ሙስናና ሥራ........
በኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ውስጥ በታየው ከፍተኛ የሙስና ወንጀል አገሪቱ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አጥታለች። ይህንን የሙስና አሰራር የተቃወሙት ስራ አስኪአጁ አቶ ምህረት ደበበ በመጨረሻ ከስልጣናቸው ተነስተዋል።
በኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ውስጥ በታየው ከፍተኛ የሙስና ወንጀል አገሪቱ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አጥታለች። ይህንን የሙስና አሰራር የተቃወሙት ስራ አስኪአጁ አቶ ምህረት ደበበ በመጨረሻ ከስልጣናቸው ተነስተዋል።
የህወሃቱ ነባር ታጋይ፣ የደህንነት ምክትል ሃላፊ ፣ በአሁኑ ጊዜ በም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመብራት ሃይል የቦርድ ሰብሰባ የሆኑት ዶ/ር ደብረ ጸዮን ገብረሚካኤል ስለአቶ ደበበ ምህረት ከሃላፊነት መነሳት ” እሱም የሚመሰገነውን ያክል ጉድለትም እንደነበረበት ይረዳል። ከሃላፊነቱ ሲነሳም አልደነገጠም።” በማለት መናገራቸው ይታወቃል። ምንም እንኳ ዶ/ር ደብረጺዮን አቶ ደበበ በብቃት ችግር እንደተነሱ አድርገው ለመገናኛ ብዙሀን ቢገልጹም፣ አቶ ምህረት ደበበ ግን በህወሃት ባለስልጣናት ስውር እጅ ሲቀነባበር የነበረውንና ኢትዮጵያን ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንድታጣ ያደረገውን ከፍተኛ ሙስና ሲቃወሙ እንደነበር ለጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ የቀረበው እና ለኢሳት የደረሰው የጸረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ሪፖርት ያስረዳል።
በ1999 እና በ2000 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የኤሌክትሪክ ኃይልን ተደራሽ ለማድረግ የሚረዱ ትራንስፎርመሮችን ለመግዛት ካወጣቸው አለም አቀፍ ጨረታዎች ጋር ተያይዞ በጨረታዎቹ ሂደት ላይ ግልጽነትና ኃላፊነት የጎደለው አሰራር መከሰቱንና ይህም የኤሌክትሪክ ኃይልን ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምርመራ በማድረግ የምርመራ ውጤቱን በወቅቱ በስልጣን ላይ ለነበሩት ለጠቅላይ ሚኒስትት መለስ ዜናዊ አቀረበ።
No comments:
Post a Comment