BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Tuesday, 17 January 2017

ኢትዮጵያ: የጭካኔና ገደቦች አመት

 መብቶች ይከበሩ፣ ለህዝብ ቅሬታዎች መልስ ይሰጥ 
(ናይሮቢ ጥር 12፣ 2017) – እ.ኤ.አ. በ 2016 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ቀዉስ ዉስጥ ወድቃለች። ሂዩማን ራይትስ ወች ዛሬ በወጠው የ 2017 ዓ.ም. የአለም ዓቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባወጀችበት በዚህ ወቅት መሰረታዊ መብቶችን በመገደብና ሰለማዊ ሰልፈኞች ላይ የከፈተችዉን ደም አፍሳሽ አፈናን  ቀጥላበታለች ብሏል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዘፈቀዳ ማሰርን ይፈቅዳል፣ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን ይገድባል፣ አንዲሁም ከውጭ አካላት ጋር መገናኘትን ይከለክላል።

በዚህ ዓመት የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በኦሮሚያና ኣማራ ክልሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰለማዊ ሰልፈኞችን ገድሏል፣ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩትን ዕስር ቤት ኣጉሯል። ታስረው ከተፈቱት ብዙዎቹ በእስር ቤት ዉስጥ ስቃይ አንደደረሰባቸው ታናግረዋል። ይህ እስረኞችን የማሰቃየት ችግር ኢትዮጵያ ዉስጥ ለረጅም ግዜ ሳይፈታ የዘለቀ ችግር ነው። መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ያደረሱትን በደሎች በተገቢው መልኩ ለመመርመርም ሆና ለአለማቀፍ ምርመራ ጥሪውች  መልስ መስጠት አልቻለም።
የታጠቁ የመንግስት ወታደሮች በመስከረም ወር 2009 ዓ. ም በቢሾፍቱ ኢትዮጵያ በተከበረው የኢሬቻ በአል ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰዎችን ሲመለከቱ።
የታጠቁ የመንግስት ወታደሮች በመስከረም ወር 2009 ዓ. ም በቢሾፍቱ ኢትዮጵያ በተከበረው የኢሬቻ በአል ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰዎችን ሲመለከቱ።
‘’የኢትዮጵያ መንግስት እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም. የቀረቡለትን ብዙ የማሸሻያ ጥሪዎችን በአግባቡ ማየትና ማሰተካከል ሲገባው ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለማፈን ያልተመጣጠነና አላስፈላጊ ሀይል ተጠቅሟል’’ ብሏል ፌሊክስ ሆርኔ በሂውማን ራይትስ ወች ከፍተኛ የአፍሪካ ተመራማሪ። ‘’የማይጨበጡ የታህድሶ ተስፋዎች በቂ አይደሉም። መንግስት ሁሉንም ትችቶች በሀይል ለማፈን ከመሞከር ይልቅ መሰረታዊ መብቶችን መመለስና ትርጉም ያለዉ ዉይይት ዉስጥ መግባት አለበት።’’ ብሏልፌሊክስ ሆርን
በባለ 687 ገጹ የዓለም ሪፖርት 27ተኛ እትም ሂውማን ራይትስ ወች ከ90 በላይ በሆኑ ሃገራት ያለውን የሰብዓዊ መብት ትግበራ ገምግሟል። በዚህ የማስተዋወቂያ ጽሁፍ ዋና ዳይሬክተር ኬንዝ ሮዝ አዲስ የህዝባዊ አገዛዝ ትውልዶች የሰብዓዊ መብቶችን ጽንሰ ሃሳብ ለመቀልበስ መሻታቸውን ጽፈዋል፤ መብትን የሚያስተናግዱበት መንገድ የብዙሃንን ፍላጎት ለመገደብ ባመቸ መልኩ መሆኑን ጽሁፋቸው ይገልጻል። ከዓለም ዓቀፉ የምጣኔ ሃብታዊ እድገት ትርፍ ተቋዳሽ እንዳልሆኑ የሚሰማቸው ሰዎች እና እየጨመረ ባለው የብጥብጥ ስጋት የሲቪክ ማህበረሰብ ቡድኖች፣ መገናኛ ብዙሃን እና ህዝቡ መብቶችን የሚያከብር ዴሞክራሲ እንዲገነባ አወንታዊ ሚና መጫወት አለባቸው።
የፀጥታ ሃይሎች በጥቅምት ወር የእሬቻ በዓልን ለማክበር የወጣውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ለመቆጣጠር የተጠቀሙት ያልተገባ አያያዝ ምክንያት ሰዎች እርስ በእርስ በመረጋገጣቸው ምክንያት በርካቶች በመሞታቸው የተቃውሞ ስልፈኞቹ ብስጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በምላሹም የተናደዱት ወጣቶች፣ በተለይም በኦሮሚያ ክልል የግልና የመንግስት ንብረቶችን አውድመዋል። ከዚህ በኋለ ነበር መንግስት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በማዋጅ በሰልፉ ግዜ የጸጥታ ሀይሎች ሰልፈኞች ላይ ላደረሷቸው በደሎች ህጋዊ ሽፋን በማላበስ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ላቀረቡት ጥያቀዎች የበለጠ ወታደራዊ መልስ አንደሚሰጥ ያመላከተው።
ሂዩማን ራይትስ ወች እንዳለው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽና መረጃ የማግኘት መብት ላይ መንግስት የጣለው ገደብ እንኳንስ ችግሩን ሊፈታ የተቃዋሚዎቹን ቅሬታዎች ለመረዳት የሚያስፈልገዉን ሁሉን ኣቀፍ ፖሎቲካዊ ዉይይት አቅም ያዳክማል
እ.ኤ.አ. በ 2016 ዓ.ም. ከታሰሩት በአስር ሽዎች ከሚቆጠሩት አስረኞች መካከል፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪዎች፣ ሙዚቀኞች፣ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች ይገኙበታል። አንደነ በቀላ ገርባ ያሉ ለዘብተኘ የሚባሉ የፖሊቲካ ፓርቲ መሪዎች በሽብር ተከሰው እስር ቤት ተወርውረዋል። የመማር ማስተማሩ ሂደት ተስተጏጉሏል፣ በሽዎች የሚቁጠሩት ደግሞ ሀገር ጥለው ተሰደዋል።
ልዩ ፖሊስ የሚባሉት የመከለከያ ሰራዊት ተወርዋሪ ሃይሎች እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም. በሶማሌ ክልል ነዋሪዎች ላይ ብዙ ግፎችን ፈጽመዋል። በኢትዮጵያ ልማት ፕሮጀቶች ምክንያት ዜጎችን ከቄዬቸው ማፈናቀሉ ኦሞ ሸለቆን ጨምሮ በብዙ ቦታዎች ቀጥሏል።
እ.ኤ.አ. የ 2016ቱ አፈና ለዓመታት በተቃዋሚ ፓርትዎች፣ ሲቪክ ማህበራትና ገለልተኛ የሚዲያ ተቋማት ላይ ሲደረግ የነበረው ስልታዊ ጥቃት ቅጥያ ሲሆን የፖሊቲካ ምህዳሩን በደንብ በመዝጋት ተቀዋሚ ድምጾችን መተንፈሻ አሳጥቷል።
 

No comments:

Post a Comment