አሰራር የተቃወሙት ስራ አስኪአጁ አቶ ምህረት ደበበ በመጨረሻ ከስልጣናቸው ተነስተዋል።


ምንጩ ከአንድ ደም.......... 


እኛ ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተውጣጣን የተለያዩ ቋንቋዎች የምንናገር የተለያየ ሀይማኖት ያለን ለዘመናት የተነሱብን 

አምባገነን አገዛዞች ነጻነት አሳጥተውን ከሰው በታች አድርገው ያዋረዱን መሆናችን አንድ ያደረገን ለነጻነታችን፣ 

ለሰውነት ክብራችን የቆምን ኢትዮጵያውያን ነን።

Monday, 30 December 2013


የወገን ጩኸቱን አናፍነው! ጩኸቱን አንቀማው!

ሰሞኑን ጠቃሚ መረጃ የምንለዋወጥባቸው ማህበራዊ ገጾቻችን በሙግት ንትርክ ማዕበል ተውጠው ተመለከትኩ … ከእምየ ምኒሊክ እሰከ በደሌ ቢራ ፣ ከድንቁ ትንታግ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ መግለጫ ፣ እርማት እስከተሰጠበት እንቁ መጽሔት ፣ ከታሪክ አዋቂው የሃገር ሽማግሌ ፕሮፊሰር ይስሐቅ የታሪክ ቀደምት ትንታኔ ታሪክ እስከ ማይጠቅመን የጁሃር መሃመድ ዘመቻ ሁሉም ሰሞነኛ ዝብሪት በየአይነቱ ሰማን ። ይህ ሁሉ ታዲያ በፈረንጆች አመት በዋዜማው ባይሆን ደስ ባለኝ! ይህም የእኛ ነገር ፣ የእኛ ኑሮ ነውና ምን ያደርጉታል?Ethiopians in Saudi Arabia suffering, December 2013
ባለሁበት የሳውዲ ምድር በአለም እንደ ጨው የተበተንን የዚያች ሃገር ዜጎችን ትኩረት ሳቢ ብቻም ሳይሆን አስጨናቂ ቀንን ተፋጦ ማወጫ ያጣ ወገን ጩኸት ደምቆ እንዳይሰማ የእኛ ነገር አልተመቸውም !

ኢኮኖሚያችን ሲያድግ የህዝቡ ኑሮ ለምን አሽቆለቆለ?

ላለፉት 8 እና ዘጠኝ ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሁለት አሃዝ አያደገ ነው ሲባል እንሰማለን፤  የእድገት ፍጥነቱ  ላይ የሚነሱ በርካታ ጥያቄውች  ቢኖሩም መንግስት  የመንገድ ግንባታ ፣ የኃይል ማመንጫ ግንባታወችን እና መሰል ነገሮችን  በመጥቀስ እድገት እንዳለ አስረግጦ ይከራከራል::  በሌላ በኩል የኢኮኖሚ እድገቱ ተመዘገበ በሚባልባቸው ዓመታት በዋጋ ንረት የህዝቡ ኑሮ ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆለ  እንደሆነ በግልፅ የሚታይ ነገር ነው:: ታዲያ  የኢኮኖሚ እድገት አለ በተባለባቸው ዓመታት የህዝቡ ኑሮ ለምን አሽቆለቆለ?

በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ

December 30, 2013

ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡፡

Saturday, 28 December 2013

Assassinating popular leaders will only invigorate the people



On Thursday November 7, 2013; the Valiant Ginbot 7 Popular Force intelligence unit foiled the assassination plot that targeted the secretary of Ginbot 7: Movement for Justice, Freedom and democracy, and commanders and high ranked officers of Ginbot 7 Popular Force. This futile attempt by the coward TPLF regime that took place in Eritrea territory is yet another sign and proof that this blood-stained regime cannot and does not survive without spilling the blood of innocent Ethiopians. Ginbot 7 and the Ethiopian people at large are outraged by the TPLF regime’s recent assassination attempt, and they strongly denounce this shameful act that does not serve any purpose.

Friday, 27 December 2013

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!


በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንምመከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።

የሰብዓዊ መብት ሚዛን ማጣት።

የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዉስጥ ባካሄደው ጥናት ባለፈዉ አመት ከክልሉ አማራ ናችሁ ተብለዉ በተባረሩ በብዙ ሺዎች በሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የክልሉ ባለስልጣኖችና የወያኔ የጸጥታ ኃይሎች የሰብአዊ መብት ጥሰት እና አካላዊ ጉዳት ማድረሳቸዉን አረጋገጠ። በክልኩ በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ቁጥራቸው ከ10 ሺህ በላይ የሚገመቱ ዜጐች ለረዥም አመታት ይኖሩበት ከነበረው አካባቢያቸው የዚህ ክልል “ተወላጆች አይደላችሁም” በማለት በሀይልና በግዳጅ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከመጋቢት 15/2005 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰደዱ መደረጋቸውን ተቋሙ አውስቷል፡፡

Thursday, 26 December 2013


በቦሌ ቡልቡላ፣ በለሚና እና በአቃቂ ክፍለ ከተማ በርካታ ህዝብ ሜዳ ላይ መውደቁ ተገለጸ

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደገለጹት ላለፉት 25 አመታት ከኖሩበት ቤት በጉልበት ተነሱ በመባላቸው ሜዳ ላይ ለመውደቅ ተገደዋል።
ነዋሪዎቹ ስሜታቸውን በከፍተኛ ሀዘን እየገለጹ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል። የመንግስትን እርምጃ በመቃወማቸው የተወሰኑ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁንም ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በአዳማም በተመሳሳይ መንገድ  ከ25 ሺ በላይ ህዝብ ቤት አልባ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።


በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በነጭ ሳር ግቢ የሚማሩ ከ25 ያላነሱ ተማሪዎች መታሰራቸው ታወቀ

Wednesday, 25 December 2013


  በደቡብ ሱዳን ተገደው የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን                         ሴቶች ጁባ ገቡ::

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ የተደፈሩ 4 ሴቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል በሚገኝበት ጁባ ደርሰው ምርመራ እየተደረገላቸው ነው። ሴቶቹ መደፈራቸውንና ሆስፒታል መግባታቸውን ለማረጋገጥ የtቻለ ሲሆን፣ ሴቶቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ አልtቻለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ታውቋል። አምባሳደሩ በዚህ አስቸጋሪ ሰአት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በአገሪቱ ያሉ ኢትዮጵያውያን ተችተዋል።

Thursday, 5 December 2013


በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ገበታው ላይ እያለ በወያኔ ታጣቂዎች በግፍ የተገደለው ወንድማችን ግድያ አጥብቀን እናወግዛለን! የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ወጣቶች ላይ በተደጋጋሚ እየፈፀመ ያለው የግፍ ግድያ, በኦሮሞ ህዝብ ላይ የከፈተው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካል ነው!


ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ በ1983 ዓ.ም በዲላ ዞን፣ ፍሰሀ ገነት ወረዳ፣ ቀበሌ 02 ተወለደ፡፡ ይህ ወጣት ተማሪ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የማርኬቲንግ ክፍል /department/ ተማሪ ሲሆን ወደ ዩኒቨርሲቲ በ2004 ዓ.ም የገባና በ2006 ዓ.ም ይመረቅ የነበረ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ህዳረ 24/2006 ዓ.ም ቁጥራቸው ከ60 በላይ ከሚሆኑ ከክፍሉ ተማሪዎች ጋር በመሆን ዳሽን ቢራ በተባለ ቦታ የግብዣ ፕሮግራም አድርገው ነበር፡፡ ከግብዣው ፕሮግራም በኋላ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ወደ ዩንቨርሲቲው ቅጥር ግቢ እየተመለሰ ሳለ የኦሮሞ ተማሪዎች ለብቻቸው ተነጥለው የትግል ዘፈኖችን እየዘፈኑ ይሄዱ ነበር፡፡ የሀበሻ ልጆችም አካባቢውን በጩኸት በመበጥበጥ በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ሰው ሁሉ ሲደበድቡ ነበር፡፡ የኦሮ ልጆች በወቅቱ የትግል ዘፈኖችን ከመዝፈን ውጪ ያነሱት ሁከት አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን ከዳሽን አለፍ ብለው “ቀሀ” የተባለውን ወንዝ ተሻግረው 18 ቀበሌ ሲደርሱ የሀበሻ ልጆች መንገዱ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የወያኔ ታጣቂዎች ላይ ድንጋይ መወርወር ጀመሩ፡፡