BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Friday, 19 September 2014

የቋራ ህዝብ አቤቱታ

መስከረም ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ በላይ የት ሄደን አቤት እንደምንል ግራ ተጋብተናልም በማለት በመንግስት አሰራር ማዘናቸውንም ተናገረዋል፡፡
የቋራ ከተማ ነዋሪዎች ከወራት በፊት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተገኙበት የጠየቋቸው የመልካም አስተዳደር ፣የመንገድ ፣የመብራት እና ስልክ ችግሮች ይፈታሉ በማለት አመራሮቹ ቃል ቢገቡም በዚህ አመት በተደለደለው የበጀት ቀመር ተጨማሪ በጀት ሳይያዝ መቅረቱ እንዳሳዘናቸው አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የወረዳዋ አመራሮች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

የነጋዴ ማህበር አመራር የሆኑት አቶ ገብረ ህይዎት ተሻገር የክልሉ አመራሮች በተገኙበት ያቀረቡት የነጋዴው አቤቱታ ከንግድና ኢንዱስትሪ ጋር ያለው መናበብ ከፍተኛ ልዩነት ያለው መሆኑን ገልጸው ባልሸጡበት ዋጋ በሚጠየቁት ግብር የተነሳ ነጋዴው ‘ይህ መንግስት ገደለን ’በማለት የሚያማርር መሆኑን ፊት ለፊት በመናገራቸው ያተረፉት ከስብሰባው በኋላ በዞን አመራሮች  ወከባ  እንጅ ምንምአይነት የግብር መሻሻል ለነጋዴው ማህበረሰብ እንዳልተደረገ በምሬት ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በድንበር አካባቢ ያለው የወቅቱን ሁኔታ በመግለጽ ለርእሰ መስተዳደሩ ያቀረቡት ኢንቨስተሮችና የአካባቢ ነዋሪዎች ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ባላት አዋሳኝ መሬት ዙሪያ የሱዳን ዜጎችና ወታደሮች ዘልቀው በመግባት መኪና መዝረፍ፣ዜጎችን መግደል እና በእሳት ማቃጠል በተደጋጋሚ ቢታይም በክልሉ መንግስት የተወሰደ ርምጃ ባለመኖሩ መቸገራቸውን ከወራት በፊት ቢገልጹም አሁንም ይኼው የጎረቤት ሃገር ጥቃት በመቀጠሉ ከአካባቢው በመሸሽ ለመኖር መገደዳቸውን በእርሻስራ የተሰማሩ ባለሃብትች ገልጸዋል፡፡
የኢንቨስትመንት ቦታ ያለ ጠረፍ ላይ ቢሆንም መከላከያ ሰራዊቱ ከተማ ላይ መሆኑ ሰራዊቱ ድንበርን ከማስከበር ይልቅ በየመጠጥ ቤቱ በመንቀሳቀስ የህብረተሰቡን ሰላም ሲያውክ እንደሚውል መታዘባቸውን ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡
ባለሃብቶቹ አክለውም በውች ሃገር ያሉ ዘመናዊ ትራክተሮችና ማሽኖችን ገዝተው በማስገባት እንዳይጠቀሙ በመታገድ ለስርአቱ አቀንቃኝ የሆኑ የመንግስት ባለስልጣናት ቤተሰቦች የሚያስመጧቸውን ማሽኖች በከፍተኛ የዋጋ ልዩነት እንዲገዙ መገደዳቸው አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ በመገኘት ለርእሰ መስተዳድሩ ቅሬታቸውን ካቀረቡት የቋራከተማ ነዋሪዎች መካከል የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካይ እንደተናገሩት ለሁሉም የእምነት ተቋማትና መንግስታዊ ድርጅቶች የቦታ ትክ ተሰጥቶ ቋሚ ቦታቸው ተከብሮ ባለበት ሁኔታ የሙስሊሙ ህብረተሰብ የአምልኮ ቦታ እስካሁን አለመከበሩ አግባብ እንዳልሆነ በምሬት ገልጸዋል፡፡ በጥንት ዘመን ‘አሞራ አገሩ ዋርካ-የእስላም ሃገሩ መካ’ የባል ነበር፡፡ አሁንም ይህ አስተሳሰብ በኛ ላይ እየጠንጸባረቀ ነው፡፡እኛ የተፈጠርነው ኢትዮጵያ ስለሆነ እንደ ኢትዮጵያዊ ልንታይ ይገባል፡፡ ሲሉ ተደምጠዋል ፡፡
ቅሬታ አቅራቢው አክለውም ኢህአዴግ በተለያዩ ቦታዎች የሚሰሩ ስራዎችን በአግባቡ ባለማወቁ ከሃላፊዎች የሚሰጠውን የውሸት ሪፖርት በማመኑ ኢህአዴግ እና ህዝቡ እየተራራቁ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡በአሁኑ ሰዓት ህብረተሰቡ የየተወከደበትን ቀን እየተራገመ ነው የሚሉት ቅሬታ አቅራቢበዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚንጓዝ ከሆነ ለሃገሪቱ የመበታተን ዕጣያሰጋታል በማልት በድፍረት ተናግረዋል ፡፡የተሸሙ ባለስልጣናት ሃላፊነትን በአግባቡ ከመስራት ይልቅ ስልጣናቸውን ለግልመጠቀሚያ እያደረጉ መሆኑንበአይናችን እያየን ነው በማለት ምሬታቸውን ሲገልጹ ተሰምተዋል ፡፡ ተወካዩ ይህን ቢያቀርቡም እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ አለማግኘታቸው እንዳሳዘናቸው ለዘጋቢያችን ገልጸዋል ፡፡
በውይይቱ እንዲገኙ የታሰቡት የተወሰኑ የስርአቱ ደጋፊዎች ብቻ እንዲሆኑ ቢታሰብም  ነዋሪችን ችግራችን እንገልጻለን በማለት በግድ በመግባታቸው አመራሮች ያላሰቡት ፈተና እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል ፡፡
ከወራት በፊት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በክልሉ የተለያዩ የሰሜን ጎንደር ጠረፍ ከተማዎች በመዘዋወር የህብረተሰቡን ችግር ለማድመጥ በሚል ቢንቀሳቀሱም የተጠየቁትን ችግሮች ለመፍታት ሳይሆን  ሕብረተሰቡ የተለያዩ ጸረ መንግስት ታጣቂ ቡድኖችን በውስጡ በማቀፍ ችግር እንዳይፈጥር እና ልዩ ልዩ ተስፋ በመስጠት መጭውን ምርጫ ያለስጋት ለማሸነፍ ሆን ብሎ በታቀደ መልኩ የምርጫው ዓመት በተቃረበ ቁጥር ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ የተለመዱ የቃል ማባበያዎች እና ማደናገሪያ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
ርእሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ በዞሩባቸው ከተሞች ተመሳሳይ ተቃውሞች እንዳጋጠማቸው ታውቋል ፡፡

No comments:

Post a Comment