BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Sunday, 28 September 2014

በካናዳ ዊኒፔግ አለም አቀፍ የስብዓዊ መብት ሙዚየም ተከፈተ በሙዚየሙ በኢትዮጵያ በተለይም በቀይ ሽብር የተደረገው ግፍ ተካቷል።


በካናዳ ዊኒፔግ የስብዓዊ መብት ሙዚየም ከ2008 ጀምሮ ሲታነጽ ቆይቶ የ ሴፕቴምበር 20 በከፍተኛ ድምቀት ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኗል፡፡ይህን ሙዚዬም ለመገንባት አስካሁን ድረስ ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ፈጅቷል፡፡ 

ሕንጻው እንዲቆም የተመረጠበት ቦት በራሱ ታሪካዊ ነው፡፡ ይህ ቤተመዘክር የሆሎኮስትን፣ በካናዳውያን አቦርጅናሎች ላይ ስለተፈጸመው ግፍና ሌሎችንም በአለም ዙሪያ በርካታ የሰበዕዊ መብት መረገጥን ለጎብኝዎች ያቀርባል፡፡ የካናዳ ሰብዓዊ መብት ቤተመዘክር ዋናው ኣላማው1ኛ ስለ ሰብዓዊ መብት ዕውቀትና ግንዛቤ ለማስጨበጥ2ኛ ለሌላውም ወገን ከበሬታ ለማጎናጸፍና 3ኛ ውይይት፣ ግንዛቤንና ተርባራዊነትን ለማበረታታ ነው፡፡ 


 በዚህ ቤተመዘክር ውስጥ በዓለም ዙሪያ ስለሰበዓዊ መብት የተደረጉትን ታሪካዊ እንቅስቃሴዎችን ከሴፕቴምበር 20, 2014 ጀምሮ በቃዋሚነት ለሕዝብ ክፍት ተደርጓል፡፡በዚህ ቤተ መዘክር ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ታላላቅ የስብዓዊ መብት ተከራካሪ ስዎች ታሪክ ሲቀርብ ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው አስሮቹ ውስጥ የአሊ ታሪክ አንዱ ነው፡፡
አሊ ሁሴን ለሰብዓዊ መብት መከበር በተለይም የደርግ ቀይ ሽብር በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ላወረደው የሕይወትና የስነልቦና ጥፋት ደከመኝ ሳይል ፕሬዘዳንት ሆኖ በሚያገለግለው ሶሴፕ መልዕክቱን እያስተላለፈና እያስተማረ ይገኛል፡፡ የቀይ ሽብር ታሪክ በራሱ በአሊ ታሪክ ተሞርክዞ በካናዳው የሰበዓዊ መብቶች ሙዚየም ለመታየት በመብቃቱ ጀግናውን አሊንና ድርጅቱን ሶሴፕን የሚያስመሰግን እና በርታ የሚያሰኝ ነው፡፡ የአሊ የቀይ ሽብር ታሪክ ከላይ በተጠቀሰው ታሪክዋ ቆንጅት እንደገለጸችው “ My story is just one of the many, part of the many, an experience on its owns “ አሊም ከሚሊዮኖቹ የቀይ ሽብር ሰለባ አንዱ ነው፣ ታሪኩም የሚሊዮኖች አካል ነው፣ የድርሻው ተመክሮ ነው፡፡ አሊ አበክሮ እንደሚለው “ ስለ ደርግ ቀይ ሽብር የምናነሳው ብቀላን ለማካሄድ ሳይሆን ይህ መሰል ግፍና ኢሰብዓዊ ግፍ ዳግም እንዳይፈጸም ትምህርት ለመስጠት ነው፡፡
አቶ አሊ ሁሴን ማንንም ከማንም ሳይለይ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት በተለይም ለፖለቲካ እስረኞች በመከራከር የሚታወቀው የሶሴፕ ፕሬዘዳንት ናቸው።ከመቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊ ሰደተኞችን ከኬንያ እና ከሱዳን ወደ ካናዳ እንዲገቡ የረዱ ያስቻሉ ግለሰብ ናቸው።እጅግ መራራ የሆነውን ትግል በጽናት የቀጠሉ ጽኑ እና ታማኝ ኢትዮጵያዊ ናቸው።በርካታ ግጥም በመግጠምም ይታወቃሉ።አቶ አሊ ይህ ታሪክ የኔ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሰማእት ታሪክ ነው ብለዋል።

No comments:

Post a Comment