የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ታጋዮች፤ ካነገቧቸው መሠረታዊ መርሆች አንዱ ፤ለሕዝብና ለሀገር
ታማኝነት ነው። ይኽ ዕምነታቸው ዘመን ተሻጋሪ ፤ ትውልድ አስከባሪ፤ ታሪክ መስካሪ ሆኖ አብሯቸው ዘልቋል ።
በዘለቄታ ቀጥለው እንዲዘልቁ ያስቻላቸውም ይኽው የማይበገር ፅኑ ዕምነታቸው ነው። ለሕዝብና ለሀገር ጠንካራ
ታማኝነታቸው ፤ በቦታ ፤ በጊዜና ፤ በሁኔታ የሚለወጥ የሚበረዝና የሚከልስ አለመሆኑን ያውቁታል ። ታማኝነት
የሚጀመረው ከራስ በመሆኑ፤ በራስ ዕምነት መተማመን፤ የአላማና የመርኅ ታማኝነትን ይወልዳል፤ ዕምነትን ያጠነክራል፤
አዕማደ-ትግል ሆኖ ፀንቶ ያፀናል ። ያበረታል -ያበረታታል ። ብርቱ ዕምነት፤ ፅኑ ዓላማ ካለ ደግሞ፤ ማነኛውንም
የማሳናክያ ዓለት ሁሉ ፤ የመረማመጃ ድንጋይ አድርጎ ረግጦ ያልፋል ።
የኢሕአፓ ታጋዮች፤ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ፤ የሚያስፈራቸው ነገር ቢኖር፤ ራሱ ፍርሃት ብቻ ነው። በትግላቸው
ሂደት ለፍርሃት ስከንዶች አይኖራቸውም ። ይኽን ባኅርይ ፤ ለአለፉት ግማሽ ምዕተ ዓመት በሚገባ አስመዝግበዋል ፡፡
BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!
Saturday, 28 January 2017
Wednesday, 18 January 2017
የኢትዮጵያ ወጣቶች ቀጣይ ትግል ቀጣይ ቃል ኪዳን
ዴሞክራሲያ ቅጽ 42 ቁ. 3 ታኅሣሥ 2009
ከፋሽስት ጣሊያን ወረራ በኋላ የመጣው ኢትዮጵያዊ ትውልድ በተለይም ፊደል ለመቁጠርና ዘመናዊ ትምህርት ለመቅሰም እድሉን ያገኘው ክፍል፤ የወገኑና የአገሩ ችግርና ብሶት እጀግ ያንገበገበው፤ ያሳሰበው ነበር። ለውስብስብ ችግሮቹ መፍትሔ ለመሻት ብዙ ጥሯል። በአፍላ የወጣትነት ዘመኑም የራሱን ጥቅምና ፍላጎት ለአገርና ለወገኑ አሳልፎ የሰጠ፤ ወደር የማይገኝለት ትውልድ በመሆኑ ታሪክ ዘወትር ሲያስታውሰው ይኖራል። በ1950ዎቹ መጨረሻና በ60ዎቹ መጀመሪያ የነበረው ወጣት ትውልድ የአገሩን ሁኔታ እንዴት መለወጥ እንደሚችል አበከሮ በመጠየቅ፤ የወቅቱን አገር አቀፍና የዓለም አቀፉን ተጨባጭ ሁኔታ በማገናዝብና ተገቢውንም ትምህርት በመቅሰም፤ አገራችን በተሻለ የእድገት፣ የልማትና የፍትኅ ጎዳና እንድትራመድ አቅሙ በፈቀደ መጠን ኃላፊነቱን ለመወጣት ጥረት አድርጓል።

Tuesday, 17 January 2017
ኢትዮጵያ: የጭካኔና ገደቦች አመት
መብቶች ይከበሩ፣ ለህዝብ ቅሬታዎች መልስ ይሰጥ
(ናይሮቢ ጥር 12፣ 2017) – እ.ኤ.አ. በ 2016 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ቀዉስ ዉስጥ ወድቃለች። ሂዩማን ራይትስ ወች ዛሬ በወጠው የ 2017 ዓ.ም. የአለም ዓቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባወጀችበት በዚህ ወቅት መሰረታዊ መብቶችን በመገደብና ሰለማዊ ሰልፈኞች ላይ የከፈተችዉን ደም አፍሳሽ አፈናን ቀጥላበታለች ብሏል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዘፈቀዳ ማሰርን ይፈቅዳል፣ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን ይገድባል፣ አንዲሁም ከውጭ አካላት ጋር መገናኘትን ይከለክላል።
Monday, 9 January 2017
Ethiopia targets opposition who met with European lawmakers
ADDIS ABABA, Ethiopia (AP) — Ethiopia said Monday it will not release a leading opposition figure detained under the country's state of emergency after meeting with European lawmakers in Belgium.
Prime Minister Hailemariam Desalegn told reporters that Merara Gudina of the Oromo Federalist Congress party instead will face justice.
Subscribe to:
Posts (Atom)