ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትብብሩ ህዳር 18 ለመስተዳድሩ ባስገባው የእውቅና ጥያቄ ፣ የተቃውሞ ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ከህዳር 27 እስከ ህዳር 28፣ 2007 ዓም ለማካሄድ ማቀዱን ገልጿል።
የእውቅና ደብዳቤውን ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር፣ የከንባታ ህዝቦች ሊቀመንበርና የትብብብሩ ም/ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ፣ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የትብብሩ ፀኃፊ እና የመኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ አቶ ኑሪ ሙደሲር በጋራ ማስገባታቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
የትብብሩ አመራሮች ወደ መስተዳድሩ በሄዱበት ወቅት የአቶ ማርቆስ ተወካይ ለሆኑት አቶ ፈለቀ አበበ ደብዳቤውን ለመስጠት ጥረት ማድረጋቸውንና ‹‹የከንቲባ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው የለም፣ እሱ ካልመራበት መቀበል አንችልም›› በሚል ደብዳቤውን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን የገለጸው ነገረ ኢትዮጵያ፣ የትብብሩ አመራሮች ታመዋል በተባሉት በአቶ ማርቆስ ተወካይ በአቶ ፈለቀ ቢሮ በአራት ምስክሮች ፊት ደብዳቤውን ማስቀመጣቸውን ዘግቧል፡፡ አመራሮቹ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በፈጣን መልዕክት መላካቸውንም ጋዜጣው ዘግቧል።
ለአንድ ቀንና ሌሊት የሚካሄደው ተቃውሞ ህዳር 27 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ተጀምሮ ህዳር 28 ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል። በጉዳዩ ዙሪያ የ9ኙ ፓርዎች ትብብር ገንዘብ ያዥና የመኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ኑሪ ሙደሲርን ስቱዲዮ ከመግባታቸው በፊት አነጋገርናቸዋል
No comments:
Post a Comment