BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

BRIGHT FUTURE FOR ETHIOPIANS !!!

Friday, 28 November 2014

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለአዳር የሚቆይ ተቃውሞ በመስቀል አደባባይ ለማካሄድ የእውቅና ጥያቄ አቀረበ

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- ትብብሩ ህዳር 18 ለመስተዳድሩ ባስገባው የእውቅና ጥያቄ ፣ የተቃውሞ ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ከህዳር 27 እስከ ህዳር 28፣ 2007 ዓም ለማካሄድ ማቀዱን ገልጿል።
የእውቅና ደብዳቤውን ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር፣ የከንባታ ህዝቦች ሊቀመንበርና የትብብብሩ ም/ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ፣ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የትብብሩ ፀኃፊ እና የመኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ አቶ ኑሪ ሙደሲር በጋራ ማስገባታቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን” “ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”



“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል”
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት

ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡

Monday, 17 November 2014

እንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ደብዳቤ መጻፏን ወያኔ አረጋገጠ


የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ለወያኔዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ደብዳቤ መጻፋቸውንና ወያኔም አቋሙን ግልጽ ማድረጓን የወያኔዉ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ተናገረ። ሬድዋን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባለፈዉ ማክሰኞ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ዴቪድ ካሜሩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደብዳቤ መጻፋቸውን የተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ሰምቻለሁ ካለ በኋለ “ለምን ጻፉ ማለት አይቻልም፤ ጥያቄዉ መሆን ያለበት ምን መለሳችሁ ነው፤” በማለት የተለመደ የማጭበርበሪያ ቃላት ደርድሯል።

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ።


Imageኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ። በደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ አንጎላዊው ጋዜጠኛ ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች መፍታት አለበት ብሏል።

ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ አንጎላዊ ጋዜጠኛ ነው። በሙያው በሃገሩ አንጎላ በርካታ ክስ እና እስር እንደገጠመው ይነገራል። ባለፈው ወር በደቡብ አፍሪካ ዊትስ በተካሄደው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽን ጨምሮ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ጥሰት በመፈጸም ከአፍሪካ ህብረት ህልም በተቃራኒ ቆማለች በማለት ተችቷል። ''የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በቀዳሚነት የመላ አፍሪካውያንን ህልም ይወክላል።

Sunday, 16 November 2014

በዝነኛው ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ (ገሞራው) ዜና እረፍት የተነሳ ከ ኢሕአፓ የተሰጠ መግለጫ

እውቁ ገጣሚ፥ ታላቁ ደራሲና ግዙፉ የሀገራችን ቅርስ ለረጅም ዓመታት በስደት መከራውን ሲያይ
በቆየበት በስቶክሆልም (ስዊድን) ከተማ በዚህ ሰሞን አርፏል። ታዋቂዋንና አቻ የሌላትን በረከተ
መርገምንና በርካታ ሊሎች የግጥም መድበሎችንና ድርሰቶችን ያቀረበው ኃይሉ በቤተ ክህነት ትምህርት
የላቀ ዕውቀት የነበረው፤ የቅኔም አባት ሆኖ የቆየ ታላቅ የአገር ቅርስ ነበር ።
ኃይሉ ለዘመናዊው ትምህርት ወደ ዩኒቨርስቲ ከገባ ተጀምሮ በተራማጅ አስተሳሰብን ያንጸባርቅ በነበረው
የተማሪ እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ሆኖ ሲታገል ከሌሎች ስምንት ተማሪዎች ጋር ከዩኒቨርስቲ ተባሮ
እንደነበር ይታወቃል ። ገሞራው በአጼው ዘመን ሲታገል በተደጋጋሚ ለበርካታ ጊዜዎች ተይዞ ታስሮ
የነበረ ሲሆን ጨካኝ በሆኑ የጸጥታ ሰራተኞች ድብደባና ስቃይን ተቀብሏል ።

ተማሪዋ በተሳፈረችበት ታክሲ ታፍና ተወስዳ በደረሰባት አስገድዶ መድፈር ሕይወቷ አለፈ


ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል
በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቄራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አየር ጤና አካባቢ አንዲት የአሥረኛ ክፍል ተማሪ በተሳፈረችበት ታክሲ ታፍና ከተወሰደች በኋላ በደረሰባት አስገድዶ መደፈር ጉዳት ሕይወቷ ማለፉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
ሟቿ ተማሪ ሃና ላላንጎ ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. አየር ጤና በተለምዶ ሳሚ ካፌ በሚባለው አካባቢ በአንድ ሚኒባስ ውስጥ ተሳፍራ ወደ ጦር ኃይሎች እየመጣች እንደነበር ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ ከትምህርት ቤት ወጥታ ወደ ቤተሰቦቿ በመጓዝ ላይ የነበረችው ሟች ተማሪ የተወሰነ ርቀት ከተጓዘች በኋላ መድረሷን ተናግራ ‹‹ወራጅ አለ›› ስትል፣ በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ አራት ወንዶችና ሾፌሩ ስለት በማውጣት አስፈራርተው እንዳገቷትም ተጠቁሟል፡፡

Tuesday, 11 November 2014

ፓርቲዎች ለሃይማኖት ተቋማት ጥሪ አቀረቡ

ጥቅምት (ሠላሳቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ››በሚል መርህ ትብብር  የመሰረቱት 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቀደም ብለው ባሳወቁት የአንድ ወር መርሃ ግብር መሰረት የጀመሪያውን ጥሪ ለሃይማኖት ተቋማት አድርገዋል።
ፓርቲዎቹ አገራችንና ህዝቧ በተፈጥሮ ሚዛን መዛባት በሚከሰትበትም ጊዜ ሆነ በአገዛዝ ሥርዓቶች ምክንያት በችግር ውስጥ በሚወድቁበት ጊዜ የኃይማኖት  ተቋማትና ምዕመናን ሚና ከፍተኛ እንደነበር አውስተው፣ ዛሬ ላይ እነዚህ የሞራልና ሥነ-ምግባር እሴቶች እየተናዱ በመሄዳቸው ዜጎች ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ተጋልጠዋል፣ የአገር ፍቅር ስሜት በጥያቄ ውስጥ ወድቋል ብለዋል።