BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 31 December 2013



በደቡብ ክልል፣ በጋሞ ዞን በቁጫ ወረዳ፣ ከመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከ1ሺ በላይ ነዋሪዎች መታሰራቸውን “አንድነት” ፓርቲ ተቃወመ፡፡
በቁጫ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰው የመብት ረገጣ እንዲቆም ለማሳሰብ ሰላማዊ ሰልፍ አደርጋለሁ ብሏል፡፡ ከትላንት በስቲያ ፓርቲው በፅ/ቤቱ “የቁጫ ህዝብ ጥያቄ የሚፈታው የዜጎች መብት ሲከበር ነው” በሚል በሰጠው መግለጫ፤ በቁጫ ወረዳ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ እየተባባሰ በመምጣቱ፣ በፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሚመራ ቡድን ወደ ሥፍራው በመላክ መረጃ ካሰባሰበ በኋላ፣ በወረዳው ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋት መርምሮ ውሳኔ ማስተላለፉን ጠቁሟል፡፡ በፓርቲው ብሄራዊ ኮሚቴ ፀሀፊ እና የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል በአቶ ትእግስቱ አወል የተመራው ቡድኑ፤ በቁጫ ለአራት ቀናት ባደረገው የመረጃ ማሰባሰብ ስራ 1015 ሰዎች በሰላም በር ፖሊስ ጣቢያ፣ በአርባ ምንጭና በጨንቻ ወህኒ ቤቶች እንደታሰሩ ማረጋገጡ ተገልጿል፡፡ ህዳር 14 ቀን 2006 ዓ.ም አቶ ዛራ ዛላ የተባሉ የሁለት ልጆች አባት፣ ኮዶ ኮኖ በተባለ ቀበሌ ውስጥ በጥይት ተመትተው ህይወታቸው ማለፉን የገለፁት የቡድኑ መሪ፤ አባወራው በጥይት ሲመቱ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ የስጋት ሳንታ፣ የገዢው ፓርቲ የወረዳው ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ አሸብር ደምሴ እና የወረዳው የፀጥታ ሀላፊ አቶ አያኖ መለና በስፍራው እንደነበሩ ከአይን እማኞች መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment